ኢሳይያስ 21:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከባድ ራእይ ተነገረኝ፤ ወንጀለኛው ይወነጅላል፤ በደለኛውም ይበድላል። የኤላም ሰዎችና የሜዶን መልእክተኛ በእኔ ላይ ይመጣሉ። ዛሬ ግን እጨነቃለሁ፤ እረጋጋለሁም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚያስጨንቅ ራእይ አየሁ፤ ከሓዲ አሳልፎ ይሰጣል፤ ዘራፊ ይዘርፋል። ኤላም ሆይ፤ ተነሺ፤ ሜዶን ሆይ፤ ክበቢ፤ እርሷ ያደረሰችውን ሥቃይ ሁሉ አስቀራለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አስጨናቂ ራእይ ተነገረኝ፤ ከሓዲ አሳልፎ ይሰጣል፤ አጥፊውም ያጠፋል። ኤላም ሆይ፥ ውጪ! ሜዶን ሆይ፥ ክበቢ፤ ጭንቀቷን ሁሉ አጠፋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አስፈሪ የሆነ ራእይ ተገልጦልኛል፤ ይኸውም አንዱ ሌላውን አሳልፎ ይሰጣል፤ ከዳተኛው ይከዳል፤ ዘራፊውም ይዘርፋል። የዔላም ሠራዊት ሆይ! አደጋ ለመጣል ውጡ! የሜዶን ሠራዊት ሆይ! ከተሞችን ክበቡ! እግዚአብሔር በባቢሎን ምክንያት የደረሰውን ሥቃይ ሁሉ ያስወግዳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከባድ ራእይ ተነገረኝ፥ ወንጀለኛው ይወነጅላል አጥፊውም ያጠፋል። ኤላም ሆይ፥ ውጪ! ሜዶን ሆይ፥ ክበቢ፥ ትካዜውን ሁሉ አስቀርቻለሁ። |
በሆሴዕም በዘጠነኛው ዓመት የአሦር ንጉሥ ሰማርያን ያዘ፤ እስራኤልንም ወደ አሶር አፈለሰ፤ በአላሔና በአቦር፤ በጎዛንም ወንዝ፤ በሜዶንም ከተሞች አኖራቸው።
በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ከአሦርና ከግብፅ፥ ከባቢሎንና ከኢትዮጵያ፥ ከኤላሜጤን፥ ከምሥራቅና ከምዕራብ ለቀሩት ለሕዝቡ ቅሬታ ይቀና ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ገና እጁን ይገልጣል።
ይህንም ሙሾ በባቢሎን ንጉሥ ላይ ታነሣለህ፤ እንዲህም ትላለህ፥ “አስጨናቂ እንዴት ዐረፈ! አስገባሪም እንዴት ጸጥ አለ!
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ የጻድቁን ድንቅ ተስፋ ከምድር ዳርቻ ሰምተናል። እነርሱ ግን፥ “የእግዚአብሔርን ሕግ ለሚያፈርሱ ወንጀለኞች ወዮላቸው!” አሉ።
ለሚያዋርዱአችሁ ወዮላቸው! እናንተን ግን የሚያዋርዳችሁ የለም፤ የሚወነጅላችሁ እናንተን የሚወነጅል አይደለም፤ ወንጀለኞች ይጠመዳሉ፤ ይያዛሉም፤ ብል እንደበላው ልብስም ያልቃሉ።
በእግዚአብሔር የተሰበሰቡም ይመለሳሉ፤ በደስታም ተመልሰው ወደ ጽዮን ይመጣሉ፤ የዘለዓለም ደስታም በራሳቸው ላይ ይሆናል፤ ሐሤትንና ደስታንም ያገኛሉ፤ መከራ፥ ኀዘንና ትካዜም ይጠፋሉ።
በሕዝቤ ላይ ተቈጥቼ ነበር፤ ርስቴንም አረከስሽ፤ በእጅሽም አሳልፌ ሰጠኋቸው፤ ለሽማግሌዎቻቸው አልራራሽም፤ ቀንበራቸውንም እጅግ አክብደሻል።
በእውነት ኤፍሬም ለእኔ የተወደደ ልጅ ነው፤ ደስ የሚያሰኝም ሕፃን ነው፤ በእርሱ ላይ በተናገርሁ ቍጥር አስበዋለሁ፤ ስለዚህ አንጀቴ ታወከችለት፤ ርኅራኄም እራራለታለሁ፥” ይላል እግዚአብሔር።
አንተ፦ እግዚአብሔር በሕማሜ ላይ ኀዘንን ጨምሮብኛልና ወዮልኝ! በልቅሶዬ ጩኸት ደክሜአለሁ፤ ዕረፍትንም አላገኘሁም ብለሃል።
በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ በመጀመሪያው ዓመተ መንግሥት ስለ ኤላም ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው።
“የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ ዋና የኀይላቸው መሣሪያ የሆነውን የኤላምን ቀስት እሰብራለሁ።
“እናንተ ቀስትን የምትገትሩ ሰዎች ሁሉ፥ በባቢሎን ላይ በዙሪያዋ ተሰለፉ፤ በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአት ሠርታለችና ወርውሩባት፤ እርስዋንም ከመውጋት ቸል አትበሉ፤
የሚቤዢአቸው ብርቱ ነው፤ ስሙም ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር ነው፤ ምድርን ያሳርፍ ዘንድ፥ በባቢሎንም የሚኖሩትን ያውክ ዘንድ ጠላቶቹን ወቀሳ ይወቅሳቸዋል።
“ፍላጾችን አዘጋጁ፤ ጕራንጕሬዎችንም ሙሉ፤ እግዚአብሔር ያጠፋት ዘንድ ቍጣው በባቢሎን ላይ ነውና የሜዶንን ንጉሥ መንፈስ አስነሥቶአል፤ የእግዚአብሔር በቀል የመቅደሱ በቀል ነውና።
በባቢሎንም ላይ እበቀላለሁ፤ የዋጠችውንም ከአፍዋ አስተፋታለሁ፤ አሕዛብም ከዚያ ወዲያ ወደ እርስዋ አይሰበሰቡም፤ የባቢሎንም ቅጥሮች ይወድቃሉ።
ባቢሎንም ወደ ሰማይ ብትወጣ፥ ቅፅሮችዋንም በኀይልዋ ብታጸና፥ ከእኔ ዘንድ አጥፊዎች ይመጡባታል፥ ይላል እግዚአብሔር።
ታው። ልቅሶዬ እጅግ ነውና፥ ልቤም ደክሞአልና፥ ክፋታቸው ሁሉ ወደ ፊትህ ይድረስ፥ ስለ ኀጢአቴ ሁሉ እኔን እንደ ቃረምኸኝ እነርሱን ቃርማቸው።
ይማረክ ዘንድ ያለው ማንም ቢኖር ወደ ምርኮነት ይሄዳል፤ በሰይፍ የሚገድል ማንም ቢኖር ራሱ በሰይፍ እንዲገደል ይገባዋል። የቅዱሳን ትዕግሥትና እምነት በዚህ ነው።
እግዚእብሔር በእኔና በአንተ መካከል ይፍረድ፤ እግዚአብሔርም አንተን ይበቀልልኝ፤ እጄ ግን በአንተ ላይ አትሆንም።