Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዮብ 32:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ለኢዮብ ተገቢ መልስ ሊሰጠው የሚችል እግዚአብሔር እንጂ ሰው ስላልሆነ፥ እናንተ ጥበብን አግኝተናል ብላችሁ በከንቱ አትመኩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ‘እኛ ጥበብ አግኝተናል፤ ሰው ሳይሆን እግዚአብሔር ይርታው’ አትበሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እናንተም፦ ጥበብን አግኝተናል፥ እግዚአብሔር ነው እንጂ ሰው አያሸንፈውም እንዳትሉ ተጠንቀቁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እና​ን​ተም፦ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበ​ብን አግ​ኝ​ተ​ናል፤ አብ​ዝ​ተ​ና​ልም እን​ዳ​ትሉ ተጠ​ን​ቀቁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 እናንተም፦ ጥበብን አግኝተናል፥ እግዚአብሔር ነው እንጂ ሰው አያሸንፈውም እንዳትሉ ተጠንቀቁ።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 32:13
23 Referencias Cruzadas  

አንተ ‘አብራምን ሀብታም ያደረግኹት እኔ ነኝ’ እንዳትል ሌላው ቀርቶ አንዲት ክር ወይም የጫማ ማሰሪያ እንኳ ከአንተ አልወስድም።


“ከእናቴ ማሕፀን ራቁቴን ተወለድኩ፤ ስሞትም ራቁቴን እሄዳለሁ፤ እግዚአብሔር ሰጠ፤ እግዚአብሔር ወሰደ፤ የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን!” አለ።


“በእርግጥ እናንተ በጣም ብልኆች ናችሁ፤ ስትሞቱም ጥበብ ከእናንተ ጋር የምትሞት ይመስላችኋል!


“ወዳጆቼ ሆይ! የእግዚአብሔር እጅ ስለ መታኝ እባካችሁ እናንተ እዘኑልኝ! ራሩልኝም!


ነገር ግን ይህን ሁሉ መከራ ያደረሰብኝና መረብ ውስጥም የጣለኝ እግዚአብሔር መሆኑን እንድታውቁ እወዳለሁ።


ኢዮብም “እንዴት የሞኝ ሴት ንግግር ትናገሪያለሽ? እግዚአብሔር መልካም ነገር ሲሰጠን በደስታ እንቀበላለን፤ ታዲያ፥ መከራ ሲያመጣብን በእርሱ ላይ ማጒረምረም ይገባናልን?” አላት። ኢዮብ ምንም እንኳ ይህ ሁሉ መከራና ሥቃይ ቢደርስበት በእግዚአብሔር ላይ ክፉ ነገር በመናገር ኃጢአት አልሠራም።


በዚያች መሬት ላይ በስንዴ ፈንታ እሾኽ፥ በገብስ ፈንታ አረም ይብቀል።” የኢዮብ ንግግር እዚህ ላይ ተፈጸመ።


በጥንቃቄ አደመጥኳችሁ፤ ሆኖም፥ ማንም ኢዮብን ለማስተባበል የቻለ የለም፤ ከእናንተም መካከል ለእርሱ ንግግር አጥጋቢ መልስ የሰጠ የለም።


ኢዮብ የተከራከረው ከእናንተ ጋር እንጂ ከእኔ ጋር አልነበረም፤ እኔም በእናንተ አነጋገር ዐይነት አልመልስለትም።


በእግዚአብሔር እስትንፋስ ይጠፋሉ፤ በቊጣውም ማዕበል ይደመሰሳሉ።


ሁሉን የሚችል አምላክ በፍላጻዎቹ ወግቶኛል፤ መርዛቸውም በሰውነቴ ተሠራጭቶአል፤ የሚያስደነግጥ የእግዚአብሔር መቅሠፍት ዙሪያዬን ከቦኛል።


ስለ እነዚህ ነገሮች ሁሉ አስቀድሜ ነግሬአችኋለሁ፤ ከመፈጸማቸውም በፊት አስታውቄአችኋለሁ፤ ይህንንም ያደረግኹት ‘ጣዖቶቻችን ይህን አደረጉ፤ የእንጨትና የብረት ምስሎቻችን ይህን ወሰኑ’ እንዳትሉ ነው።


እነርሱ ከብዙ ጊዜ በፊት ሳይሆን አሁን የተፈጠሩ ናቸው፤ እናንተም ‘ቀደም ብለን ዐውቀናቸዋል’ እንዳትሉ ከአሁን በፊት ከቶ አልሰማችኋቸውም።


ራሳቸውን ብልኆችና ጥበበኞች አድርገው ለሚቈጥሩ ወዮላቸው!


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ጠቢብ በጥበቡ፥ ብርቱ ሰውም በኀይሉ፥ ባለጸጋም በሀብቱ አይመካ፤


ከዳንኤል ይበልጥ ጥበበኛ የሆንክ ይመስልሃል፤ ምንም ምሥጢር እንደማይሰወርብህም ታስባለህ፤


“እኔ እግዚአብሔር በመጀመሪያ ለይሁዳ ነገድ ድልን አጐናጽፋለሁ፤ ይህንንም የማደርገው የዳዊት ልጆች ክብርና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ክብር ከሌሎቹ የይሁዳ ነገድ ተወላጆች ከፍ ከፍ እንዳይል ነው።


ኢየሱስም “ከእግዚአብሔር ሥልጣን ባይሰጥህ ኖሮ በእኔ ላይ ምንም ሥልጣን ባልኖረህ ነበር፤ ሆኖም ለአንተ አሳልፎ የሰጠኝ የባሰ ኃጢአት አለበት” አለው።


ማንም ራሱን አያታል፤ በዚህ ዓለም የጥበብ ደረጃ ጥበበኛ መስሎ የሚታይ ቢኖር የእግዚአብሔርን እውነተኛ ጥበብ እንዲያገኝ ራሱን እንደ ሞኝ ይቊጠር።


እግዚአብሔርም ጌዴዎንን እንዲህ አለው፦ “በምድያማውያን ላይ ድልን አቀዳጃቸው ዘንድ ከአንተ ጋር ያሉ ሰዎች ለእኔ እጅግ ብዙ ሆነዋል፤ በራሳቸው ኀይል የሚያሸንፉ ስለሚመስላቸው ለእኔ ክብር ከመስጠት ይቈጠባሉ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos