ከመጀመሪያውም ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻው ቀን ድረስ ዕለት ዕለት የእግዚአብሔርን ሕግ መጽሐፍ ያነብብ ነበር። በዓሉንም ሰባት ቀን ያህል አደረጉ፤ በስምንተኛውም ቀን እንደ ሕጋቸው ወጡ።
ዮሐንስ 7:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኋለኛዪቱ በታላቅዋ የበዓል ቀንም ጌታችን ኢየሱስ ቆመና ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፥ “የተጠማ ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የበዓሉ መጨረሻ በሆነው በታላቁ ቀን፣ ኢየሱስ ቆሞ ከፍ ባለ ድምፅ እንዲህ አለ፤ “ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከበዓሉም በታላቁ በኋለኛው ቀን ኢየሱስ ቆሞ እንዲህ ሲል ጮኸ፤ “ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የበዓሉ መጨረሻ በሆነው በታላቁ ቀን ኢየሱስ ቆመና ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፦ “ውሃ የጠማው ቢኖር ወደ እኔ መጥቶ ይጠጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከበዓሉም በታላቁ በኋለኛው ቀን ኢየሱስ ቆሞ፦ “ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይመጣና ይጠጣ። |
ከመጀመሪያውም ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻው ቀን ድረስ ዕለት ዕለት የእግዚአብሔርን ሕግ መጽሐፍ ያነብብ ነበር። በዓሉንም ሰባት ቀን ያህል አደረጉ፤ በስምንተኛውም ቀን እንደ ሕጋቸው ወጡ።
እኅቴ ሙሽሪት ሆይ፥ ወደ ገነቴ ገባሁ፥ ከርቤዬን ከሽቱዬ ጋር ለቀምሁ፥ እንጀራዬን ከማሬ ጋር በላሁ፥ የወይን ጠጄን ከወተቴ ጋር ጠጣሁ። ባልንጀሮች በሉ፥ ጠገቡም፤ የወንድሞች ልጆች ጠጡ፥ ሰከሩም፥ ልባቸው የጠፋ ነውና።
ካህናት ሆይ፥ ለኢየሩሳሌም ወደ ልቧ የሚገባ ነገርን ተናገሩ፤ ውርደቷ እንደ ተፈጸመ፥ ኀጢአቷም እንደ ተሰረየ፥ ከእግዚአብሔርም እጅ ስለ ኀጢአቷ ሁሉ ሁለት እጥፍ እንደ ተቀበለች አጽናኑአት።
በደረቅ መሬት ላይ ለሚሄድና ለተጠማ ውኃን እሰጣለሁ፤ መንፈሴን በዘርህ ላይ፥ በረከቴንም በልጆችህ ላይ አኖራለሁ፤
እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ፥ ወደ ውኃ ሂዱ፤ ገንዘብም የሌላችሁ ሂዱና ግዙ፤ ብሉ፤ ያለ ገንዘብም ያለ ዋጋም የወይን ጠጅና ወተት ጠጡ።
ስሙኝ፤ ጎዳናዬን ተከተሉ፤ አድምጡኝም፤ ሰውነታችሁም በበረከት ትኖራለች፤ የታመነችዪቱን የዳዊትን ምሕረት፥ የዘለዓለምን ቃል ኪዳን ከእናንተ ጋር አደርጋለሁ።
በኀይልህ ጩኽ፤ አትቈጥብ፤ ድምፅህን እንደ መለከት አንሣ፤ ለሕዝቤ ኀጢአታቸውን፥ ለያዕቆብ ቤትም በደላቸውን ንገር።
ጌታ ሆይ! አንተ ኀይሌና ረዳቴ፥ በመከራም ቀን መጠጊያዬ ነህ፤ ከምድር ዳርቻ አሕዛብ ወደ አንተ መጥተው፥ “በእውነት አባቶቻችን ውሸትንና ከንቱን ነገር ለምንም የማይረባቸውን ጣዖትን ሠርተዋል” ይላሉ።
“ሂድ፤ እንዲህ ብለህ በኢየሩሳሌም ጆሮ ተናገር፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የብላቴንነትሽን ምሕረት፥ የታጨሽበትንም ፍቅር፥ በምድረ በዳ ዘር ባልተዘራበት ምድር እንደ ተከተልሽኝ አስቤአለሁ።
ሕያው ነፍስ ያለው ተንቀሳቃሽ ሁሉ ወንዙ በሚገባበት ስፍራ ሁሉ በሕይወት ይኖራል፤ ይህም ውኃ በዚያ ስለ ደረሰ ዓሣዎች እጅግ ይበዛሉ፤ የባሕሩም ውኃ ይፈወሳል፤ ወንዙም በሚመጣበት ያለው ሁሉ በሕይወት ይኖራል።
ሰባት ቀን ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት አቅርቡ፤ ስምንተኛዋም ቀን የተቀደሰች ጉባኤ ትሁንላችሁ፤ ለእግዚአብሔርም የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቅርቡ፤ የመሰናበቻ በዓል ነውና፤ የተግባር ሥራ ሁሉ አትሥሩበት።
ከሰባተኛውም ወር በዐሥራ አምስተኛው ቀን የምድሩን ፍሬ ካከማቻችሁ በኋላ፥ የእግዚአብሔርን በዓል ሰባት ቀን ታደርጋላችሁ፤ የመጀመሪያዋ ቀን ዕረፍት ትሁን፤ ስምንተኛዋም ቀን ዕረፍት ትሁን።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይጠብቃቸዋል፣ እነርሱም ይበሉአቸዋል፥ የወንጭፉንም ድንጋዮች ይረግጣሉ፣ እንደ ወይን ጠጅም ይጠጡአቸዋል፥ እንደ ጥዋዎችም እንደ መሠዊያም ማዕዘኖች የተሞሉ ይሆናሉ።
እርሱም፥ “ነቢዩ ኢሳይያስ እንደ ተናገረ የእግዚአብሔርን መንገድ ጥረጉ እያለ በምድረ በዳ የሚሰብክ የዐዋጅ ነጋሪ ድምፅ እኔ ነኝ” አለ።
ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አለው፥ “የእውነትና የሕይወት መንገድ እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።
ጌታችን ኢየሱስም፥ “የእግዚአብሔርን ስጦታና ውኃ አጠጪኝ ብሎ የሚለምንሽ ማን እንደ ሆነ ብታውቂስ አንቺ ደግሞ በለመንሺው ነበር፤ እርሱም የሕይወትን ውኃ በሰጠሽ ነበር” ብሎ መለሰላት።
ያቺ ሴትም እንዲህ አለችው፥ “ጌታዬ መቅጃ እንኳ የለህም፤ ጕድጓዱም ጥልቅ ነው፤ እንግዲህ የሕይወት ውኃ ከወዴት ታገኛለህ?
እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ግን ለዘለዓለም አይጠማም፤ እኔ የምሰጠው ውኃ በውስጡ ለዘለዓለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆንለታል እንጂ።”
ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ “የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም፤ በእኔ የሚያምንም ለዘለዓለም አይጠማም።
ጌታችን ኢየሱስም በመቅደስ ሲያስተምር ቃሉን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፥ “እኔን ታውቁኛላችሁ፤ ከወዴትም እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ፤ እኔ ራሴ የመጣሁ አይደለሁም፤ ነገር ግን እናንተ የማታውቁት የላከኝ እውነተኛ አለ።
የእግዚአብሔርን ጽዋና የአጋንንትን ጽዋ አንድ አድርጋችሁ መጠጣት አትችሉም፤ የእግዚአብሔርን ማዕድና የአጋንንትንም ማዕድ በአንድነት ልትበሉ አትችሉም።
ሁሉም ያን መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ፤ ይኸውም በኋላቸው ከሚሄደው ከመንፈሳዊ ዐለት የጠጡት ነው፤ ያም ዐለት ክርስቶስ ነበረ።
እንዲሁም ኅብስቱን ከተቀበሉ በኋላ ጽዋውን አንሥቶ፥ “አዲስ ሥርዐት የሚጸናበት ይህ ጽዋ ደሜ ነው እንዲህ አድርጉ፤ በምትጠጡበትም ጊዜ አስቡኝ” አላቸው።
እኛ ሁላችንም በአንድ መንፈስ አንድ አካል ለመሆን ተጠምቀናል፤ አይሁድ ብንሆን፥ አረማውያንም ብንሆን፥ ባሪያዎችም ብንሆን፥ ነጻዎችም ብንሆን ሁላችን አንድ መንፈስ ጠጥተናልና።