ኤርምያስ 9:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ጠቢብ በጥበቡ፥ ብርቱ ሰውም በኀይሉ፥ ባለጸጋም በሀብቱ አይመካ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ጥበበኛ በጥበቡ አይታበይ፤ ኀያልም በኀይሉ አይመካ፤ ሀብታምም በሀብቱ አይኵራራ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፤ ኀያልም በኀይሉ አይመካ፤ ባለጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፥ |
ከእኔ በኋላ የሚመጣው ጠቢብ ይሁን ሞኝ ተለይቶ አይታወቅም፤ ይሁን እንጂ እኔ የደከምኩበትንና በጥበቤ ያተረፍኩትን ነገር ሁሉ ወስዶ ባለቤት ይሆናል፤ ይህም ከንቱ ነው።
በዚህ ዓለም የተመለከትኩት ሌላም ነገር አለ፤ ይኸውም ፈጣን ሯጮች በአሸናፊነት አይወጡም፤ ጀግኖችም በጦርነት ድል አያደርጉም፤ ጠቢባን የዕለት እንጀራን፥ ብልኆች ሀብትን አያገኙም፤ ችሎታ ያላቸውም ሰዎች በማዕርግ አያድጉም፤ ነገር ግን ሁሉንም ጊዜና ዕድል ያጋጥማቸዋል፤
ከእንግዲህ ወዲህ ‘እግዚአብሔርን ዕወቅ’ ብሎ ባልንጀራውንም ሆነ ወንድሙን የሚያስተምር ማንም አይኖርም፤ ከትልቁ ጀምሮ እስከ ትንሹ ሁሉም ያውቁኛል፤ በደላቸውን ይቅር እልላቸዋለሁ፤ ኃጢአታቸውንም አላስታውስባቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
“የሞአብ ሕዝብ ሆይ! በኀይላችሁና በሀብታችሁ ብዛት ተማምናችሁ ነበር፤ አሁን ግን እነሆ እናንተ ራሳችሁ እንኳ ትማረካላችሁ፤ ከሞሽ ተብሎ የሚጠራው ጣዖት ከልዑላን መሳፍንትና ከካህናቱ ጋር ተማርኮ ይወሰዳል።
እየቀነሰ በሚሄደው ኀይላችሁ የምትመኩት ለምንድን ነው? እናንተ እምነተቢስ ሕዝብ ሆይ! ‘አደጋ የሚጥልብኝ ማነው?’ ብላችሁ በሀብታችሁ ክምችት ተመክታችኋል።
ግብጽም ባዶዋን ምድረ በዳ ሆና ትቀራለች። በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ። “ ‘አንተ የዓባይ ወንዝ የእኔ ነው፤ ይህን ወንዝ የሠራሁት እኔ ነኝ’ ብለሃልና።
ብራቸውን በየመንገዱ ላይ ይወረውራሉ፤ ወርቃቸውም እንደ ርኩስ ነገር ይቈጠራል፤ ብርና ወርቃቸው በእግዚአብሔር ቊጣ ቀን አያድኑአቸውም፤ ራባቸውን አያስወግዱላቸውም፤ ወይም ሆዳቸውን አይሞሉላቸውም፤ በኃጢአት ለመውደቃቸው ምክንያት የሆኑባቸው እነርሱ ናቸው።
እንግዲህ የመለከት፥ የእንቢልታ፥ የመሰንቆ፥ የክራር፥ የበገና፥ የዋሽንትና፥ የሙዚቃም ሁሉ ድምፅ ስትሰሙ ላቆምኩት ምስል በመሬት ላይ ተደፍታችሁ ብትሰግዱ መልካም ነው፤ ባትሰግዱ ግን በሚነደው የእሳት ነበልባል ጒድጓድ ውስጥ ወዲያውኑ ትጣላላችሁ፤ ከእጄም የሚያድናችሁ አምላክ እንደሌለ ዕወቁ።”
“እነሆ፥ እኔ ናቡከደነፆር ለሰማይ ንጉሥ ምስጋና፥ ክብርና ውዳሴ አቀርባለሁ፤ እርሱ የሚያደርገው ነገር ሁሉ ትክክል ነው፤ መንገዱም ፍትሓዊ ነው፤ በትዕቢት የሚመሩትንም ሁሉ ማዋረድ ይችላል።”
እግዚአብሔር መልካም የሆነውንና ከአንተ የሚፈልገውን ነግሮሃል፤ ይኸውም ፍትሕን እንድትጠብቅ፥ ደግነትን እንድትወድ፥ ከአምላክህ ጋር በትሕትና እንድትመላለስ ነው።
እግዚአብሔር ቊጣውን በሚገልጥበት በዚያን ቀን ሰዎችን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፤ እንደ እሳት ባለው ቅናቱ ምድር ሁሉ ትጠፋለች፤ ይህም የሚሆነው በዓለም የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በድንገት የሚያልቁ ስለ ሆነ ነው።
ደቀ መዛሙርቱም በቃሉ ተደነቁ፤ ኢየሱስ ግን መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “ልጆች ሆይ! ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንዴት አስቸጋሪ ነው!
ከዚህም በቀር ጌታዬን ኢየሱስ ክርስቶስን ከማወቅ የበለጠ ሌላ ምንም ነገር እንደሌለ ስለማምን ሁሉን ነገር እንደ ኪሣራ እቈጥረዋለሁ፤ ስለ እርሱም ሁሉን ነገር አጥቻለሁ። ክርስቶስንም ለማግኘት ስል ሁሉን ነገር እንደ ቤት ጥራጊ እቈጥራለሁ።