Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 21:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ስለ ሞተው ሰው ራሳ​ቸ​ውን አይ​ላጩ፤ ጢማ​ቸ​ው​ንም አይ​ላጩ፤ ሥጋ​ቸ​ው​ንም አይ​ንጩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 “ ‘ካህናት ዐናታቸውን አይላጩ፤ የጢማቸውን ዙሪያ አይላጩ፤ ሰውነታቸውንም አይንጩ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ካህናት አናታቸውን አይላጩ፥ ጢማቸውንም አይላጩ፥ ገላቸውንም በመቁረጥ አይተልትሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 “ካህናት፥ ለሙታን በማዘን የራስ ጠጒራቸውን አይላጩ፤ ጢማቸውን አሳጥረው አይቊረጡ፤ ፊታቸውንም አይንጩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ራሳቸውን አይላጩ፥ ጢማቸውንም አይላጩ፥ ሥጋቸውንም አይንጩ።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 21:5
12 Referencias Cruzadas  

ለራ​ሳ​ችሁ እዘኑ፤ ጣዖ​ታ​ች​ሁና መሠ​ዊ​ያ​ችሁ ያሉ​ባት ዲቦን ትጠ​ፋ​ለ​ችና፤ ወደ​ዚ​ያም ወጥ​ታ​ችሁ በሞ​ዓብ ናባው አል​ቅሱ፤ ወዮም በሉ፤ ራስ ሁሉ በራ ይሆ​ናል፤ ክን​ድም ሁሉ ይቈ​ረ​ጣል።


በዚ​ያም ቀን የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልቅ​ሶ​ንና ዋይ​ታን፥ ራስን መን​ጨ​ት​ንና ማቅን መል​በ​ስን ጠራ።


ታላ​ላ​ቆ​ችና ታና​ና​ሾች በዚች ምድር ይሞ​ታሉ ፥ አይ​ቀ​በ​ሩም ሰዎ​ችም አያ​ለ​ቅ​ሱ​ላ​ቸ​ውም፤ ስለ እነ​ር​ሱም ፊት አይ​ነ​ጩ​ላ​ቸ​ውም፤ ራስ​ንም አይ​ላ​ጩ​ላ​ቸ​ውም፤


በሰው ሁሉ ራስ ላይ ቡሃ​ነት አለ፤ ጽሕ​ማ​ቸ​ውን ሁሉ ይላ​ጫሉ፤ እጆች ሁሉ ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ፤ ሁሉም በወ​ገ​ባ​ቸው ማቅን ይታ​ጠ​ቃሉ።


ራሳ​ቸ​ው​ንም አይ​ላጩ፥ የራ​ሳ​ቸ​ው​ንም ጠጕር ይከ​ር​ከሙ እንጂ ጠጕ​ራ​ቸ​ውን አያ​ሳ​ድጉ።


“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! ራስን ከሚ​ላጭ ምላጭ ይልቅ የተ​ሳለ ጐራ​ዴን ውሰድ፤ ወስ​ደ​ህም በእ​ር​ስዋ ራስ​ህ​ንና ጢም​ህን ተላጭ፤ ሚዛ​ን​ንም ውሰድ፤ ጠጕ​ሩ​ንም ትከ​ፋ​ፍ​ለ​ዋ​ለህ።


ሙሴም አሮ​ንን፥ ልጆ​ቹ​ንም አል​ዓ​ዛ​ር​ንና ኢታ​ም​ርን፥ “እን​ዳ​ት​ሞቱ፥ በማ​ኅ​በ​ሩም ላይ ሁሉ ቍጣ እን​ዳ​ይ​ወ​ርድ ራሳ​ች​ሁን አት​ንጩ፤ ልብ​ሳ​ች​ሁ​ንም አት​ቅ​ደዱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስላ​ቃ​ጠ​ላ​ቸው ማቃ​ጠል ግን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሁሉ ያል​ቅሱ።


ራሱን ያጐ​ሰ​ቍል ዘንድ ከሕ​ዝቡ በማ​ንም አይ​ር​ከስ።


ዓመት በዓ​ላ​ች​ሁ​ንም ወደ ልቅሶ፥ ዝማ​ሬ​ያ​ች​ሁ​ንም ወደ ዋይታ እለ​ው​ጣ​ለሁ፤ ማቅ​ንም በወ​ገብ ሁሉ ላይ፥ ቡሃ​ነ​ት​ንም በራስ ሁሉ ላይ ላይ አመ​ጣ​ለሁ፤ እንደ ወዳጅ ልቅሶ አደ​ር​ጋ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ያሉት እንደ መከራ ቀን ይሆ​ናሉ።


ተማርከው ከአንቺ ዘንድ ወጥተዋልና ስለ ተድላሽ ልጆች ራስሽን ንጪ፥ ጠጕርሽንም ተቈረጪ፥ ቡሃነትሽንም እንደ ንስር አስፊ።


“ለሞተ ሰውም በዐ​ይ​ና​ችሁ መካ​ከል ፊታ​ች​ሁን አት​ንጩ፤ ራሳ​ች​ሁ​ንም አት​ላጩ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos