Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 21:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ስለ ምድረ በዳ የተ​ነ​ገረ ቃል፤ ዐውሎ ነፋስ በም​ድረ በዳ እን​ደ​ሚ​ያ​ልፍ፥ እን​ዲሁ ከሚ​ያ​ስ​ፈራ ሀገር ከም​ድረ በዳ ይመ​ጣል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 በባሕሩ ዳር ባለው ምድረ በዳ ላይ የተነገረ ንግር፤ ዐውሎ ነፋስ ከደቡብ እየጠራረገ እንደሚመጣ፣ ወራሪ ከአሸባሪ ምድር፣ ከምድረ በዳ ይመጣል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በባሕር አጠገብ ስላለው ስለ ምድረ በዳ የተነገረ ትንቢት። ዐውሎ ነፋስ ከደቡብ እንደሚወጣ፥ እንዲሁ ከሚያስፈራ አገር ከምድረበዳ ይወጣል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 በባሕር አጠገብ ስለሚገኝ ምድረ በዳ የተነገረ የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው። ከደቡብ በኩል የሚመጣው ዐውሎ ነፋስ ሁሉን ነገር ጠራርጎ እንደሚወስድ አስፈሪ ከሆነች ከአንዲት አገር ከባድ ጥፋት ይመጣል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በባሕር አጠገብ ስላለው ስለ ምድረ በዳ የተነገረ ሸክም። ዐውሎ ነፋስ ከደቡብ እንደሚወጣ፥ እንዲሁ ከሚያስፈራ አገር ከምድረ በዳ ይወጣል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 21:1
21 Referencias Cruzadas  

“ባቢ​ሎ​ንን የወ​ፎች መኖ​ሪያ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ እንደ ኢም​ን​ትም ትሆ​ና​ለች፤ በጥ​ፋ​ትም እንደ ረግ​ረግ ጭቃ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ” ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ባሕር በባ​ቢ​ሎን ላይ ወጣ፤ በሞ​ገ​ዱም ብዛት ተከ​ደ​ነች።


የአ​ሞጽ ልጅ ኢሳ​ይ​ያስ በባ​ቢ​ሎን ላይ ያየው ራእይ።


እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ ይገለጣል፥ ፍላጻውም እንደ መብረቅ ይወጣል፣ ጌታ እግዚአብሔርም መለከትን ይነፋል፥ በደቡብም ዐውሎ ነፋስ ይሄዳል።


ስለ ደማ​ስቆ የተ​ነ​ገረ ቃል። “እነሆ፥ ደማ​ስቆ ከከ​ተ​ሞች መካ​ከል ተለ​ይታ ትጠ​ፋ​ለች፤ ትፈ​ር​ሳ​ለ​ችም።


የሌላ ሀገር ሰዎች፥ የአ​ሕ​ዛብ ጨካ​ኞች የሆኑ፥ ቈር​ጠው ጣሉት፤ በተ​ራ​ሮ​ችና በሸ​ለ​ቆ​ዎች ሁሉ ውስጥ ጫፎቹ ወደቁ፤ ቅር​ን​ጫ​ፎ​ቹም በም​ድር ፈሳ​ሾች ሁሉ ላይ ተሰ​ባ​በሩ፤ የም​ድ​ርም አሕ​ዛብ ሁሉ ከጥ​ላው ተመ​ል​ሰው ተዉት።


እር​ሱና ሕዝቡ የአ​ሕ​ዛ​ብም ኀያ​ላን ምድ​ሪ​ቱን ለማ​ጥ​ፋት ይላ​ካሉ፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ን​ንም በሰ​ይፍ ይወ​ጉ​አ​ቸ​ዋል፤ ምድ​ሪ​ቱም በሙ​ታን ትሞ​ላ​ለች።


ከተ​ሰ​ወረ ማደ​ሪ​ያ​ውም ችግር፥ ከተ​ራ​ሮች ጫፍም ብርድ ይመ​ጣል።


ፍላ​ጾ​ቻ​ቸው ተስ​ለ​ዋል፤ ቀስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ተለ​ጥ​ጠ​ዋል፤ የፈ​ረ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም ኮቴ እንደ ቡላድ፥ የሰ​ረ​ገ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም መን​ኰ​ራ​ኵር እንደ ዐውሎ ነፋስ ይቈ​ጠ​ራል።


እኔም አየሁ፤ እነ​ሆም ከሰ​ሜን በኩል ዐውሎ ነፋ​ስና ታላቅ ደመና፥ የሚ​በ​ር​ቅም እሳት መጣ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ፀዳል ነበረ፤ በመ​ካ​ከ​ልም በእ​ሳቱ ውስጥ የሚ​ብ​ለ​ጨ​ለጭ ነገር ነበረ።


እንደ ዝናም ትወ​ጣ​ለህ፤ እንደ ደመ​ናም ምድ​ርን ትሸ​ፍን ዘንድ ትደ​ር​ሳ​ለህ፤ አን​ተም ከብዙ ሕዝ​ብና ሠራ​ዊት ጋር ትወ​ድ​ቃ​ለህ።”


ስለ​ዚህ በሠ​ራ​ዊት ጌታ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መዓት በጽኑ ቍጣው ቀንም ሰማ​ያት ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ፤ ምድ​ርም ከመ​ሠ​ረቷ ትና​ወ​ጣ​ለች።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያዕ​ቆ​ብን ይም​ረ​ዋል፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ደግሞ ይመ​ር​ጠ​ዋል፤ በሀ​ገ​ራ​ቸ​ውም ያር​ፋሉ፤ መጻ​ተ​ኞ​ችም ከእ​ነ​ርሱ ጋር አንድ ይሆ​ናሉ፤ ከያ​ዕ​ቆ​ብም ቤት ጋር ይጨ​መ​ራሉ።


ከደ​መ​ና​ዎች ከፍታ በላይ ዐር​ጋ​ለሁ፤ በል​ዑ​ልም እመ​ሰ​ላ​ለሁ አልህ።


አንቺ ድን​ግል የባ​ቢ​ሎን ልጅ ሆይ፥ ውረጂ፤ በት​ቢ​ያም ላይ ተቀ​መጪ፤ የከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሴት ልጅ ሆይ፥ ከዚህ በኋላ ለስ​ላ​ሳና ቅም​ጥል አት​ባ​ዪ​ምና ያለ ዙፋን በመ​ሬት ላይ ተቀ​መጪ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ በባ​ቢ​ሎን ላይና በከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር በሚ​ኖ​ሩት ላይ የሚ​ያ​ቃ​ጥ​ልና የሚ​ያ​ጠፋ ነፋ​ስን አስ​ነ​ሣ​ለሁ።


ስድ​ባ​ች​ንን ስለ ሰማን አፍ​ረ​ናል፤ ባዕ​ዳን ሰዎ​ችም ወደ ቤተ መቅ​ደ​ሳ​ችን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ገብ​ተ​ዋ​ልና ውር​ደት ፊታ​ች​ንን ከድ​ኖ​ታል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios