Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዮሐንስ 7:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

38 በእ​ኔም የሚ​ያ​ምን መጽ​ሐፍ እንደ ተና​ገረ የሕ​ይ​ወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈ​ስ​ሳል።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

38 በእኔ የሚያምን፣ መጽሐፍ እንዳለ የሕይወት ውሃ ምንጭ ከውስጡ ይፈልቃል።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

38 በእኔ የሚያምን፥ መጽሐፍ እንዳለው፥ የሕይወት ውሃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

38 በእኔ የሚያምን ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚለው፥ የሕይወት ውሃ ምንጭ ከውስጡ ይፈልቃል።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

38 በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ፥ የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል” ብሎ ጮኸ።

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 7:38
16 Referencias Cruzadas  

እኔ ከም​ሰ​ጠው ውኃ የሚ​ጠጣ ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ጠ​ማም፤ እኔ የም​ሰ​ጠው ውኃ በው​ስጡ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት የሚ​ፈ​ልቅ የውኃ ምንጭ ይሆ​ን​ለ​ታል እንጂ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሁል​ጊዜ ከአ​ንተ ጋር ይኖ​ራል፤ እንደ ነፍ​ስ​ህም ፍላ​ጎት ያጠ​ግ​ብ​ሃል፤ አጥ​ን​ት​ህ​ንም ያለ​መ​ል​ማል፤ አን​ተም እን​ደ​ሚ​ጠጣ ገነት፥ ውኃ​ውም እን​ደ​ማ​ያ​ቋ​ርጥ ምንጭ ትሆ​ና​ለህ።


በደ​ረቅ መሬት ላይ ለሚ​ሄ​ድና ለተ​ጠማ ውኃን እሰ​ጣ​ለሁ፤ መን​ፈ​ሴን በዘ​ርህ ላይ፥ በረ​ከ​ቴ​ንም በል​ጆ​ችህ ላይ አኖ​ራ​ለሁ፤


ውኃ​ው​ንም ከሕ​ይ​ወት ምን​ጮች በደ​ስታ ትቀ​ዳ​ላ​ችሁ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስጦ​ታና ውኃ አጠ​ጪኝ ብሎ የሚ​ለ​ም​ንሽ ማን እንደ ሆነ ብታ​ው​ቂስ አንቺ ደግሞ በለ​መ​ን​ሺው ነበር፤ እር​ሱም የሕ​ይ​ወ​ትን ውኃ በሰ​ጠሽ ነበር” ብሎ መለ​ሰ​ላት።


የሕይወት ምንጭ በጻድቃን አፍ ነው፥ የኃጥኣንን አፍ ግን ጥፋት ይከድነዋል።


በዚያም ቀን የሕይወት ውኃ ከኢየሩሳሌም ይወጣል፣ እኵሌታው ወደ ምሥራቁ ባሕር፥ እኵሌታውም ወደ ምዕራቡ ባሕር ይሄዳል፣ ይህ በበጋና በክረምት ይሆናል።


ቃል በብልህ ሰው ልብ ውስጥ የጠለቀ ውኃ ነው፥ የሚፈልቅም የሕይወት ምንጭና ፈሳሽ ወንዝ ነው።


“ከእ​ነ​ርሱ ጋር ያለው ቃል ኪዳኔ ይህ ነው” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ “በአ​ንተ ላይ ያለው መን​ፈሴ በአ​ፍ​ህም ውስጥ ያደ​ረ​ግ​ሁት ቃሌ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለ​ዓ​ለም ድረስ ከአ​ፍህ፥ ከዘ​ር​ህም አፍ፥ ከዘር ዘር​ህም አፍ አይ​ጠ​ፋም፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከወ​ን​ድ​ሞ​ችህ እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስ​ነ​ሣ​ል​ሃል፤ እር​ሱ​ንም ስሙት።


የብ​ር​ሃን ፍሬው በጎ ሥራና እው​ነት፥ ቅን​ነ​ትም ሁሉ ነውና።


በዚ​ያን ጊዜ አን​ካ​ሳ​ዎች እንደ ሚዳቋ ይዘ​ል​ላሉ፤ የዲ​ዳ​ዎ​ችም ምላስ ርቱዕ ይሆ​ናል፤ በም​ድረ በዳ ውኃ፥ በተ​ጠማ መሬ​ትም ፈሳሽ ይፈ​ል​ቃ​ልና።


እና​ንተ የተ​ጠ​ማ​ችሁ ሁሉ፥ ወደ ውኃ ሂዱ፤ ገን​ዘ​ብም የሌ​ላ​ችሁ ሂዱና ግዙ፤ ብሉ፤ ያለ ገን​ዘ​ብም ያለ ዋጋም የወ​ይን ጠጅና ወተት ጠጡ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios