መዝሙር 43 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉምየስደት ጊዜ ጸሎት 1 አምላክ ሆይ! ፍረድልኝ፤ በአንተ ከማያምኑ አሕዛብ ፊት ስለ እኔ ተከራከርልኝ፤ ከአታላዮችና ከክፉ ሰዎችም እጅ አድነኝ። 2 አንተ አምላኬ፥ ጠንካራ ምሽጌ ነህ፤ ታዲያ፥ ስለምን ትተወኛለህ? ለምንስ ጠላቶቼ እያበሳጩ ያሳዝኑኝ? 3 ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤ እነርሱ እየመሩ ወደ ተቀደሰው ተራራህ፥ ወደ ማደሪያ መቅደስህም ያምጡኝ። 4 አምላክ ሆይ! ከዚያም በኋላ ለአንተ ለምታስደስተኝ ወደ መሠዊያህ ሄጄ እሰግድልሃለሁ፤ አንተ አምላኬ ነህ፤ በገናዬን እየደረደርኩ አመሰግንሃለሁ። 5 እኔ ለምን ተስፋ እቈርጣለሁ? ለምንስ እጨነቃለሁ? በእግዚአብሔር እተማመናለሁ። ስለሚረዳኝም እርሱን አመሰግናለሁ። |