Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 48:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 “የሞአብ ሰዎች ሆይ! ‘እኛ ተዋጊ አርበኞችና በጦርነት የተፈተንን ወታደሮች ነን’ ብላችሁ ስለምን ትመካላችሁ? አጥፊው መጥቶአል፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 “እናንተ፣ ‘እኛ ተዋጊዎች ነን፤ በጦርነትም ብርቱ ነን’ ልትሉ እንዴት ቻላችሁ?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 እናንተ፦ እኛ ኃያላን በውጊያም ጽኑዓን ነን፥ እንዴት ትላላችሁ?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እና​ንተ፦ እኛ ኀያ​ላን በሰ​ል​ፍም ጽኑ​ዓን ነን እን​ዴት ትላ​ላ​ችሁ?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እናንተ፦ እኛ ኃያላን በሰልፍም ጽኑዓን ነን እንዴት ትላላችሁ?

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 48:14
12 Referencias Cruzadas  

ንጉሥ በሠራዊቱ ብዛት አይድንም፤ አርበኛም በከፍተኛ ኀይሉ አያመልጥም።


ስለዚህ ጌታ የሠራዊት አምላክ በግዙፉ ሠራዊቱ ላይ የሚያመነምን በሽታ ይልክበታል፤ በሰውነቱም ውስጥ እንደ እሳት የሚያቃጥል ትኲሳት ይልክበታል።


የአሦር ንጉሠ ነገሥት በመደንፋት ሲናገር እንዲህ ብሎአል፦ “ይህን ሁሉ ያደረግኹ እኔ ራሴ ነኝ፤ እኔ ብርቱ፥ ዐዋቂና ብልኅ ነኝ፤ በመንግሥታት መካከል የነበረውን ወሰን አፈራረስኩ፤ ያካበቱትንም ሀብት ሁሉ ወሰድኩ፤ በእነዚያም አገሮች የሚኖሩትን ሕዝብ ሁሉ በጀግንነቴ አዋረድኳቸው።


የሞአብና የዐሞን ሕዝብ በሠራዊት አምላክ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ስላፌዙና ስለ ዛቱ ይህ ቅጣት የሚደርስባቸው ለትዕቢታቸው አጸፋ የሚከፈል ዕድል ፈንታቸው ስለ ሆነ ነው።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ከሚግዶል ጀምሮ እስከ አስዋን ድረስ የግብጽ ደጋፊዎች በጦርነት ያልቃሉ፤ የግብጽም ዕብሪተኛ ኀይል ይዋረዳል። እኔ ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።


አለታማው ገደል ላይ የምትኖሪ፥ እስከ ተራራማው ጫፍ ድረስ የምትደርሽ ሆይ! ተፈሪነትሽና የልብሽ ኲራት አታለውሻል፤ ምንም እንኳ መኖሪያሽን እንደ ንስር ጎጆ ብታደርጊ እኔ ከዚያ ላይ አወርድሻለሁ ይላል እግዚአብሔር።”


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ጠቢብ በጥበቡ፥ ብርቱ ሰውም በኀይሉ፥ ባለጸጋም በሀብቱ አይመካ፤


ታዲያ ‘እኛ ጠቢባን ነን፤ የእግዚአብሔርንም ሕግ እናውቃለን’ የምትሉት ስለምንድን ነው? ሐሰተኞች ጸሐፊዎች ሕጌን እንዳዛቡ አትመለከቱምን?


የይሁዳ ሕዝብ እንዲህ ይላሉ፦ “የሞአብ ሕዝብ ምን ያኽል ኩራተኛ መሆኑን፥ ትዕቢተኛነቱን፥ ዕብሪተኛነቱንና ንቀቱን ሰምተናል፤ ነገር ግን ፉከራው ሁሉ ከንቱ ነው።”


በዚህ ዓለም የተመለከትኩት ሌላም ነገር አለ፤ ይኸውም ፈጣን ሯጮች በአሸናፊነት አይወጡም፤ ጀግኖችም በጦርነት ድል አያደርጉም፤ ጠቢባን የዕለት እንጀራን፥ ብልኆች ሀብትን አያገኙም፤ ችሎታ ያላቸውም ሰዎች በማዕርግ አያድጉም፤ ነገር ግን ሁሉንም ጊዜና ዕድል ያጋጥማቸዋል፤


እግዚአብሔር ከለላዬ ነው፤ እንዴት “እንደ ወፍ ወደ ተራራዎች ሽሽ” ትሉኛላችሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios