Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


ኤርምያስ 45 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም


እግዚአብሔር ለባሮክ የሰጠው ተስፋ

1 የኢዮስያስ ልጅ ኢዮአቄም በይሁዳ በነገሠ በአራተኛው ዓመት ባሮክ በቃል የነገርኩትን ሁሉ በብራና ጥቅል ጻፈው፤

2 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ስለ ባሮክ የተናገረውን እንዲህ ብዬ ነገርኩት፦

3 እግዚአብሔር በሕመሜ ላይ ሐዘን ጨምሮብኝ ምንም ዕረፍት ሳይኖረኝ በመቃተት ደክሜአለሁና ወዮልኝ!

4 “ነገር ግን እኔ እግዚአብሔር የገነባሁትን አፈርሳለሁ፤ የተከልኩትንም እነቅላለሁ፤ ይህንንም በምድር ሁሉ ላይ አደርጋለሁ፤

5 ታዲያ አንተ ለራስህ የተለየ መልካም ነገር እንዳደርግልህ ትፈልጋለህን? ይህን መፈለግ የለብህም፤ እኔ መቅሠፍትን በሰው ዘር ሁሉ ላይ አመጣለሁ፤ ይሁን እንጂ በምትሄድበት ቦታ ሁሉ ሌላው ቢቀር ሕይወትህ እንድትተርፍ አደርጋለሁ። እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia
Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos