የጾባው ሀዳድዔዜር ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተ ምሥራቅ ወደሚገኙት ሶርያውያን መልእክት ላከ፤ እነርሱም የሀዳድዔዜር የሠራዊት አለቃ በሆነው በሾባክ መሪነት ወደ ሔላም መጡ።
መዝሙር 60:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ ሆይ! እስከ አሁን ጣልከን፤ ሰባበርከን፤ እስከ አሁን ተቈጣኸን፤ አሁን መልሰን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ጣልኸን፤ አንኰታኰትኸን፤ ተቈጣኸንም፤ አሁን ግን መልሰህ አብጀን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመዘምራን አለቃ፥ ለትምህርት የዳዊት ቅኔ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላኬ ሆይ፥ ልመናዬን ስማኝ፥ ጸሎቴንም አድምጠኝ። |
የጾባው ሀዳድዔዜር ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተ ምሥራቅ ወደሚገኙት ሶርያውያን መልእክት ላከ፤ እነርሱም የሀዳድዔዜር የሠራዊት አለቃ በሆነው በሾባክ መሪነት ወደ ሔላም መጡ።
ስለዚህም ዳዊት ወደ ባዓል ፈራጺም ወርዶ ፍልስጥኤማውያንን ድል ካደረገ በኋላ “እግዚአብሔር በጠላቶቼ መካከል እንደ ጐርፍ ሰባብሮ ገባ” አለ፤ ስለዚህም የዚያ ስፍራ ስም “ባዓል ፈራጺም” ተብሎ ተጠራ።
በመላው ኤዶም ብዙ የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ፤ በዚያም የሚኖሩ ሰዎች የእርሱ ተገዢዎች ሆኑ፤ እግዚአብሔር ዳዊትን በሄደበት ስፍራ ሁሉ ድልን ሰጠው።
ከዚያም በኋላ ዳዊት የሶርያ ግዛት የሆነችው የጾባ ንጉሥ የሆነውን የረሖብን ልጅ ሀዳድዔዜርን ድል አደረገ፤ ሀዳድዔዜር ድል በተመታበትም ጊዜ በላይኛው ኤፍራጥስ ወንዝ የሚገኘውን ግዛቱን ለማስመለስ በጒዞ ላይ ነበር።
አሜስያስ “የጨው ሸለቆ” እየተባለ በሚጠራው ስፍራ ዐሥር ሺህ የሚሆኑ የኤዶም ወታደሮችን ፈጀ፤ ሴላዕ ተብላ የምትጠራውንም ከተማ ይዞ “ዮቅትኤል” ብሎ ጠራት፤ እስከ አሁንም በዚሁ ስም ትጠራለች።
ቀጥሎም ንጉሥ ዳዊት በሶርያ አገር እስከ ሐማት ግዛት አጠገብ በምትገኘው በጾባ ንጉሥ በሀዳድዔዜር ላይ አደጋ ጣለ፤ ይህንንም ያደረገው ሀዳድዔዜር ከላይ በኩል በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ ያለውን ግዛት በቊጥጥሩ ሥር ለማድረግ ዘምቶ ስለ ነበር ነው፤
ዳዊት ሰሎሞንንም እንዲህ አለው፤ “ልጄ ሆይ፥ የአባትህን አምላክ እንድታውቅ፥ በሙሉ ልብና በፈቃደኛ አእምሮ እንድታገለግለው ዐደራ እልሃለሁ፤ እርሱ ሐሳባችንንና ምኞታችንን ሁሉ ያውቃል፤ ወደ እርሱ ብትቀርብ እርሱም ወደ አንተ ይቀርባል፤ ብትተወው ግን እርሱም ለዘለዓለም ይተውሃል፤
ከዚህ በኋላ አሜስያስ በወኔ ተነሣሥቶ ወታደሮቹን በመምራት ወደ ጨው ሸለቆ ሄደ፤ በዚያም ወታደሮቹ በኤዶም ሠራዊት ላይ አደጋ ጥለው ዐሥር ሺህ ወታደሮችን ገደሉ፤
የእስራኤል እረኛ፥ የዮሴፍን ልጆች እንደ መንጋ የምትመራ አምላክ ሆይ! በኪሩቤል ላይ ባለው ዙፋንህ ተቀምጠህ፥ ጸሎታችንን አድምጥ፤ ብርሃንህም ይብራ።
አንድ ጊዜ በራእይ ለታማኝ አገልጋይህ እንዲህ ብለህ ተናግረሃል፤ “አንዱን ታላቅ ጀግና ረድቼአለሁ፤ ከሕዝቤ መካከል መርጬ ዘውድን አቀዳጅቼዋለሁ።
“እኔ የይሁዳን ሕዝብ ብርቱ አደርጋለሁ፤ የእስራኤልንም ሕዝብ እታደጋለሁ፤ ስለምራራላቸውም ሁሉንም ወደ አገራቸው እመልሳለሁ፤ ከዚህ በፊት ከቶ ጥዬአቸው እንደማላውቅ ይሆናሉ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው ስለ ሆንኩ ጸሎታቸውን እሰማለሁ።
ሳሙኤል ግን “ያደረግኸው ነገር ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። ሳኦልም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ሕዝቡ ሊከዱኝ ተቃርበው ነበር፤ አንተም በቀጠርከኝ ሰዓት ሳትመጣ ቀረህ፤ ከዚህም በላይ ፍልስጥኤማውያን መጥተው በሚክማስ ተሰለፉ፤
ወሬ ነጋሪውም “እስራኤላውያን ድል ሆነው ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፤ ይህም ሽንፈት በእኛ ላይ መድረሱ እጅግ አሠቃቂ ነው፤ ከዚህም ሁሉ ጋር ልጆችህ ሖፍኒና ፊንሐስ ተገደሉ፤ የእግዚአብሔርም የቃል ኪዳን ታቦት ተማረከች” ሲል መለሰለት።