Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 50:43 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

43 የባቢሎን ንጉሥ ይህን ወሬ ሲሰማ እጁ ሽባ ሆኖ ተንጠልጥሎ ይቀራል፤ በምጥ እንደ ተያዘች ሴት ይጨነቃል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

43 የባቢሎን ንጉሥ ስለ እነርሱ ሰማ፤ እጆቹም በድን ሆኑ፤ ጭንቀት ይዞታል፤ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ታምሟል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

43 የባቢሎን ንጉሥ ወሬአቸውን ሰምቶአል፥ እጆቹም ደክመዋል፥ ጣርም ይዞታል፥ ምጥ ወላድ ሴትን እንደሚይዛት ጭንቀት ይዞታል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

43 የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ውካ​ታ​ቸ​ውን ሰም​ቶ​አል፤ እጁም ደክ​ማ​ለች፤ ምጥ ወላድ ሴትን እን​ደ​ሚ​ይ​ዛ​ትም ጭን​ቀት ይዞ​ታል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

43 የባቢሎን ንጉሥ ወሬአቸውን ሰምቶአል፥ እጁም ደክማለች፥ ጭንቀትም ይዞታል፥ ምጥ ወላድ ሴትን እንደሚይዛት ጭንቀት ይዞታል።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 50:43
8 Referencias Cruzadas  

እስቲ ቆም ብላችሁ አስቡ! ወንድ አምጦ ልጅን መውለድ ይችላልን? ታዲያ ወንድ ሁሉ እንደ ወላድ ሴት በእጆቹ ወገቡን ይዞ የማየው ስለምንድን ነው? የእያንዳንዱስ ሰው ፊት ስለምን ገረጣ?


ጠላት በቦጽራ ላይ ክንፉን በስፋት ዘርግቶ ወደ ታች እንደሚወርድ ንስር በመሆን ጉብ ይልባታል፤ በዚያን ጊዜ የኤዶም ወታደሮች በምጥ ተይዛ በፍርሃት እንደምትጨነቅ ወላድ ሴት ይሆናሉ።


የደማስቆ ሕዝብ ተዳከሙ፤ ለመሸሽ ወደ ኋላ ተመለሱ ፍርሀትም ያዛቸው፤ የምጥ ጣር እንደ ያዛትም ሴት ተጨነቁ።


የእርሱ ከተማ ከዳር እስከ ዳር የተያዘች መሆንዋን ለባቢሎን ንጉሥ ለመንገር አንዱ ሩዋጭ ለሌላው ሩዋጭ፥ አንዱ መልእክተኛ ለሌላው መልእክተኛ መልእክቱን ለማስተላለፍ ይሯሯጣሉ።


የኢየሩሳሌም ሕዝብ እንዲህ ይላሉ፦ “ወሬውን ስለ ሰማን ክንዳችን ዛለ፤ በምጥ እንደ ተያዘች ሴትም ጭንቀትና ሕመም ተሰምቶናል፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos