Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ቆሮንቶስ 11:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 እን​ዲ​ሁም ኅብ​ስ​ቱን ከተ​ቀ​በሉ በኋላ ጽዋ​ውን አን​ሥቶ፥ “አዲስ ሥር​ዐት የሚ​ጸ​ና​በት ይህ ጽዋ ደሜ ነው እን​ዲህ አድ​ርጉ፤ በም​ት​ጠ​ጡ​በ​ትም ጊዜ አስ​ቡኝ” አላ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 እንዲሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን አንሥቶ፣ “ይህ ጽዋ በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው፤ ስለዚህ ከጽዋው በምትጠጡበት ጊዜ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት” አለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 እንዲሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን አንሥቶ “ይህ ጽዋ በደሜ የሚመሰረት አዲስ ኪዳን ነው፤ በምትጠጡበት ጊዜ ሁሉ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት፤” አለ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 እንዲሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን አንሥቶ “ይህ ጽዋ በደሜ የሚመሠረት አዲስ ኪዳን ነው፤ በምትጠጡበት ጊዜ ሁሉ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት” አለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 እንደዚሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን ደግሞ አንሥቶ፦ ይህ ጽዋ በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው፤ በጠጣችሁት ጊዜ ሁሉ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት አለ።

Ver Capítulo Copiar




1 ቆሮንቶስ 11:25
11 Referencias Cruzadas  

እን​ዲ​ሁም ከእ​ራት በኋላ ጽዋ​ዉን አን​ሥቶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ይህ ጽዋ ስለ እና​ንተ በሚ​ፈ​ስ​ሰው ደሜ የሚ​ሆን አዲስ ኪዳን ነው።


በዘ​ለ​ዓ​ለም ኪዳን ደም ለበ​ጎች ትልቅ እረኛ የሆ​ነ​ውን ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ከሙ​ታን ያስ​ነ​ሣው፥


በመ​ን​ፈስ እንጂ በፊ​ደል ለማ​ይ​ሆን ለአ​ዲስ ሕግ አገ​ል​ጋ​ዮች አደ​ረ​ገን፤ ፊደል ይገ​ድ​ላል፥ መን​ፈስ ግን ሕያው ያደ​ር​ጋል።


ይህ የም​ን​ባ​ር​ከው የበ​ረ​ከት ጽዋ ከክ​ር​ስ​ቶስ ደም ጋር አንድ አይ​ደ​ለ​ምን? የም​ን​ፈ​ት​ተው ይህስ ኅብ​ስት ከክ​ር​ስ​ቶስ ሥጋ ጋር አንድ አይ​ደ​ለ​ምን?


ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ ልባ​ቸው ተሸ​ፍ​ኖ​አል፤ ያም መጋ​ረጃ ብሉይ ኪዳን በተ​ነ​በ​በት ዘመን ሁሉ ጸንቶ ኖሮ​አል፤ ክር​ስ​ቶስ እስ​ኪ​ያ​ሳ​ል​ፈው ድረስ አል​ተ​ገ​ለ​ጠ​ምና።


ሙሴም የደ​ሙን እኵ​ሌታ ወስዶ በቆሬ ውስጥ አደ​ረ​ገው፤ የደ​ሙ​ንም እኵ​ሌታ በመ​ሠ​ዊ​ያው ረጨው።


ሙሴም ደሙን ወስዶ በሕ​ዝቡ ላይ ረጨው፤ በዚህ ቃል ሁሉ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ና​ንተ ጋር ያደ​ረ​ገው የቃል ኪዳኑ ደም እነሆ” አለ።


“እነሆ ከእ​ስ​ራ​ኤል ቤትና ከይ​ሁዳ ቤት ጋር አዲስ ቃል ኪዳን የም​ገ​ባ​በት ወራት ይመ​ጣል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤


አመ​ሰ​ገነ፤ ባረከ፤ ፈተተ፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “እንኩ ብሉ፤ ስለ እና​ንተ የሚ​ሰ​ጠው ሥጋዬ ይህ ነው፤ መታ​ሰ​ቢ​ያ​ዬ​ንም እን​ዲሁ አድ​ርጉ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios