Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 4:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 እንደታመመች የበኩርዋንም እንደምትወልድ ሴት የጭንቀት ድምፅ ሰምቻለሁና፤ የጽዮን ሴት ልጅ ድምፅ በድካም ታቃስታለች፥ እጆችዋንም በመዘርጋት፦ “በነፍሰ ገዳዮች ፊት ነፍሴ ዝላለችና ወዮልኝ!” አለች።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 የበኵር ልጇን ለመውለድ እንደምታምጥ፣ በወሊድ እንደምትጨነቅ ሴት ድምፅ ሰማሁ፤ የጽዮን ሴት ልጅ ትንፋሽ ዐጥሯት ስትጮኽ፣ እጇን ዘርግታ፣ “ወዮልኝ! ተዝለፈለፍሁ፣ በነፍሰ ገዳዮች እጅ ወደቅሁ!” ስትል ሰማሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ምጥ የያዛት ሴት የምታሰማውን ጩኸት የመሰለ ድምፅ ሰማሁ፤ የመጀመሪያ ልጅዋን የምትወልድ በካር ሴት የምታሰማውን ድምፅ የመሰለ ኡኡታም አዳመጥኩ፤ ይህም ድምፅ ኢየሩሳሌም ትንፋሽ አጥሮአት እጅዋን ዘርግታ “ወዮልኝ! ጠፋሁ! እነሆ ሊገድሉኝ መጡ!” እያለች የምታሰማው ጩኸት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 እን​ደ​ም​ታ​ምጥ፥ የበ​ኵር ልጅ​ዋ​ንም እን​ደ​ም​ት​ወ​ልድ ሴት ጩኸት፥ ጩኸ​ት​ሽን ሰም​ቻ​ለ​ሁና፤ የጽ​ዮን ሴት ልጅ ድምፅ በድ​ካም ሰለለ፤ እጆ​ች​ዋ​ንም ትዘ​ረ​ጋ​ለች፤ ተገ​ድ​ለው ከሞ​ቱት የተ​ነሣ ነፍሴ ዝላ​ለ​ችና ወዮ​ልኝ! አለች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 እንደምታምጥ የበኵርዋንም እንደምትወልድ ሴት ድምፅ ሰምቻለሁና፥ የጽዮን ሴት ልጅ ድምፅ በድካም ይሰልላል፥ እጆችዋንም ትዘረጋለችና፦ ተገድለው ከሞቱት የተነሣ ነፍሴ ዝላለችና ወዮልኝ! አለች።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 4:31
35 Referencias Cruzadas  

ርብቃም ይስሐቅን አለችው፦ “ከኬጢ ሴቶች ልጆች የተነሣ ሕይወቴን ጠላሁት፥ ያዕቆብ ከዚህ አገር ሴቶች ልጆች ሚስትን የሚያገባ ከሆነ በሕይወት መኖር ለምኔ ነው?”


“ሕይወቴ ሰለቸኝ፥ የኀዘን እንጉርጉሮዬን እለቅቀዋለሁ፥ በነፍሴም ምሬት እናገራለሁ።


መኖሪያዬ የራቀ እኔ ወዮልኝ፥ በቄዳር ድንኳኖች አደርሁ።


እጆቻቸሁን ለጸሎት ወደ እኔ ስትዘረጉ፤ ዐይኖቼን ከእናንተ እሰውራለሁ፤ አብዝታችሁ ብትጸልዩም እንኳ አልሰማችሁም፤ እጆቻችሁ በደም ተበክለዋል፤


ሽብር ይይዛቸዋል፤ ሥቃይና ጭንቀት ይደርስባቸዋል፤ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ያምጣሉ፤ እርስ በርሳቸው በድንጋጤ ይተያያሉ፤ ፊታቸውም በፍርሀት ቀይ ይሆናል።


ስለዚህ ወገቤ ሕመም ተሞላ፤ ምጥ እንደ ያዛት ሴት አስጨነቀኝ፤ ከሕመሜ የተነሣ አልሰማም፥ ከድንጋጤም የተነሣ አላይም።


የፀነሰች ሴት ለመውለድ ስትቀርብ እንደምትጨነቅና በምጥ አንደምትጮኽ፥ አቤቱ ጌታ፥ በፊትህ እንዲሁ ሆነናል።


ከድሮ ዘመን ጀምሮ ዝም ብያለሁ፥ ዝም ብዬም ታግሻለሁ፤ አሁን ምጥ እንደ ያዛት ሴት እጮኻለሁ፤ አጠፋለሁ በአንድነትም እጨርሳለሁ።


እኔም፤ “ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው ነኝ፤ የምኖረውም ከንፈሮቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል ነው፤ ዐይኖቼም ንጉሡን፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አይቷልና ጠፍቻለሁ፤ ወዮልኝ!” አልሁ።


ስለ ስብራቴ ወዮልኝ! ቁስሌም የማይሽር ነው፥ እኔ ግን፦ “በእውነት የመከራ ቁስሌ ነው እርሱንም መሸከም ይገባኛል” አልሁ።


ወዳጆችሽ እንዲሆኑ ያስተማርሻቸውን በራስሽ ላይ አለቆች ባደረጋቸው ጊዜ ምን ትያለሽ? እንደ ወላድ ሴት ምጥ አይዝሽምን?


ወደ ሜዳ ብወጣ፥ እነሆ፥ በሰይፍ የሞቱ አሉ፤ ወደ ከተማም ብገባ፥ እነሆ፥ በራብ ደዌ የከሱ አሉ፤ ነቢዩና ካህኑም ወደማያውቁት አገር ሄደዋልና።’”


ለምን ሕመሜ የማያቋርጥ ሆነ? ቁስሌስ የማይፈወስ ለምን ሆነ? ለምንስ፦ አልሽርም አለ? በውኑ እንደ ሐሰተኛ ምንጭ፥ እንዳልታመነች ውኃ ትሆንብኛለህን?


ስለዚህ ልጆቻቸውን ለራብ ስጥ፥ ለሰይፍም እጅ አሳልፈህ ስጣቸው፥ ሚስቶቻቸውም የወላድ መካንና መበለቶች ይሁኑ፥ ወንዶቻቸውም በሞት ይጥፉ፥ ጉልማሶቻቸውም በጦርነት ጊዜ በሰይፍ ይመቱ።


አንቺ በሊባኖስ የምትቀመጪ፥ በዝግባ ዛፍም ውስጥ ጎጆሽን የምትሠሪ ሆይ! ምጥ እንደ ያዛት ሴት ሕመም በያዘሽ ጊዜ እንዴት ታቃስቻለሽ!”


ጠይቁ፥ ወንድ ይወልድ እንደሆነ ተመልከቱ፤ ስለምን ሰው ሁሉ እንደ ወላድ ሴት እጁን በወገቡ ላይ አድርጎ ፊቱም ሁሉ ገርጥቶ አየሁ?


“ባሮክ ሆይ! የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይልሃል፦


ከተሞቹ ተይዘዋል፥ አምባዎቹም ተወስደዋል፥ በዚያም ቀን የሞዓብ ኃያላን ልብ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ልብ ሆኖአል።


እነሆ፥ እንደ ንስር ወጥቶ ይበራል ክንፉንም በባሶራ ላይ ይዘረጋል፥ በዚያም ቀን የኤዶምያስ ኃያላን ልብ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ልብ ይሆናል።”


ደማስቆ ደከመች ለመሸሽም ዘወር አለች መንቀጥቀጥም ያዛት፥ እንደ ወላድም ሴት ጣርና ምጥ ያዛት።


የባቢሎን ንጉሥ ወሬአቸውን ሰምቶአል፥ እጆቹም ደክመዋል፥ ጣርም ይዞታል፥ ምጥ ወላድ ሴትን እንደሚይዛት ጭንቀት ይዞታል።


የተዋበችውንና የተቀማጠለችውን የጽዮንን ልጅ አጐሳቁላለሁ።


ፌ። ጽዮን እጅዋን ዘረጋች የሚያጽናናት የለም፥ እግዚአብሔር በያዕቆብ ዙሪያ ያሉትን እንዲያስጨንቁት አዘዘ፥ ኢየሩሳሌም በመካከላቸው እንደ ርኩስ ነገር ሆናለች።


ሬስ። አቤቱ፥ ተጨንቄአለሁና፥ አንጀቴም ታውኮብኛልና ተመልከት፥ ዓመፃን ፈጽሞ አድርጌአለሁና ልቤ በውስጤ ተገላበጠብኝ፥ በሜዳ ሰይፍ ልጆቼን አጠፋ በቤትም ሞት አለ።


ሳን። ብላቴናውና ሽማግሌው በመንገዶች ላይ ተጋደሙ፥ ደናግሎቼና ጐበዛዝቴ በሰይፍ ወድቀዋል፥ በቁጣህ ቀን ገደልሃቸው፥ ሳትራራ አረድሃቸው።


ምጥ እንደ ያዛት ሴት ጭንቅ ይመጣበታል፤ በሚወለድበት ጊዜ ወደ ማኅፀን አፍ ራሱን አያቀርብምና ማስተዋል የጎደለው ልጅ ነው።


የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እንደምትወልድ ሴት አምጪ፥ ተጨነቂ፤ አሁን ከከተማ ወጥተሽ በሜዳ ትቀመጫለሽና፥ ወደ ባቢሎንም ትሄጃለሽ፤ በዚያ ትድኛለሽ፥ በዚያም ጌታ ከጠላቶችሽ እጅ ይቤዥሻል።


አሁንስ ለምን ጮክ ብልሽ ታለቅሻለሽ? በአንቺ ዘንድ ንጉሥ ስለ ሌለ ነውን? እንደምትወልድ ሴት ምጥ የያዘሽ፥ መካሪሽ ስለ ጠፋ ነውን?


የዛፍ ፍሬና የወይን ፍሬ ከተለቀሙ በኋላ እንደ ቀረው ቃርሚያ ሆኛለሁና ወዮልኝ! መብል የሚሆን ዘለላ፥ ነፍሴም የተመኘችው በመጀመሪያ የበሰለው በለስ የለም።


“ለጽዮን ልጅ “እነሆ፥ ንጉሥሽ የዋህ ሆኖ በአህያ ላይና በአህያይቱ ግልገል በውርንጫ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል፥ በሉአት።”


ወንጌልን ብሰብክ እንኳ ግዴታዬ ነውና የምመካበት የለኝም፤ ወንጌልን ባልሰብክ ወዮልኝ!


እነርሱም፦ “ሰላምና ደኅንነት ነው” በሚሉ ጊዜ ምጥ እንደ ያዛት እርጉዝ ሴት ድንገተኛ ጥፋት በእነርሱ ላይ ይመጣባቸዋል፤ ከቶም አያመልጡም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos