Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 48:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 በዲ​ቦን የም​ት​ኖሪ ሆይ! ሞአ​ብን የሚ​ያ​ጠፋ ወጥ​ቶ​ብ​ሻ​ልና፥ አም​ባ​ሽ​ንም ሰብ​ሮ​አ​ልና ከክ​ብ​ርሽ ውረጂ፤ በጭ​ቃም ላይ ተቀ​መጪ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 “ሞዓብን የሚያጠፋ፣ በአንቺ ላይ ይመጣልና፤ የተመሸጉ ከተሞችሽንም ያጠፋልና፤ አንቺ የዲቦን ሴት ልጅ ሆይ፤ ከክብርሽ ውረጂ፤ በደረቅም መሬት ተቀመጪ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 በዲቦን የምትኖሪ ሆይ! ሞዓብን የሚያጠፋ ወጥቶብሻልና፥ አምባሽንም ሰብሮአልና ከክብርሽ ውረጂ በደረቅም መሬት ላይ ተቀመጪ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ምሽጎችዋም ፍርስራሽ ሆነው እንዲቀሩ የሚያደርግ ሞአብን የሚደመስሳት እነሆ እዚህ ስለ አለ፥ በዲቦን ከተማ የምትኖሩ ሁሉ ከክብር ቦታችሁ ወርዳችሁ በምድር ትቢያ ላይ ተቀመጡ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 በዲቦን የምትኖሪ ሆይ፥ ሞዓብን የሚያጠፋ ወጥቶብሻልና፥ አምባሽንም ሰብሮአልና ከክብርሽ ውረጂ በጥማትም ተቀመጪ።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 48:18
13 Referencias Cruzadas  

አንቺ ድን​ግል የባ​ቢ​ሎን ልጅ ሆይ፥ ውረጂ፤ በት​ቢ​ያም ላይ ተቀ​መጪ፤ የከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሴት ልጅ ሆይ፥ ከዚህ በኋላ ለስ​ላ​ሳና ቅም​ጥል አት​ባ​ዪ​ምና ያለ ዙፋን በመ​ሬት ላይ ተቀ​መጪ።


ዘራ​ቸ​ውም ከሐ​ሴ​ቦን እስከ ዴቦን ድረስ ጠፋ፤ ሴቶ​ቻ​ቸ​ውም ደግሞ በሞ​ዓብ ላይ እሳ​ትን አነ​ደዱ።”


ለራ​ሳ​ችሁ እዘኑ፤ ጣዖ​ታ​ች​ሁና መሠ​ዊ​ያ​ችሁ ያሉ​ባት ዲቦን ትጠ​ፋ​ለ​ችና፤ ወደ​ዚ​ያም ወጥ​ታ​ችሁ በሞ​ዓብ ናባው አል​ቅሱ፤ ወዮም በሉ፤ ራስ ሁሉ በራ ይሆ​ናል፤ ክን​ድም ሁሉ ይቈ​ረ​ጣል።


በዲ​ቦን፥ በና​ባው፥ በቤ​ት​ዲ​ብ​ላ​ታ​ይም ላይ፥


ሐሴ​ቦን፥ በሜ​ሶ​ርም ያሉት ከተ​ሞች ሁሉ፥ ዲቦን፥ ባሞ​ት​በ​ዐል፥ ቤት​በ​አ​ል​ም​ዖን፥


አሁ​ንም በም​ድረ በዳ፥ በደ​ረ​ቅና በተ​ጠ​ማች መሬት ተተ​ከ​ለች።


ስለ​ዚ​ህም ሕዝቤ ወደ ምርኮ ሄዱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አላ​ወ​ቁ​ት​ምና፤ ብዙ​ዎቹ በረ​ኃ​ብና በውኃ ጥም ሞቱ፤


እር​ሱም እጅግ ተጠ​ምቶ ነበ​ርና፥ “አንተ ይህ​ችን ታላቅ ማዳን በባ​ሪ​ያህ እጅ ሰጥ​ተ​ሃል፤ አሁ​ንም በጥም እሞ​ታ​ለሁ፤ ባል​ተ​ገ​ረ​ዙ​ትም እጅ እወ​ድ​ቃ​ለሁ” ብሎ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ።


በአ​ር​ኖን ሸለቆ ዳር ካለ​ችው ከአ​ሮ​ዔር፥ በሸ​ለ​ቆ​ውም መካ​ከል ካለ​ችው ከተማ ጀምሮ የሚ​ሶር ሜዳ ሁሉ እስከ ዲቦን ድረስ፥


“አጣ​ሮት፥ ዲቦን፥ ያዜር፥ ነምራ፥ ሐሴ​ቦን፥ ኤል​ያሌ፥ ሲባማ፥ ናባው፥ ቤያን፤


ሕዝ​ቡም በዚያ ስፍራ ውኃ ተጠሙ፥ “እኛ​ንና ልጆ​ቻ​ች​ንን፥ ከብ​ቶ​ቻ​ች​ን​ንም በጥ​ማት ልት​ገ​ድል ለምን ከግ​ብፅ አወ​ጣ​ኸን?” ሲሉ በሙሴ ላይ አን​ጐ​ራ​ጐሩ።


ልጄ ሲሞት አላ​የ​ውም ብላ ቀስት ተወ​ር​ውሮ የሚ​ደ​ር​ስ​በ​ትን ያህል ርቃ በአ​ን​ጻሩ እየ​ተ​መ​ለ​ከ​ተች፥ ፊት ለፊት ተቀ​መ​ጠች፤ ቃል​ዋ​ንም አሰ​ምታ አለ​ቀ​ሰች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios