Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 14:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 እና​ንተ የከ​ተ​ሞች በሮች ሆይ፥ ወዮ በሉ፤ እና​ን​ተም ከተ​ሞች ሆይ፥ ደን​ግጡ፥ ጩኹም፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሆይ፥ ሁላ​ች​ሁም ቀል​ጣ​ች​ኋል፤ ጢስ ከሰ​ሜን ይወ​ጣ​ልና፥ እን​ግ​ዲ​ህም አት​ኖ​ሩ​ምና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 በር ሆይ፤ ዋይ በል! ከተማ ሆይ፤ ጩኽ! ፍልስጥኤማውያን ሆይ፤ ሁላችሁም በፍርሀት ቅለጡ! ጢስ ከሰሜን መጥቶብሃል፤ ከሰልፉ ተነጥሎ የሚቀር የለምና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 አንተ በር ሆይ፥ ወዮ በል፥ አንቺም ከተማ ሆይ፥ ጩኺ፤ ፍልስጥኤም ሆይ፥ ሁላችሁም ቀልጣችኋል፤ ጢስ ከሰሜን ይመጣል ከጭፍራውም ተለይቶ የሚቀር የለም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 በመግቢያው በር ሆናችሁ ወዮ በሉ! በከተማው ውስጥ ሆናችሁ ኡኡ! በሉ፤ ከወታደሮቹ አንዱ እንኳ ወደ ኋላ የማይል ኀይለኛ ጠላት ከሰሜን ስለ መጣ ፍልስጥኤማውያን ሁሉ በፍርሃት ይርበድበዱ!

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 አንተ በር ሆይ፥ ወዮ በል፥ አንቺም ከተማ ሆይ፥ ጩኺ፥ ፍልስጥኤም ሆይ፥ ሁላችሁም ቀልጣችኋል፥ ጢስ ከሰሜን ይመጣል ከጭፍራውም ተለይቶ የሚቀር የለም።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 14:31
13 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፥ “ከሰ​ሜን ወገን ክፉ ነገር በም​ድ​ሪቱ በተ​ቀ​መጡ ሁሉ ላይ ይፈ​ስ​ሳል።


የአ​ሦር ንጉሥ አርና ጣን​ታ​ንን በሰ​ደደ ጊዜ፥ እር​ሱም ወደ አዛ​ጦን በመጣ ጊዜ፥ አዛ​ጦ​ን​ንም ወግቶ በያ​ዛት ጊዜ፥


ፍል​ስ​ጥ​ኤም ሆይ፥ ከእ​ባቡ ዘር እፉ​ኝት ይወ​ጣ​ልና፥ ፍሬ​ውም የሚ​በ​ር​ርና እሳት የሚ​መ​ስል እባብ ይሆ​ና​ልና፥ የኀ​ይ​ላ​ችሁ ቀን​በር ተሰ​ብ​ሮ​አ​ልና ሁላ​ች​ሁም ደስ አይ​በ​ላ​ችሁ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን ቀር​ቦ​አ​ልና አል​ቅሱ፤ ጥፋ​ትም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ይመ​ጣል።


ከተ​ሞ​ችም ባድማ ይሆ​ናሉ፤ ቤቶ​ችም ባዶ ሆነው ይቀ​ራሉ፤ ይጠ​ፋ​ሉም።


ሞዓብ ዋይ በሉ፤ ሁሉም በሞ​ዓብ ዋይ ይላ​ሉና፤ በዴ​ሴት የሚ​ኖ​ሩም አያ​መ​ል​ጡም፤ ጠብን ያጭ​ራሉ፤ ያፍ​ራ​ሉም።


የጌ​ጦ​ች​ሽም ሣጥ​ኖች ያለ​ቅ​ሳሉ፤ ይዋ​ረ​ዳ​ሉም፤ ብቻ​ሽ​ንም ትቀ​ሪ​ያ​ለሽ፤ ከም​ድ​ርም ጋር ትቀ​ላ​ቀ​ያ​ለሽ።”


በዚ​ያም ቀን ይህን ቅኔ በይ​ሁዳ ምድር ይዘ​ም​ራሉ፤ እነ​ሆም፥ የጸ​ና​ችና የም​ታ​ድን፥ ቅጥ​ር​ንና ምሽ​ግ​ንም የም​ታ​ደ​ርግ ከተማ አለ​ችን።


በየ​ቍ​ጥ​ራ​ቸው ያል​ፋሉ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም አንዱ አይ​ጠ​ፋም፤ እርስ በር​ሳ​ቸው አይ​ተ​ጣ​ጡም፤ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዝ​ዞ​አ​ቸ​ዋ​ልና መን​ፈ​ሱም ሰብ​ስ​ቦ​አ​ቸ​ዋ​ልና።


“በፊ​ትህ እሄ​ዳ​ለሁ፤ ተራ​ሮ​ች​ንም ዝቅ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ የና​ሱ​ንም ደጆች እሰ​ብ​ራ​ለሁ፤ የብ​ረ​ቱ​ንም መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎች እቈ​ር​ጣ​ለሁ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ ውኃ ከሰ​ሜን ይነ​ሣል፥ የሚ​ያ​ጥ​ለ​ቀ​ል​ቅም ፈሳሽ ይሆ​ናል፤ በሀ​ገ​ሪ​ቱና በመ​ላዋ ሁሉ፥ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱና በሚ​ኖ​ሩ​ባ​ትም ላይ ይጐ​ር​ፋል፤ ሰዎ​ቹም ይጮ​ኻሉ፤ በም​ድ​ርም የሚ​ኖሩ ሁሉ ያለ​ቅ​ሳሉ።


ይህም የሚ​ሆ​ነው ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ሁሉ ታጠፋ ዘንድ፥ ጢሮ​ስ​ንና ሲዶ​ናን የቀ​ሩ​ት​ንም ረዳ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ታጠፋ ዘንድ ስለ​ም​ት​መ​ጣው ቀን ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ን​ንና በከ​ፍ​ቶር ደሴት የቀ​ሩ​ትን ያጠ​ፋ​ልና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios