ሐኖንም የዳዊትን አገልጋዮች ወስዶ የጢማቸውን ገሚስ ላጨ፤ ልብሳቸውንም እስከ ወገባቸው ድረስ ከሁለት ቀድዶ ሰደዳቸው።
ኢሳይያስ 15:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለራሳችሁ እዘኑ፤ ጣዖታችሁና መሠዊያችሁ ያሉባት ዲቦን ትጠፋለችና፤ ወደዚያም ወጥታችሁ በሞዓብ ናባው አልቅሱ፤ ወዮም በሉ፤ ራስ ሁሉ በራ ይሆናል፤ ክንድም ሁሉ ይቈረጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዲቦን ወደ መቅደሱ ወጣ፤ ሊያለቅስም ወደ ኰረብታው ሄደ፤ ሞዓብ ስለ ናባው፣ ስለ ሜድባም ዋይታ ያሰማል፤ ራስ ሁሉ ተመድምዷል፤ ጢምም ሁሉ ተላጭቷል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ባይት ወደ ዲቦንም ወደ ኮረብታ መስገጃዎችም ለልቅሶ ወጥተዋል፤ ሞዓብ በናባውና በሜድባ ላይ ታለቅሳለች፤ ራሳቸው ሁሉ ተነጭቶአል፥ ጢማቸውም ሁሉ ተላጭቷል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጺቦን ሕዝብም በቤተ ጣዖታቸው ለማልቀስ ወደ ኰረብታ ይወጣሉ፤ የሞአብ ሕዝብ ስለ ነቦና ስለ ሜዳባ ከተሞቻቸው በከባድ ሐዘን ያለቅሳሉ፤ ከሐዘናቸውም የተነሣ ጠጒራቸውንና ጢማቸውን ተላጭተዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ባይት ወደ ዲቦንም ወደ ኮረብታ መስገጃዎችም ለልቅሶ ወጥተዋል፥ ሞዓብ በናባውና በሜድባ ላይ ታለቅሳለች፥ ራሳቸው ሁሉ ተነጭቶአል፥ ጢማቸውም ሁሉ ተላጭቶአል። |
ሐኖንም የዳዊትን አገልጋዮች ወስዶ የጢማቸውን ገሚስ ላጨ፤ ልብሳቸውንም እስከ ወገባቸው ድረስ ከሁለት ቀድዶ ሰደዳቸው።
ሐናንም የዳዊትን አገልጋዮች ወስዶ የጢማቸውን ግማሽ አስላጫቸው፤ ልብሳቸውንም እስከ ወገባቸው ድረስ ለሁለት ቀድዶ ሰደዳቸው።
እናንተ የከተሞች በሮች ሆይ፥ ወዮ በሉ፤ እናንተም ከተሞች ሆይ፥ ደንግጡ፥ ጩኹም፤ ፍልስጥኤማውያን ሆይ፥ ሁላችሁም ቀልጣችኋል፤ ጢስ ከሰሜን ይወጣልና፥ እንግዲህም አትኖሩምና።
በየመንገድዋ ማቅ ታጠቁ፤ በየሰገነቶችዋም አልቅሱ፤ በየአደባባዮችዋም እንባን እጅግ እያፈሰሳችሁ ወዮ በሉ።
ለኀፍረት ይሆንብሃል፤ ሞዓብ በመሠዊያዎችዋ ደክማለችና፤ ለጸሎትም ወደ ጣዖቶችዋ ትሄዳለች፤ ሊያድኑአትም አይችሉም።
እንዲህም ይሆናል፤ ስለ ሥራሽ ክፋት በሽቱ ፋንታ ትቢያ ይሁንብሽ፤ በወርቅ መታጠቂያሽም ፋንታ ገመድ ታጠቂ፤ በራስ ወርቅ ቀጸላሽም ፋንታ ቡሃነት ይውጣብሽ፤ በሐር መጐናጸፊያሽ ፋንታ ማቅ ልበሽ።
የእስራኤል ልጆች በመንገዳቸው ዐምጸዋልና፥ ቅዱስ አምላካቸውንም ረስተዋልና ከብዙ ሰዎች ድምፅ ተሰማ፤ የእስራኤል ልጆች ልቅሶና ጩኸትም ተሰማ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እነሆ ውኃ ከሰሜን ይነሣል፥ የሚያጥለቀልቅም ፈሳሽ ይሆናል፤ በሀገሪቱና በመላዋ ሁሉ፥ በከተማዪቱና በሚኖሩባትም ላይ ይጐርፋል፤ ሰዎቹም ይጮኻሉ፤ በምድርም የሚኖሩ ሁሉ ያለቅሳሉ።
ስለ ሞአብ፤ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ናባው ጠፍታለችና ወዮላት! ቂርያታይም አፍራለች፤ ተይዛማለች፤ መጠጊያዋም አፍራለች፤ ደንግጣማለች።
በዲቦን የምትኖሪ ሆይ! ሞአብን የሚያጠፋ ወጥቶብሻልና፥ አምባሽንም ሰብሮአልና ከክብርሽ ውረጂ፤ በጭቃም ላይ ተቀመጪ።
ሞአብንና በኮረብታው መስገጃ ላይ የሚሠዋውን፥ ለአማልክቱም የሚያጥነውን አጠፋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።
ሐሴቦን ሆይ! ጋይ ፈርሳለችና አልቅሽላት፤ እናንተም የራባት ሴቶች ልጆች ሆይ! ሚልኮም፥ ካህናቱና አለቆቹም በአንድነት ይማረካሉና ጩኹ፤ ማቅም ታጠቁ፤ አልቅሱም።
“እግዚአብሔር የቍጣውን ትውልድ ጥሎአልና፥ ትቶታልምና ጠጕርሽን ቈርጠሽ፥ ጣዪው፤ በከንፈሮችሽም ሙሾ አውርጂ።
ማቅም ትታጠቃላችሁ፤ ድንጋጤም ይሸፍናችኋል፤ በፊትም ሁሉ ላይ ሐፍረት ይሆናል፤ በራሳችሁም ሁሉ ላይ ቡሃነት ይሆናል።
ዓመት በዓላችሁንም ወደ ልቅሶ፥ ዝማሬያችሁንም ወደ ዋይታ እለውጣለሁ፤ ማቅንም በወገብ ሁሉ ላይ፥ ቡሃነትንም በራስ ሁሉ ላይ ላይ አመጣለሁ፤ እንደ ወዳጅ ልቅሶ አደርጋችኋለሁ፤ ከእርሱም ጋር ያሉት እንደ መከራ ቀን ይሆናሉ።
ሙሴም ከሞዓብ ሜዳ በኢያሪኮ ፊት ለፊት ወዳለው ወደ ናባው ተራራ ወደ ፈስጋ ራስ ወጣ፤ እግዚአብሔርም እስከ ዳን ድረስ ያለውን የገለዓድን ምድር አሳየው፤