Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 51:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

43 ከተ​ሞ​ችዋ ባድ​ማና ደረቅ ምድር፥ ሰውም የማ​ይ​ቀ​መ​ጥ​በት፥ የሰ​ውም ልጅ የማ​ያ​ል​ፍ​በት ምድር ሆኑ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

43 ከተሞቿ ሰው የማይኖርባቸው፣ ዝርም የማይልባቸው፣ ደረቅና ምድረ በዳ፣ ባድማ ምድርም ይሆናሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

43 ከተሞችዋ ባድማና ደረቅ ምድር ምድረ በዳም፥ ሰውም የማይቀመጥባቸው የሰውም ልጅ የማያልፍባቸው ምድር ሆኑ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

43 ከተሞቹ ውሃ የማይገኝባቸውና ማንም ሊኖርባቸውም ሆነ ሊተላለፍባቸው የማይችል ምድረ በዳ ሆነዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

43 ከተሞችዋ ባድማና ደረቅ ምድር ምድረ በዳም፥ ሰውም የማይቀመጥበት የሰውም ልጅ የማያልፍበት ምድር ሆኑ።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 51:43
12 Referencias Cruzadas  

እነ​ር​ሱም፥ “ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣን፥ በም​ድረ በዳና በባ​ድማ፥ ዕን​ጨ​ትና ውኃ፥ የእ​ን​ጨት ፍሬም በሌ​ለ​በት ምድር፥ ሰው በማ​ያ​ል​ፍ​በ​ትና የሰው ልጅም በማ​ይ​ቀ​መ​ጥ​በት ምድር የመ​ራን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወዴት አለ? አላ​ሉም።


ለዘ​ለ​ዓ​ለም የሚ​ቀ​መ​ጥ​ባት አይ​ገ​ኝም፤ ከት​ው​ል​ድም እስከ ትው​ልድ ድረስ ሰው አይ​ኖ​ር​ባ​ትም፤ ዓረ​ባ​ው​ያ​ንም በእ​ርሷ አያ​ል​ፉም፤ እረ​ኞ​ችም በው​ስ​ጥዋ አያ​ር​ፉም።


ማንም እን​ዳ​ይ​ቀ​መ​ጥ​ባት የባ​ቢ​ሎ​ንን ምድር ባድማ ያደ​ር​ጋት ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐሳብ በባ​ቢ​ሎን ላይ ጸን​ቶ​አ​ልና ምድር ተና​ወ​ጠች፤ ታመ​መ​ችም።


ባቢ​ሎ​ንም ባድ​ማና የቀ​በሮ ማደ​ሪያ፥ ማፍ​ዋ​ጫም ትሆ​ና​ለች፤ የሚ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ትም ሰው አይ​ገ​ኝም።


እና​ታ​ችሁ እጅግ ታፍ​ራ​ለች፤ የወ​ለ​ደ​ቻ​ች​ሁም ትጐ​ሰ​ቍ​ላ​ለች፤ እነሆ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ኋለ​ኛ​ዪቱ ትሆ​ና​ለች፤ ምድረ በዳና ደረቅ ምድር፥ በረ​ሀም ትሆ​ና​ለች።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ሕ​ዛብ ላይ ነገሠ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቅ​ዱስ ዙፋኑ ላይ ይቀ​መ​ጣል።


ስለ​ዚህ ምክ​ን​ያት ጥፋት ይመ​ጣ​ብ​ሻል፤ ጥል​ቀ​ቱን አታ​ው​ቂም፤ በው​ስ​ጡም ትወ​ድ​ቂ​ያ​ለሽ፤ ጕስ​ቁ​ልና ይመ​ጣ​ብ​ሻል፤ ማም​ለ​ጥም አይ​ቻ​ል​ሽም፤ ሞት ድን​ገት ይመ​ጣ​ብ​ሻል፤ አታ​ው​ቂ​ምም።


አቤቱ! ከሰው ጀምሮ እስከ እን​ስሳ ድረስ ማንም እን​ዳ​ይ​ቀ​መ​ጥ​ባት፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ባድማ እን​ድ​ት​ሆን ታጠ​ፋት ዘንድ በዚች ስፍራ ላይ ተና​ግ​ረ​ሃል በል።


በከ​ተ​ማ​ዎ​ች​ዋም እሾህ፥ በቅ​ጥ​ሮ​ች​ዋም አሜ​ከላ ይበ​ቅ​ሉ​ባ​ታል፤ የአ​ጋ​ን​ንት ማደ​ሪ​ያና የሰ​ጎን ስፍራ ትሆ​ና​ለች።


ምድ​ራ​ቸ​ውን ለጥ​ፋ​ትና ለዘ​ለ​ዓ​ለም ማፍ​ዋጫ አድ​ር​ገ​ዋል፤ የሚ​ያ​ል​ፍ​ባት ሁሉ ይደ​ነ​ቃል፤ ራሱ​ንም ያነ​ቃ​ን​ቃል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios