Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ቆሮንቶስ 1:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 እንግዲህ በመጽሐፍ እንደ ተጻፈው “የሚመካ በጌታ ይመካ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 እንግዲህ፣ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው፤ “የሚመካ በጌታ ይመካ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ስለዚህ፥ እንደተጻፈው ይሆን ዘንድ፥ “የሚመካ በጌታ ይመካ፤”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 መጽ​ሐፍ እንደ አለው ይሆን ዘንድ “የሚ​መ​ካስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመካ።”

Ver Capítulo Copiar




1 ቆሮንቶስ 1:31
13 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን “የሚመካ በጌታ ይመካ።”


እኛ እግዚአብሔርን በመንፈስ የምናመልክና በውጭ በሚታየው ሥርዓት ሳይሆን በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ የምንመካ ስለ ሆንን በእውነት ተገርዘናል።


በቅዱስ ስሙ ደስ ይበላችሁ! እግዚአብሔርን የሚፈልግ ሰው ሁሉ ሐሴት ያድርግ!


ወደ ሰማይ ትበትናቸዋለህ፤ ነፋስም ጠራርጎ ይወስዳቸዋል፤ ዐውሎ ነፋስም ይበትናቸዋል፤ በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር ደስ ይልሃል፤ በእኔ በእስራኤል ቅዱስም ትመካለህ።


በእውነትና በቅንነት ‘ሕያው እግዚአብሔርን’ ብላችሁ ብትምሉ ሕዝቦች ይባረካሉ፤ በዚህም ይመካሉ።”


ነገር ግን የእስራኤል ልጆች ሁሉ በእኔ በእግዚአብሔር ድልንና ክብርን ያገኛሉ።


በቅዱስ ስሙ ደስ ይበላችሁ! እግዚአብሔርን የሚፈልግ ሰው ሁሉ ሐሴት ያድርግ!


እግዚአብሔርንም፥ “አዳኝ አምላካችን ሆይ! ከአሕዛብ መካከል መልሰህ ወደ አገራችን አግባን፤ በዚያን ጊዜ እናመሰግን ዘንድ፥ ቅዱስ ስምህንም እናከብር ዘንድ፥ እባክህ ታደገን!” በሉት።


በሙሉ ልቤ በእግዚአብሔር እመካለሁ፤ ትሑቶች ይህን ሰምተው ደስ ይበላቸው!


አብርሃም የጸደቀው በሥራ ቢሆን ኖሮ፥ የሚመካበት ነገር ባገኘ ነበር፤ ይሁን እንጂ በእግዚአብሔር ፊት መመካት አይችልም።


ወንድሞች ሆይ! እናንተን ለመጥቀም ብዬ በዚህ ጉዳይ እኔንና አጵሎስን እንደ ምሳሌ አድርጌ ተናገርኩ፤ ይህንንም ያደረግኹት “ከተጻፈው አትለፍ” የሚለውን ምክር ትርጒሙን ከእኛ እንድትማሩ ብዬ ነው፤ ስለዚህ በአንድ ሰው መመካት ሌላውን ሰው ግን መናቅ አይገባችሁም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios