መዝሙር 42 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)የዳዊት መዝሙር። 1 አቤቱ፥ ፍረድልኝ፥ ከጽድቅ ከወጡ ሕዝብም በቀሌን ተበቀል። ከዐመፀኛና ከሸንጋይ ሰው አድነኝ። 2 አንተ አምላኬ፥ ኀይሌም ነህና፥ ለምን ትተወኛለህ? ጠላቶቼ ቢያስጨንቁኝ ለምን አዝኜ እመለሳለሁ? 3 ብርሃንህንና ጽድቅህን ላክ፤ እነርሱም ይምሩኝ፥ አቤቱ ወደ መቅደስህ ተራራና ወደ ማደሪያህ ይውሰዱኝ። 4 ወደ እግዚአብሔር መሠዊያ፥ ጐልማስነቴንም ደስ ወዳሰኛት ወደ አምላኬ እገባለሁ፤ አቤቱ፥ አምላኬ፥ በመሰንቆ አመሰግንሃለሁ። 5 ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ ታውኪኛለሽ? የፊቴን መድኀኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ በእግዚአብሔር ታመኚ። |