እግዚአብሔርም የከለዳውያንን አደጋ ጣዮች፥ የሶርያውያንንም አደጋ ጣዮች፥ የሞዓባውያንንም አደጋ ጣዮች፥ የአሞንንም ልጆች አደጋ ጣዮች ሰደደበት፤ በባሪያዎቹ በነቢያት ቃል እንደ ተናገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል ያጠፉት ዘንድ በይሁዳ ላይ ሰደዳቸው።
ኤርምያስ 25:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ ልኬ የሰሜንን ወገኖች ሁሉ፤ ባሪያዬንም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እወስዳለሁ፤ በዚችም ምድርና በሚቀመጡባትም ሰዎች ላይ፥ በዙሪያዋም ባሉ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ፤ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፤ ለጥፋትና ለፉጨት ለዘለዓለምም ዕፍረት ባድማ አደርጋቸዋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰሜንን ሕዝብ ሁሉ፣ አገልጋዬንም የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እጠራለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “በዚህች ምድርና በነዋሪዎቿም ላይ፣ በአካባቢዋም ባሉ ሕዝቦች ሁሉ ላይ አመጣባቸዋለሁ፤ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፤ ሰዎች የሚጸየፏቸውና የሚሣለቁባቸው፣ የዘላለምም ባድማ አደርጋቸዋለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ የሰሜንን ወገኖች ሁሉ እልካለሁ ይላል ጌታ፥ ባርያዬንም የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እወስዳለሁ፥ በዚህችም ምድር በሚቀመጡባትም ሰዎች፥ በዙሪያዋም ባሉ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ፤ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፥ ለመሣቀቂያና ለማፍዋጫም ለዘለዓለምም ባድማ አደርጋቸዋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘እነሆ በስተሰሜን ወዳሉት ነገዶችና አገልጋዬ ወደ ሆነው ወደ ባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር መልእክተኛ እልካለሁ፤ ይሁዳንና በውስጥዋ የሚኖሩትን፥ እንዲሁም በጐረቤት ያሉትን ሕዝቦች ይወጉ ዘንድ አመጣቸዋለሁ፤ ይህችን አገር ከነጐረቤቶችዋ አጠፋለሁ፤ ለማየት የሚያስፈሩና መሳለቂያ እስኪሆኑ ድረስ ለዘለዓለም ፍርስራሽ ሆነው እንዲቀሩ አደርጋቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልኬ የሰሜንን ወገኖች ሁሉ ባሪያዬንም የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እወስዳለሁ፥ በዚህችም ምድር በሚቀመጡባትም ሰዎች በዙሪያዋም ባሉ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ፥ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፥ ለመደነቂያና ለማፍዋጫም ለዘላለምም ባድማ አደርጋቸዋለሁ። |
እግዚአብሔርም የከለዳውያንን አደጋ ጣዮች፥ የሶርያውያንንም አደጋ ጣዮች፥ የሞዓባውያንንም አደጋ ጣዮች፥ የአሞንንም ልጆች አደጋ ጣዮች ሰደደበት፤ በባሪያዎቹ በነቢያት ቃል እንደ ተናገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል ያጠፉት ዘንድ በይሁዳ ላይ ሰደዳቸው።
“ስለዚህም የእግዚአብሔር ቍጣ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ሆነ፤ በዐይናችሁም እንደምታዩ ለድንጋጤና ለመደነቂያ፥ ለመዘበቻም አሳልፎ ሰጣቸው።
በኤርምያስ አፍ የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል እንዲፈጸም፥ ምድሪቱ ሰንበትን በማድረግዋ እስክታርፍ ድረስ፥ በተፈታችበትም ዘመን ሁሉ፥ ሰባ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ፥ ሰንበትን አገኘች።
እኔ አዝዤ ቅዱሳኔን አመጣቸዋለሁ፤ ኀያላኔንም አመጣቸዋለሁ፤ ደስ እያላቸውም ይመጣሉ፤ ቍጣዬንም ይፈጽማሉ፤ ያዋርዱአቸዋልም።
ከአንተ ከሚወጡት ከምትወልዳቸው ልጆችህ ማርከው ይወስዳሉ፤ በባቢሎንም ንጉሥ ቤት ውስጥ ጃንደረቦችና የቤት አሽከሮች ይሆናሉ” አለው።
ቂሮስንም፥ “ብልህ ሁን፤ እርሱም ኢየሩሳሌምን፦ ትታነጺያለሽ ቤተ መቅደስንም እመሠርታለሁ ብሎ ፈቃዴን ሁሉ ይፈጽማል” ይላል።
እነሆ እኔ በሰሜን ያሉትን የመንግሥታቱን ወገኖች ሁሉ እጠራለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ እነርሱም ይመጣሉ እያንዳንዳቸውም በኢየሩሳሌም በር መግቢያ በዙሪያዋና በቅጥርዋ ሁሉ ላይ፥ በይሁዳም ከተሞች ሁሉ ላይ ዙፋናቸውን ያስቀምጣሉ።
የወሬ ድምፅ ተሰማ፤ እነሆም የይሁዳን ከተሞች ባድማና የሰገኖ ማደሪያ ያደርጋቸው ዘንድ ከሰሜን ምድር ታላቅ መነዋወጥ መጥቶአል።
እግዚአብሔር ለሕዝቤ ለእስራኤል ያወረስሁትን ርስት ለሚነኩት ክፉዎች ጎረቤቶች ሁሉ እንዲህ ይላልና፥ “እነሆ ከምድራቸው እነቅላቸዋለሁ፤ የይሁዳንም ቤት ከመካከላቸው እነቅለዋለሁ።
የአንበሳ ደቦሎች በእርሱ ላይ አገሡ፤ በእርሱም ላይ ደነፉ፤ ምድሩንም ባድማ አደረጉ፤ ከተሞቹንም አፈረሱ፤ የሚቀመጥባቸውም የለም።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ እነሆ አንተን ከወዳጆችህ ሁሉ ጋር አፈልስሃለሁ፤ እነርሱም በጠላቶቻቸው ሰይፍ ይወድቃሉ፤ ዐይኖችህም ያያሉ፤ አንተንና ይሁዳንም ሁሉ በባቢሎን ንጉሥ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እርሱም ወደ ባቢሎን ያፈልሳቸዋል፤ በሰይፍም ይገድላቸዋል።
በማሳድዳቸውም ስፍራ ሁሉ ለስድብና ለምሳሌ፥ ለጥላቻና ለርግማን ይሆኑ ዘንድ በምድር መንግሥታት ሁሉ እንዲበተኑ አደርጋለሁ።
በሰይፍና በራብ፥ በቸነፈርም አሳድዳቸዋለሁ፤ ባሳደድሁባቸውም አሕዛብ ሁሉ ዘንድ ለርግማንና ለጥፋት፥ ለማፍዋጫም፥ ለመሰደቢያም እንዲሆኑ በምድር መንግሥታት ሁሉ ዘንድ ለመበተን አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።
ነገር ግን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በዚች ምድር ላይ በዘመተ ጊዜ፦ ኑ ከከለዳውያን ሠራዊትና ከሶርያ ሠራዊት ፊት የተነሣ ወደ ኢየሩሳሌም እንሂድ፤ አልን፤ እንዲሁም በኢየሩሳሌም ተቀመጥን።”
“አንድ የመጽሐፍ ክርታስ ውሰድ፥ ለአንተም ከተናገርሁበት ቀን ከይሁዳ ንጉሥ ከኢዮስያስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በእስራኤልና በይሁዳ ላይ በአሕዛብም ሁሉ ላይ የተናገርሁህን ቃል ሁሉ ጻፍበት።
የይሁዳንም ንጉሥ ኢዮአቄምን እንዲህ በለው፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አንተ፦ የባቢሎን ንጉሥ በርግጥ ይመጣል፤ ይችንም ሀገር ያፈርሳታል፤ ሰውና እንስሳም ያልቃሉ ብለህ ለምን ጻፍህበት? ብለህ ይህን ክርታስ አቃጥለሃል።
አንበሳ ከጕድጓዱ ወጥቶአል፤ አሕዛብንም ሊያጠፋቸው የሚዘርፍ ተነሥቶአል፤ ምድርሽን ባድማ ያደርግ ዘንድ፥ ከተሞችሽንም ሰው እንዳይኖርባቸው ያፈርሳቸው ዘንድ ከስፍራው ወጥቶአል።
የአዛዦችም አለቃ ኤርምያስን ወሰደው፤ እንዲህም አለው፥ “አምላክህ እግዚአብሔር ይህን ክፉ ነገር በዚህ ስፍራ ላይ ተናገረ።
እንዲህም በላቸው፦ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ልኬ ባሪያዬን የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን አመጣለሁ፤ ዙፋኑንም እኔ በሸሸግኋቸው በእነዚህ ድንጋዮች ላይ አኖራለሁ፤ ጋሻዎቹንም በእነርሱ ላይ ያነሣል።
እነሆ ከእርስዋ ዘንድ በቶሎ አባርራቸዋለሁና ከዮርዳኖስ ዳር ወደ ኤታም እንደ አንበሳ ይወጣል፤ ጐልማሶችንም በእርስዋ ላይ እሾማለሁ፤ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ወይስ ለእኔ ጊዜን የሚወስን ማን ነው? ወይስ ፊቴን የሚቃወም እረኛ ማን ነው?”
እናንተ የብንያም ልጆች፥ ክፉ ነገር፥ ታላቅም ጥፋት ከመስዕ ይጐበኛልና ከኢየሩሳሌም ውስጥ ለመሸሽ ጽኑ፤ በቴቁሔ መለከቱን ንፉ፤ በቤትካሪም ላይ ምልክትን አንሡ።
የፈረሶቹን የሩጫ ድምፅ ከዳን ሰማን፤ ከሠራዊቱ ፈረሶች ሩጫ ድምፅ የተነሣም ምድር በመላዋ ተንቀጠቀጠች፤ መጥተውም ምድሪቱንና በእርስዋም ያለውን ሁሉ፥ ከተማዪቱንና የተቀመጡባትንም በሉ።
ሰዎች የሚኖሩባቸው ከተሞች ይጠፋሉ፤ ምድሪቱም ውድማ ትሆናለች፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ በላቸው።”
“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ጢሮስ ሆይ! እነሆ ከሰሜን የነገሥታት ንጉሥ የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን ከፈረሶችና ከሰረገሎች፥ ከፈረሰኞችም፥ ከጉባኤና ከብዙ ሕዝብም ጋር በአንቺ ላይ አመጣለሁ።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያሳድዱአትና ይበዘብዙአት ዘንድ በልባቸው ሁሉ ደስታና በነፍሳቸው ንቀት ምድሬን ርስት አድርገው ለራሳቸው በሰጡ በቀሩት አሕዛብና በኤዶምያስ ሁሉ ላይ በቅንአቴ እሳት ተናግሬአለሁ፤
አቤቱ፥ የተቀደስህ አምላኬ ሆይ፥ አንተ ከዘላለም ጀምሮ አልነበርህምን? እኛ አንሞትም፣ አቤቱ፥ ለፍርድ ሠርተኸዋል፥ ለተግሣጽም አድርገኸዋል።