Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


ሰቈቃወ 1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም መከ​ራና ኀዘን

1 አሌፍ። ሕዝብ ሞል​ቶ​ባት የነ​በ​ረች ከተማ ብቻ​ዋን እን​ዴት ተቀ​መ​ጠች! በአ​ሕ​ዛብ ተመ​ልታ የነ​በ​ረች እንደ መበ​ለት ሆና​ለች፤ አሕ​ዛ​ብን ትገዛ የነ​በ​ረች፥ አው​ራ​ጃ​ዎ​ች​ንም ትገዛ የነ​በ​ረች ገባር ሆና​ለች።

2 ቤት። በሌ​ሊት እጅግ ታለ​ቅ​ሳ​ለች፤ እን​ባ​ዋም በጉ​ን​ጭዋ ላይ አለ፤ ከሚ​ያ​ፈ​ቅ​ሩ​አት ሁሉ የሚ​ያ​ጽ​ና​ናት የለም፤ ወዳ​ጆ​ች​ዋም ሁሉ ወነ​ጀ​ሉ​አት፤ ጠላ​ቶ​ችም ሆኑ​አት።

3 ጋሜል። ይሁዳ ስለ ውር​ደ​ቷና ስለ ባር​ነቷ ብዛት ተሰ​ደ​ደች፤ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ተቀ​መ​ጠች፤ ዕረ​ፍ​ትም አላ​ገ​ኘ​ችም፤ የሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​አት ሁሉ በሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁ​አት መካ​ከል ያዙ​ዋት።

4 ዳሌጥ። ወደ ዓመት በዓል የሚ​መጣ የለ​ምና የጽ​ዮን መን​ገ​ዶች አለ​ቀሱ፤ በሮ​ችዋ ሁሉ ፈር​ሰ​ዋል፤ ካህ​ና​ቷም ያለ​ቅ​ሳሉ፤ ደና​ግ​ሎ​ች​ዋም ተማ​ረኩ፤ እር​ስ​ዋም በም​ሬት አለች።

5 ሄ። ስለ ኀጢ​አቷ ብዛት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዋ​ር​ዶ​አ​ታ​ልና የሚ​ዘ​ባ​በ​ቱ​ባት በራ​ስዋ ላይ ሆኑ፤ ጠላ​ቶ​ች​ዋም ተደ​ሰቱ፤ ሕፃ​ና​ቶ​ች​ዋም በአ​ስ​ጨ​ና​ቂ​ዎች ፊት ተማ​ር​ከ​ዋል።

6 ዋው። ከጽ​ዮን ሴት ልጅ ውበት ሁሉ ተወ​ስ​ዶ​አል፤ አለ​ቆ​ችዋ መሰ​ማ​ሪያ እን​ደ​ማ​ያ​ገኙ አውራ በጎች ሆኑ፤ ከሚ​ያ​ባ​ር​ሩ​አ​ቸው ፊት ተዳ​ክ​መው ሄዱ።

7 ዛይ። ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ቀድሞ ወድዳ በሠ​ራ​ችው ሥራ ሁሉ የመ​ከ​ራ​ዋን ወራት አሰ​በች፤ ሕዝ​ብዋ በአ​ስ​ጨ​ና​ቂ​ዎች እጅ በወ​ደቀ ጊዜ፥ የሚ​ረ​ዳ​ትም በሌ​ላት ጊዜ፥ አስ​ጨ​ና​ቂ​ዎች አዩ​አት፤ በመ​ፍ​ረ​ስ​ዋም ሳቁ።

8 ሔት። ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እጅግ ኀጢ​አት ሠር​ታ​ለች፤ ስለ​ዚህ ረክ​ሳ​ለች፤ በተ​ጨ​ነ​ቀ​ች​በት ቦታ ያከ​ብ​ሩ​አት የነ​በሩ ሁሉ ውር​ደ​ቷን አይ​ተ​ዋ​ልና አቃ​ለ​ሉ​አት፤ እር​ስ​ዋም እየ​ጮ​ኸች ታለ​ቅ​ሳ​ለች፤ ወደ ኋላ​ዋም ዘወር አለች።

9 ጤት። ግዳ​ጅዋ ከእ​ግ​ርዋ በታች ነበረ፤ ፍጻ​ሜ​ዋን አላ​ሰ​በ​ችም፤ ከባድ ሸክ​ምን ተሸ​ከ​መች፤ የሚ​ያ​ጽ​ና​ና​ትም የለም፤ አቤቱ! ጠላት ከፍ ከፍ ብሎ​አ​ልና መከ​ራ​ዬን ተመ​ል​ከት።

10 ዮድ። አስ​ጨ​ና​ቂው በም​ኞቷ ሁሉ ላይ እጁን ዘረጋ፤ ወደ ጉባ​ኤህ እን​ዳ​ይ​ገቡ ያዘ​ዝ​ሃ​ቸው አሕ​ዛብ ወደ መቅ​ደ​ስዋ ሲገቡ አይ​ታ​ለ​ችና።

11 ካፍ። ሕዝ​ብዋ ሁሉ እን​ጀራ አጥ​ተው ያለ​ቅ​ሳሉ፤ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን ለማ​በ​ር​ታት ፍላ​ጎ​ታ​ቸ​ውን ስለ መብል ሰጥ​ተ​ዋል፤ አቤቱ! ተጐ​ሳ​ቍ​ያ​ለ​ሁና እይ፤ ተመ​ል​ከ​ትም።

12 ላሜድ። እና​ንተ መን​ገድ ዐላ​ፊ​ዎች ሁሉ! በእ​ና​ንተ ዘንድ ምንም የለ​ምን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽኑ ቍጣው ቀን እኔን እን​ዳ​ስ​ጨ​ነ​ቀ​በት በእኔ ላይ እንደ ተደ​ረ​ገው እንደ እኔ ቍስል የሚ​መ​ስል ቍስል እን​ዳለ ተመ​ል​ከቱ፤ እዩም።

13 ሜም። ከላይ እሳ​ትን ሰደደ፤ አጥ​ን​ቶ​ች​ንም አቃ​ጠለ፤ ለእ​ግሬ ወጥ​መድ ዘረጋ፤ ወደ ኋላም መለ​ሰኝ፥ አጠ​ፋ​ኝም፤ ቀኑ​ንም ሁሉ መከራ አጸ​ና​ብኝ።

14 ኖን። በእጄ ስለ​ተ​ታቱ ኀጢ​አ​ቶች ተጋ፤ በአ​ን​ገቴ ላይ ወጥ​ተ​ዋል፤ ጕል​በቴ ደከመ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልቋ​ቋ​መው በማ​ል​ች​ለው መከራ እጅ ሰጥ​ቶ​ኛ​ልና።

15 ሳም​ኬት። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀያ​ላ​ኖ​ችን ሁሉ ከመ​ካ​ከሌ አስ​ወ​ገ​ዳ​ቸው፤ ምር​ጦ​ችን ያደ​ቅቅ ዘንድ ጊዜን ጠራ​ብኝ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ድን​ግ​ሊ​ቱን የይ​ሁ​ዳን ልጅ በመ​ጭ​መ​ቂያ እን​ደ​ሚ​ጨ​መቅ ወይን ረገ​ጣት። ስለ​ዚ​ህም አለ​ቅ​ሳ​ለሁ።

16 ዔ። የሚ​ያ​ጽ​ና​ናኝ፥ ነፍ​ሴ​ንም የሚ​መ​ል​ሳት ከእኔ ርቆ​አ​ልና ዐይኔ ውኃ ያፈ​ስ​ሳል። ጠላት በር​ት​ቶ​አ​ልና ልጆች ጠፍ​ተ​ዋል።

17 ፌ። ጽዮን እጅ​ዋን ዘረ​ጋች፤ የሚ​ያ​ጽ​ና​ና​ትም የለም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በያ​ዕ​ቆብ ዙሪያ ያሉ​ትን እን​ዲ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁት አዘዘ፤ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው እንደ ረከ​ሰች ሆና​ለች።

18 ጻዴ። ቃሉን አማ​ር​ሬ​አ​ለ​ሁና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጻድቅ ነው። እና​ንተ አሕ​ዛብ ሁሉ እባ​ካ​ችሁ ስሙ፤ መከ​ራ​ዬ​ንም ተመ​ል​ከቱ፤ ደና​ግ​ሎ​ችና ጐል​ማ​ሶች ተማ​ር​ከው ሄደ​ዋ​ልና።

19 ቆፍ። ወዳ​ጆ​ችን ጠራሁ፤ እነ​ር​ሱም ቸል አሉኝ፤ ካህ​ና​ቶ​ችና ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን ያበ​ረቱ ዘንድ መብል ሲፈ​ልጉ በከ​ተማ ውስጥ ሳያ​ገኙ አለቁ።

20 ሬስ። አቤቱ! ተጨ​ን​ቄ​አ​ለ​ሁና፥ አን​ጀ​ቴም ታው​ኮ​ብ​ኛ​ልና ተመ​ል​ከት፤ መራራ ኀዘን አዝ​ኛ​ለ​ሁና ልቤ በው​ስጤ ተገ​ላ​በ​ጠ​ብኝ፤ በሜዳ ሰይፍ አመ​ከ​ነ​ችኝ፤ በቤ​ትም ሞት አለ።

21 ሣን። እኔ እን​ደ​ማ​ለ​ቅስ ሰም​ተ​ዋል፤ የሚ​ያ​ጽ​ና​ናኝ የለም፤ ጠላ​ቶች ሁሉ መከ​ራ​ዬን ሰም​ተ​ዋል፤ አንተ አድ​ር​ገ​ኸ​ዋ​ልና ደስ አላ​ቸው፤ ስለ እርሱ የተ​ና​ገ​ር​ኸ​ውን ቃል ታመ​ጣ​ለህ፤ እነ​ር​ሱም እንደ እኔ ይሆ​ናሉ።

22 ታው። ልቅ​ሶዬ እጅግ ነውና፥ ልቤም ደክ​ሞ​አ​ልና፥ ክፋ​ታ​ቸው ሁሉ ወደ ፊትህ ይድ​ረስ፥ ስለ ኀጢ​አቴ ሁሉ እኔን እንደ ቃረ​ም​ኸኝ እነ​ር​ሱን ቃር​ማ​ቸው።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos