ከፍ ከፍ ብሎ የነበረውም ይህ ቤት ባድማ ይሆናል፤ በዚያም የሚያልፍ ሁሉ እያፍዋጨ፦ እግዚአብሔር በዚህ ሀገርና በዚህ ቤት ስለ ምን እንዲህ አደረገ? ብሎ ይደነቃል።
ኤርምያስ 18:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምድራቸውን ለጥፋትና ለዘለዓለም ማፍዋጫ አድርገዋል፤ የሚያልፍባት ሁሉ ይደነቃል፤ ራሱንም ያነቃንቃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድራቸው ባድማ፣ ለዘላለም መሣለቂያ ይሆናል፤ በዚያ የሚያልፍ ሁሉ ይደነቃል፤ በመገረምም ራሱን ይነቀንቃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድራቸውን ለመሣቀቂያና ለዘለዓለም ማፍዋጫ አድርገዋል፤ የሚያልፍባት ሁሉ ይደነቃል፥ ራሱንም ይነቀንቃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምድራቸው የዘለዓለም መሳለቂያ፥ ባድማ ትሆናለች፤ በአጠገብዋ የሚያልፉ ሁሉ በማፌዝ ራሳቸውን ይነቀንቃሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድራቸውን ለመደነቂያና ለዘላለም ማፍዋጫ አድርገዋል፥ የሚያልፍባት ሁሉ ይደነቃል፥ ራሱንም ያነቃንቃል። |
ከፍ ከፍ ብሎ የነበረውም ይህ ቤት ባድማ ይሆናል፤ በዚያም የሚያልፍ ሁሉ እያፍዋጨ፦ እግዚአብሔር በዚህ ሀገርና በዚህ ቤት ስለ ምን እንዲህ አደረገ? ብሎ ይደነቃል።
“ስለዚህም የእግዚአብሔር ቍጣ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ሆነ፤ በዐይናችሁም እንደምታዩ ለድንጋጤና ለመደነቂያ፥ ለመዘበቻም አሳልፎ ሰጣቸው።
እግዚአብሔር ስለ እርሱ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ቀላል አድርጋሃለች፤ በንቀትም ሥቃብሃለች፤ የኢየሩሳሌም ልጅ ራስዋን ነቅንቃብሃለች።
እኔም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ ነው?” አልሁ። እርሱም መልሶ እንዲህ አለኝ፥ “ከተሞች የሚኖርባቸውን አጥተው እስኪፈርሱ ድረስ፥ ቤቶችም ሰው አልቦ እስኪሆኑ፥ ምድርም ፈጽሞ ባድማ ሆና እስክትቀር ድረስ ነው፤”
ይህችንም ከተማ ለጥፋትና ለማፍዋጫ አደርጋታለሁ፤ በእርስዋም የሚያልፍ ሁሉ ስለ ተደረገባት መቅሠፍት ሁሉ ይደነግጣል፤ ያፍዋጫልም።
እነሆ ልኬ የሰሜንን ወገኖች ሁሉ፤ ባሪያዬንም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እወስዳለሁ፤ በዚችም ምድርና በሚቀመጡባትም ሰዎች ላይ፥ በዙሪያዋም ባሉ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ፤ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፤ ለጥፋትና ለፉጨት ለዘለዓለምም ዕፍረት ባድማ አደርጋቸዋለሁ።
በሰይፍና በራብ፥ በቸነፈርም አሳድዳቸዋለሁ፤ ባሳደድሁባቸውም አሕዛብ ሁሉ ዘንድ ለርግማንና ለጥፋት፥ ለማፍዋጫም፥ ለመሰደቢያም እንዲሆኑ በምድር መንግሥታት ሁሉ ዘንድ ለመበተን አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።
“የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ቍጣዬና መቅሠፍቴ በኢየሩሳሌም በሚኖሩ ላይ እንደ ፈሰሰ፥ እንዲሁ ወደ ግብፅ በገባችሁ ጊዜ መዓቴ ይፈስስባችኋል፤ እናንተም ለጥላቻና ለጥፋት ለስድብና ለርግማን ትሆናላችሁ፤ ይችንም ስፍራ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩአትም።
ወደ ግብፅም ይገቡ ዘንድ፥ በዚያም ይቀመጡ ዘንድ ፊታቸውን ያቀኑትን የይሁዳን ቅሬታ እወስዳለሁ፤ ሁሉም ይጠፋሉ፤ በግብፅም ምድር ይወድቃሉ፤ በሰይፍና በራብ ይጠፋሉ፤ ከታናሹም ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ በሰይፍና በራብ ይሞታሉ፤ ለጥላቻና ለጥፋት፥ ለመረገሚያና ለመሰደቢያ ይሆናሉ።
እስራኤል ለአንተ መሳቂያ አልሆነምን? ወይስ በሌቦች መካከል ተገኝቶአልን? ስለ እርሱ በተናገርህ ጊዜ ራስህን ትነቀንቃለህ።
ባሶራ ምድረ በዳ፥ መሰደቢያና መረገሚያም እንድትሆን በራሴ ምያለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ከተሞችዋም ሁሉ ለዘለዓለም ባድማ ይሆናሉ።
“ኤዶምያስም ምድረ በዳ ትሆናለች፤ የሚያልፍባትም ሁሉ ይደነቃል፤ ስለ መጣባትም መቅሠፍት ሁሉ ያፍዋጭባታል።
ከእግዚአብሔር ቍጣ የተነሣ ባድማ ትሆናለች እንጂ ሰው አይቀመጥባትም፤ በባቢሎንም በኩል የሚያልፍ ሁሉ ይደነቃል፤ በመጣባትም መቅሠፍት ሁሉ ያፍዋጫል።
ኢየሩሳሌምንም የፍርስራሽ ክምር፥ የቀበሮም ማደሪያ አደርጋታለሁ፤ የይሁዳንም ከተሞች ሰው እንዳይቀመጥባቸው አጠፋቸዋለሁ።
ላሜድ። እናንተ መንገድ ዐላፊዎች ሁሉ! በእናንተ ዘንድ ምንም የለምን? እግዚአብሔር በጽኑ ቍጣው ቀን እኔን እንዳስጨነቀበት በእኔ ላይ እንደ ተደረገው እንደ እኔ ቍስል የሚመስል ቍስል እንዳለ ተመልከቱ፤ እዩም።
ለምድሪቱም ሕዝብ፦ ጌታ እግዚአብሔር በኢየሩሳሌም ስለሚኖሩ ስለ እስራኤል ምድርም እንዲህ ይላል፦ የሚኖሩባት ሁሉ በዐመፅ ይኖራሉና ምድሪቱ በመላዋ ትጠፋ ዘንድ እንጀራቸውን በችግር ይበላሉ፤ ውኃቸውንም በድንጋጤ ይጠጣሉ።
የአሕዛብ ነጋዴዎችም አፍዋጩብሽ፤ አንቺም ፈጽመሽ ትጠፊያለሽ፤ ከእግዲህም ወዲያ እስከ ዘለዓለም አትኖሪም።”
ስለዚህ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለቀሩት አሕዛብ ርስት ትሆኑ ዘንድ በዙሪያችሁ ያሉ አሕዛብ አዋርደዋችኋልና፤ ውጠዋችሁማልና፥ እናንተም የተናጋሪዎች ከንፈር መተረቻና የአሕዛብ ማላገጫ ሆናችኋልና፤
እጄንም እዘረጋባቸዋለሁ፤ በሚኖሩበትም ስፍራ ሁሉ ምድሪቱን ከዴብላታ ምድረ በዳ ይልቅ ውድማና በረሃ አደርጋታለሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።”
ምድርም ከእነርሱ መጥፋት የተነሣ ባዶ ትቀራለች፤ እነርሱም ሳይኖሩ በተፈታችበት ዘመን ዕረፍት ታደርጋለች፤ ፍርዴንም ስለ ናቁ፥ ነፍሳቸውም ሥርዐቴን ስለ ተጸየፈች የኀጢአታቸውን ቅጣት ይሸከማሉ።
አንተን ለጥፋት፥ በእርስዋም የሚኖሩትን ለማፍዋጫ እሰጥ ዘንድ የዘንበሪን ሥርዓትና የአክዓብን ቤት ሥራ ሁሉ ጠብቃችኋል፥ በምክራቸውም ሄዳችኋል፥ የሕዝቤንም ስድብ ትሸከማላችሁ።
እግዚአብሔር መቅሠፍትህን፥ የዘርህንም መቅሠፍት፥ ታላቅና የሚያስፈራ መቅሠፍትን፥ ለብዙ ጊዜ የሚኖር ክፉ ደዌና ሕማምን ሁሉ ያመጣብሃል።
ምድርም በሁለንተናዋ ዲንና ጨው፥ መቃጠልም እንደ ሆነባት፥ እንዳይዘራባትም፥ እንዳታበቅልም፥ ማናቸውም ሣርና ልምላሜም እንዳይወጣባት፥ እግዚአብሔር በቍጣውና በመዓቱ እንደ ገለበጣቸው እንደ ሰዶምና ገሞራ፥ እንደ አዳማና እንደ ሲባዮ እንደ ሆነች ባዩ ጊዜ፥