Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 21:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ስለ​ዚ​ህም ወገቤ ሕማም ተሞላ፤ እን​ደ​ም​ት​ወ​ልድ ሴትም ምጥ ያዘኝ፤ ከሕ​ማሜ የተ​ነሣ አል​ሰ​ማም፤ ከድ​ን​ጋ​ጤም የተ​ነሣ አላ​ይም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ወገቤ በዚህ ሥቃይ ተሞላ፤ በምጥ ላይ እንዳለች ሴት ጭንቅ ያዘኝ፤ በሰማሁት ነገር ተንገዳገድሁ፤ ባየሁትም ነገር ተሸበርሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ስለዚህ ወገቤ ሕመም ተሞላ፤ ምጥ እንደ ያዛት ሴት አስጨነቀኝ፤ ከሕመሜ የተነሣ አልሰማም፥ ከድንጋጤም የተነሣ አላይም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 በዚህም ምክንያት ሰውነቴ ታመመ፤ ምጥ እንደ ያዛት ሴትም አስጨነቀኝ፤ በምሰማው ነገር ታወክሁ፤ በማየውም ነገር ግራ ተጋባሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ስለዚህ ወገቤ ሕመም ተሞላ፥ እንደምትወልድ ሴት ምጥ ያዘኝ፥ ከሕመሜ የተነሣ አልሰማም፥ ከድንጋጤም የተነሣ አላይም።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 21:3
17 Referencias Cruzadas  

በኀ​ይ​ላ​ቸው የሚ​ታ​መኑ፥ በባ​ለ​ጠ​ግ​ነ​ታ​ቸ​ውም ብዛት የሚ​ኮሩ፤


ሽማ​ግ​ሎች ይደ​ነ​ግ​ጣሉ፤ እን​ደ​ም​ት​ወ​ልድ ሴትም ምጥ ይይ​ዛ​ቸ​ዋል፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ይገ​ዳ​ደ​ላሉ፤ ይደ​ነ​ቃሉ፤ ፊታ​ቸ​ውም እንደ እሳት ይን​በ​ለ​በ​ላል።


ሞዓብ ራሷን ይዛ ትጮ​ኻ​ለች፤ ለል​ቧም ይረ​ዳ​ታል፤ እስከ ሴጎ​ርም ድረስ ብቻ​ዋን ታለ​ቅ​ሳ​ለች። ሞዓብ እንደ ሦስት ዓመት ጥጃ ናትና በሉ​ሒት ዐቀ​በት ትጮ​ኻ​ለች። በአ​ሮ​ሜ​ዎን መን​ገ​ድም ይመ​ለ​ሳሉ፤ ይጮ​ኻ​ሉም፥ ጥፋ​ትና መና​ወ​ጥም ይሆ​ናል።


ስለ​ዚህ ልቤ ስለ ሞዓብ እንደ መሰ​ንቆ ትጮ​ኻ​ለች። አጥ​ን​ቶ​ችም እንደ ተመ​ረገ ግድ​ግዳ ይሆ​ናሉ።


ስለ​ዚህ በኢ​ያ​ዜር ልቅሶ ስለ ሴባማ ወይን ግንድ አለ​ቅ​ሳ​ለሁ፤ ሐሴ​ቦ​ንና ኤል​ያሊ ሆይ፥ ዛፎ​ችሽ ወድ​ቀ​ዋል፤ የዛ​ፍ​ሽን ፍሬና የወ​ይ​ን​ሽን መከር እረ​ግ​ጣ​ለሁ፤ ተክ​ሎ​ችሽ ሁሉ ይወ​ድ​ቃሉ።


የፀ​ነ​ሰች ሴት ለመ​ው​ለድ ስት​ቀ​ርብ እን​ደ​ም​ት​ጨ​ነ​ቅና በምጥ እን​ደ​ም​ት​ጮህ፥ አቤቱ፥ እን​ዲሁ በፊ​ትህ ለወ​ዳ​ጅህ ሆነ​ናል።


አን​ጀቴ! አን​ጀቴ! ልቤ በጣም ታም​ሞ​አል፤ ነፍ​ሴም አእ​ም​ሮ​ዋን አጥ​ታ​ለች፤ በው​ስ​ጤም ልቤ ታው​ኮ​ብ​ኛል፤ ነፍ​ሴም የመ​ለ​ከ​ትን ድም​ፅና የሰ​ል​ፍን ውካታ ሰም​ታ​ለ​ችና ዝም እል ዘንድ አል​ች​ልም።


ሐቄ​ር​ዮት ተያ​ዘች፤ አን​ባ​ዎ​ች​ዋም ተወ​ስ​ደ​ዋል፤ በዚ​ያም ቀን የሞ​አብ ኀያ​ላን ልብ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ልብ ይሆ​ናል።


እነሆ እንደ ንስር ወጥቶ ይመ​ለ​ከ​ታል፤ ክን​ፉ​ንም በባ​ሶራ ላይ ይዘ​ረ​ጋል፤ በዚ​ያም ቀን የኤ​ዶ​ም​ያስ ኀያ​ላን ልብ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ልብ ይሆ​ናል።


የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ውካ​ታ​ቸ​ውን ሰም​ቶ​አል፤ እጁም ደክ​ማ​ለች፤ ምጥ ወላድ ሴትን እን​ደ​ሚ​ይ​ዛ​ትም ጭን​ቀት ይዞ​ታል፤


ጩኸ​ታ​ቸ​ውን ሰም​ተን፥ እጃ​ችን ደክ​ማ​ለች፤ ወላ​ድን ሴት ምጥ እን​ደ​ሚ​ይ​ዛት ጭን​ቀት ይዞ​ናል።


እኔ ሰምቻለሁ፥ ልቤም ደነገጠብኝ፣ ከድምፁ የተነሣ ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ፣ መንቀጥቀጥ ወደ አጥንቶቼ ውስጥ ገባ፣ በስፍራዬ ሆኜ ተናወጥሁ፣ በሚያስጨንቁን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ የመከራን ቀን ዝም ብዬ እጠብቃለሁ።


ሴት በም​ት​ወ​ል​ድ​በት ጊዜ ወራቷ ስለ ደረሰ ታዝ​ና​ለች፤ ነገር ግን ልጅ​ዋን ከወ​ለ​ደች በኋላ ስለ ደስ​ታዋ ከዚያ ወዲያ ምጥ​ዋን አታ​ስ​በ​ውም፤ በዓ​ለም ወንድ ልጅን ወል​ዳ​ለ​ችና።


ከፈ​ራ​ህ​በት ከል​ብህ ፍር​ሀት የተ​ነሣ፥ በዐ​ይ​ን​ህም ካየ​ኸው የተ​ነሣ፥ ሲነጋ እን​ዴት ይመሽ ይሆን? ትላ​ለህ፤ ሲመ​ሽም እን​ዴት ይነጋ ይሆን? ትላ​ለህ።


ሰላምና ደኅንነት ነው ሲሉ ያን ጊዜ ምጥ እርጕዝን እንደሚይዛት ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል፤ከቶም አያመልጡም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos