ርብቃ ይስሐቅን “ዔሳው ባገባቸው በእነዚህ በሒታውያን ሴቶች ምክንያት መኖሬን ጠላሁት፤ ያዕቆብ ደግሞ ከነዚህ ከሒታውያን ሴቶች አንዲቱን ካገባ ከመኖር ይልቅ ሞቴን እመርጣለሁ” አለችው።
ኤርምያስ 4:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምጥ የያዛት ሴት የምታሰማውን ጩኸት የመሰለ ድምፅ ሰማሁ፤ የመጀመሪያ ልጅዋን የምትወልድ በካር ሴት የምታሰማውን ድምፅ የመሰለ ኡኡታም አዳመጥኩ፤ ይህም ድምፅ ኢየሩሳሌም ትንፋሽ አጥሮአት እጅዋን ዘርግታ “ወዮልኝ! ጠፋሁ! እነሆ ሊገድሉኝ መጡ!” እያለች የምታሰማው ጩኸት ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የበኵር ልጇን ለመውለድ እንደምታምጥ፣ በወሊድ እንደምትጨነቅ ሴት ድምፅ ሰማሁ፤ የጽዮን ሴት ልጅ ትንፋሽ ዐጥሯት ስትጮኽ፣ እጇን ዘርግታ፣ “ወዮልኝ! ተዝለፈለፍሁ፣ በነፍሰ ገዳዮች እጅ ወደቅሁ!” ስትል ሰማሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደታመመች የበኩርዋንም እንደምትወልድ ሴት የጭንቀት ድምፅ ሰምቻለሁና፤ የጽዮን ሴት ልጅ ድምፅ በድካም ታቃስታለች፥ እጆችዋንም በመዘርጋት፦ “በነፍሰ ገዳዮች ፊት ነፍሴ ዝላለችና ወዮልኝ!” አለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደምታምጥ፥ የበኵር ልጅዋንም እንደምትወልድ ሴት ጩኸት፥ ጩኸትሽን ሰምቻለሁና፤ የጽዮን ሴት ልጅ ድምፅ በድካም ሰለለ፤ እጆችዋንም ትዘረጋለች፤ ተገድለው ከሞቱት የተነሣ ነፍሴ ዝላለችና ወዮልኝ! አለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደምታምጥ የበኵርዋንም እንደምትወልድ ሴት ድምፅ ሰምቻለሁና፥ የጽዮን ሴት ልጅ ድምፅ በድካም ይሰልላል፥ እጆችዋንም ትዘረጋለችና፦ ተገድለው ከሞቱት የተነሣ ነፍሴ ዝላለችና ወዮልኝ! አለች። |
ርብቃ ይስሐቅን “ዔሳው ባገባቸው በእነዚህ በሒታውያን ሴቶች ምክንያት መኖሬን ጠላሁት፤ ያዕቆብ ደግሞ ከነዚህ ከሒታውያን ሴቶች አንዲቱን ካገባ ከመኖር ይልቅ ሞቴን እመርጣለሁ” አለችው።
“እጆቻችሁን ወደ እኔ ለጸሎት ብትዘረጉ፥ ወደ እናንተ አልመለከትም፤ እጆቻችሁ በደም የተበከሉ ስለ ሆኑ የቱንም ያኽል ልመና ብታበዙ አልሰማችሁም፤
“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለረጅም ጊዜ ታገሥኩ፤ ጸጥ ብዬም ራሴን ገታሁ፤ አሁን ግን ምጥ እንደ ያዛት ሴት ከፍተኛ ድምፅ አሰማለሁ፤ የቊጣ እስትንፋስ እተነፍሳለሁ።
እኔም “እነሆ አንደበቶቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል የምኖር፥ አንደበቴም የረከሰብኝ ሰው ነኝ፤ ንጉሡን የሠራዊት አምላክን በዐይኖቼ አይቼአለሁና መጥፋቴ ስለ ሆነ ወዮልኝ!” አልኩ።
የኢየሩሳሌም ሕዝብ እየጮሁ እንዲህ ይላሉ፥ “በብርቱ ስለ ቈሰልን ወዮልን! ቊስላችንም የማይፈወስ ነው፤ እኛ ግን ይህን ሁሉ መከራ መታገሥ የምንችል መስሎን ነበር።
ወደየመስኩ ብወጣ በጦርነት የተገደሉ ሰዎችን ሬሳ አያለሁ፤ ወደ ከተማም ብገባ በራብ ለመሞት የሚያጣጥሩ ሰዎችን አያለሁ፤ ነቢያትና ካህናት የራሳቸውን ጉዳይ ይከታተላሉ፤ ነገር ግን የሚያደርጉትን አያውቁም።”
አምላክ ሆይ! አሁን ግን ልጆቻቸው በራብ እንዲያልቁ፥ እነርሱም በጦርነት እንዲወድቁ አድርግ፤ ሴቶቻቸው ያለ ባልና ያለ ልጅ ይቅሩ፤ ወንዶቻቸው በበሽታ ወጣቶቻቸውም በጦርነት ይደምሰሱ።
አሁንማ ከሊባኖስ መጥቶ በተሠራ የሊባኖስ እንጨት ውስጥ በሰላም ዐርፋችሁ ትኖራላችሁ፤ ነገር ግን እንደ ወላድ ሴት የምጥ ጣዕር ሲይዛችሁ ምን ይበጃችሁ ይሆን?
እስቲ ቆም ብላችሁ አስቡ! ወንድ አምጦ ልጅን መውለድ ይችላልን? ታዲያ ወንድ ሁሉ እንደ ወላድ ሴት በእጆቹ ወገቡን ይዞ የማየው ስለምንድን ነው? የእያንዳንዱስ ሰው ፊት ስለምን ገረጣ?
ጠላት በቦጽራ ላይ ክንፉን በስፋት ዘርግቶ ወደ ታች እንደሚወርድ ንስር በመሆን ጉብ ይልባታል፤ በዚያን ጊዜ የኤዶም ወታደሮች በምጥ ተይዛ በፍርሃት እንደምትጨነቅ ወላድ ሴት ይሆናሉ።
“ጽዮን እጆችዋን ትዘረጋለች፤ ነገር ግን ማንም የሚያጽናናት የለም፤ ጐረቤቶቹ ሁሉ የያዕቆብ ዘር ጠላቶች እንዲሆኑ እግዚአብሔር አዟል። ኢየሩሳሌምም በመካከላቸው እንደ ርኩስ ነገር ሆናለች።
“እግዚአብሔር ሆይ! ራሴ እንዴት እንደ ተበጠበጠ ተመልከት! በአንተ ላይ ስላመፅሁ ሆዴ ተሸበረ፤ ልቤም ተሰበረ፤ በመንገድም ሆነ በቤት ውስጥ ሕዝቤ እያለቀ ነው።
ወጣቶችና ሽማግሌዎች በተመሳሳይ ሁኔታ ሞተው በየመንገዱ ዳር ወደቁ፤ ወጣቶች ወንዶችና ሴቶች በጠላት ሰይፍ ተጨፈጨፉ፤ በቊጣህ ቀን ያለ ምሕረት እንዲታረዱ አደረግህ።
የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሆይ! ምጥ እንደ ያዛት ሴት እየቃተታችሁ ተንፈራፈሩ፤ ከከተማ ተባራችሁ በሜዳ ላይ ትሰፍራላችሁ ወደ ባቢሎንም ትሄዳላችሁ፤ ይሁን እንጂ በዚያ እግዚአብሔር ያድናችኋል፤ ከጠላቶቻችሁም እጅ ይታደጋችኋል።
እንደዚህ ከፍ አድርገሽ የምትጮኺው፥ ምጥ እንደ ያዛት ሴት የምትጨነቂው ለምንድን ነው? ንጉሥ ስለሌለሽ ነውን? ወይስ አማካሪዎችሽ ሁሉ ስለ ጠፉ ነውን?
የመከር ፍሬ ተሰብስቦ የወይኑም ቃርሚያ ከተቃረመ በኋላ ሊበላ የሚፈልገውን የወይን ዘለላ እንደማያገኝ ሰው ስለ ሆንኩ ወዮልኝ! እኔ የምመኘውም አስቀድሞ የደረሰው የበለስ ፍሬ የለም።
“የጽዮን ከተማ ለምትባለው ለኢየሩሳሌም፦ ‘እነሆ! ንጉሥሽ ትሑት ሆኖ በአህያይቱና በውርንጫዋ ላይ ሆኖ ወደ አንቺ ይመጣል!’ ብላችሁ ንገሩአት።”
ሰዎች “ሁሉ ነገር ሰላምና የተረጋጋ ነው” ሲሉ እርጉዝ ሴትን ምጥ እንደሚይዛት ዐይነት ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል፤ በምንም ዐይነት አያመልጡም።