Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘካርያስ 10:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 “እኔ የይሁዳን ሕዝብ ብርቱ አደርጋለሁ፤ የእስራኤልንም ሕዝብ እታደጋለሁ፤ ስለምራራላቸውም ሁሉንም ወደ አገራቸው እመልሳለሁ፤ ከዚህ በፊት ከቶ ጥዬአቸው እንደማላውቅ ይሆናሉ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው ስለ ሆንኩ ጸሎታቸውን እሰማለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 “የይሁዳን ቤት አበረታለሁ፤ የዮሴፍንም ቤት እታደጋለሁ። ስለምራራላቸው፣ ወደ ቦታቸው እመልሳቸዋለሁ፤ እነርሱም በእኔ እንዳልተተዉ ሰዎች ይሆናሉ፤ እኔ አምላካቸው እግዚአብሔር ነኝና፣ ጸሎታቸውን እሰማለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 የይሁዳን ቤት አበረታለሁ፥ የዮሴፍንም ቤት አድናለሁ፤ ስለምራራላቸው ወደ ቦታቸው እመልሳቸዋለሁ፤ እነርሱም በእኔ እንዳልተተዉ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው ጌታ ነኝና፥ እኔም እሰማቸዋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ወድጃቸዋለሁና የይሁዳን ቤት አበረታለሁ፥ የዮሴፍንም ቤት አድናለሁ፣ አደላድላቸዋለሁም፣ እመልሳቸዋለሁ፣ እኔም አምላካቸው እግዚአብሔር ነኝና፥ እኔም እሰማቸዋለሁና እንዳልጣልኋቸው ይሆናሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ወድጃቸዋለሁና የይሁዳን ቤት አበረታለሁ፥ የዮሴፍንም ቤት አድናለሁ፥ አደላድላቸዋለሁም፥ እመልሳቸዋለሁ፥ እኔም አምላካቸው እግዚአብሔር ነኝና፥ እኔም እሰማቸዋለሁና እንዳልጣልኋቸው ይሆናሉ።

Ver Capítulo Copiar




ዘካርያስ 10:6
39 Referencias Cruzadas  

እርሱን ለመርዳትና ለማበርታት፥ እኔ ዘወትር ከእርሱ ጋር ነኝ።


በዚያን ጊዜ ጌታ በመላው ዓለም ተበታትነው ይኖሩ የነበሩትን የእስራኤልንና የይሁዳን ሕዝብ ከአራቱ ማእዘን ሰብስቦ ያመጣቸው መሆኑን ለመንግሥታት ሁሉ የሚያሳውቅበትን አርማ ከፍ አድርጎ ያቆማል።


እግዚአብሔር ለሕዝቡ ለእስራኤል እንደገና ምሕረትን ያደርጋል፤ የራሱ ወገኖችም አድርጎ ይመርጣቸዋል፤ እንደገናም በአገራቸው እንዲኖሩ ይፈቅድላቸዋል፤ መጻተኞችም እንኳ መጥተው ከእነርሱ ጋር ተስማምተው አብረው ይኖራሉ።


እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ! እኔ አምላክህ ነኝ፥ ተስፋ አትቊረጥ! እኔ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፤ ድል ነሺ በሆነ ክንዴ እደግፍሃለሁ።


ኀፍረትም ሆነ ውርደት ስለማይደርስብሽ አትፍሪ፤ በወጣትነትሽ ጊዜ የደረሰብሽን ኀፍረት ትረሺአለሽ፤ ባልዋ እንደ ሞተባት ሴት ብቸኛ ሆነሽ ያሳለፍሽውን የስድብ ዘመን አታስታውሺም።


እጅግ ከመቈጣቴ የተነሣ ለጥቂት ጊዜ ትቼሽ ነበር፤ ነገር ግን በዘለዓለማዊ ፍቅሬ እራራልሻለሁ፤ ይላል አዳኝሽ እግዚአብሔር።


እርሱ በሚነግሥበት ጊዜ የይሁዳ ሕዝብ ደኅንነት ያገኛል፤ የእስራኤልም ሕዝብ በሰላም ይኖራል፤ እርሱም ‘እግዚአብሔር ጽድቃችን’ ተብሎ ይጠራል።


እስራኤልና ይሁዳ አንድ ይሆናሉ፤ ሁለቱም በአንድነት በስተሰሜን ካለው አገር ከምርኮ ይመለሳሉ፤ ለቀድሞ አባቶቻችሁ የዘለዓለም ርስት አድርጌ ወደ ሰጠኋቸው ምድር ተመልሰው ይገባሉ።”


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤልን ልጆች ቤት መልሼ እሠራለሁ፤ ለያንዳንዱም ቤተሰብ ምሕረቴን እልካለሁ፤ የኢየሩሳሌም ከተማ እንደገና ትሠራለች፤ ቤተ መንግሥቱም በድሮ ቦታ ተመልሶ ይታነጻል።


ልጆቻቸው እንደ ቀድሞ አባቶቻቸው ተፈርተው ይኖራሉ፤ ይህም ማኅበራዊ ኑሮአቸው በፊቴ የጸና ይሆናል፤ ሲጨቊኑአቸው የነበሩትንም ሁሉ እቀጣለሁ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔ የእስራኤል ነገዶች ሁሉ አምላክ የምሆንበትና እነርሱም ሕዝቤ የሚሆኑበት ጊዜ ይመጣል፤


“እስራኤል ሆይ! እናንተ የተወደዳችሁ ልጆቼ ናችሁ፤ ከሁሉ አስበልጬ የምወዳችሁ አይደለምን? ምሕረት አደርግላችሁ ዘንድ ወደ እኔ ላቀርባችሁ እፈቅዳለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እነሆ ከእስራኤል ሕዝብና ከይሁዳ ሕዝብ ጋር አዲስ ቃል ኪዳን የምገባበት ጊዜ ይመጣል፤


ሕዝብም ሆነ እንስሳ በቊጥር እንዲበዛ አደርጋለሁ፤ ብዙ ልጆች ወልዳችሁ በቊጥር ትበዛላችሁ፤ እዚያም ጥንት በኖራችሁበት ሁኔታ ትኖራላችሁ፤ ከምንጊዜውም ይልቅ አበለጽጋችኋለሁ፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ታውቃላችሁ።


ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እስራኤላውያን ደግመው አንድ ጊዜ ይህን እንዲለምኑኝ አደርጋለሁ፤ ቊጥራቸውንም እንደ በጎች መንጋ አበዛዋለሁ።


“የሰው ልጅ ሆይ! አንድ በትር ወስደህ ‘በእርሱ ላይ ለይሁዳና ከእርሱ ጋር ለተባበሩ እስራኤላውያን’ ብለህ ጻፍ፤ ከዚያም ሌላ በትር ወስደህ በእርሱ ላይ ‘ለዮሴፍ ማለት ለኤፍሬምና ከእርሱ ጋር ለተባበሩ እስራኤላውያን’ ብለህ ጻፍ።


ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “አሁን ግን የያዕቆብ ልጆች ለሆኑት ለእስራኤል ሕዝብ ምሕረት አደርግላቸዋለሁ፤ እንደገናም አበለጽጋቸዋለሁ፤ ቅዱስ ስሜም እንዳይሰደብ እከላከላለሁ።


በዚያን ጊዜ የይሁዳና የእስራኤል ሕዝብ አንድ ይሆናሉ፤ ሁለቱንም የሚያስተዳድር አንድ መሪ ይመርጣሉ፤ እንደገናም በገዛ ምድራቸው ላይ በዕድገትና በብልጽግና ይኖራሉ፤ የኢይዝራኤልም ቀን ታላቅ ይሆናል።


ለይሁዳ ሕዝቦች ግን ፍቅር አሳያቸዋለሁ፤ እኔ አምላካቸው እግዚአብሔር አድናቸዋለሁ፤ የማድናቸውም በጦርነት ኀይል አይደለም፤ በሰይፍ፥ በቀስትና በፍላጻ ወይም በፈረስና በፈረሰኛ አይደለም።”


ጥበብ ያላቸው እነዚህን ነገሮች ይረዳሉ፤ አስተዋዮችም ያውቋቸዋል፤ የእግዚአብሔር መንገድ ትክክል ነው፤ ጻድቃን ይሄዱበታል፤ ኃጢአተኞች ግን ይሰናከሉበታል።


ሕዝቤን በምድሪቱ ላይ እመሠርታለሁ፤ እንዲበለጽጉም አደርጋቸዋለሁ፤ ‘ምሕረት አይደረግላችሁም’ የተባሉትን ምሕረት አደርግላቸዋለሁ፤ ‘ሕዝቤ አይደላችሁም’ የተባሉትንም ‘ሕዝቤ ናችሁ’ እላቸዋለሁ፤ እነርሱም ‘አንተ አምላካችን ነህ’ ይሉኛል።”


የያዕቆብ ልጆች እንደ እሳት፥ የዮሴፍ ልጆች እንደ ነበልባል፥ የዔሳውም ልጆች እንደ ገለባ ይሆናሉ፤ እሳት ገለባን እንደሚያቃጥል የያዕቆብና የዮሴፍ ልጆች የዔሳውን ልጆች ያጠፋሉ። ይህንንም የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እናንተ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሆይ! ሂዱና ጠላቶቻችሁን እንደ እህል አበራዩ! ቀንዱ ብረት፥ ሰኮናው ነሐስ እንደ ሆነ በሬ ብርቱ አደርጋችኋለሁ፤ ብዙ መንግሥታትን ትደመስሳላችሁ፤ እነርሱ በግፍ የሰበሰቡትን ሀብትና ንብረት ሁሉ ለመላው ዓለም ጌታ ለእኔ ለእግዚአብሔር አምጥታችሁ ታቀርባላችሁ።”


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በዚያ ቀን አንካሶችንና እኔ ስለ ቀጣኋቸው ተሰደው መከራ የደረሰባቸውን ሕዝቤን እሰበስባለሁ።


ስለዚህ እናቱ እርሱን እስከምትወልድበት ጊዜ ድረስ እግዚአብሔር ሕዝቡን ይተዋቸዋል፤ ከዚህ በኋላ በስደት ላይ ያሉት ወገኖቹ ተመልሰው ከወገኖቻቸው ጋር ይቀላቀላሉ።


አንበሳ በብዙ የዱር አራዊት መካከል፥ የአንበሳ ደቦልም በበግ መንጋዎች መካከል ዘለው ጉብ እያሉባቸውና እየቦጫጨቁ በሚሄዱበት ጊዜ ለአራዊቱ ምንም ረዳት አይገኝላቸውም፤ ከሞት የተረፉትንም የያዕቆብን ልጆች በብዙ ሕዝቦች መካከል እንደዚሁ ያደርጋሉ።


ኀይል ያላቸው ቢሆኑም ይህን አይተው ያፍራሉ፤ እጆቻቸውን በአፋቸው ላይ ያኖራሉ፤ ጆሮዎቻቸውንም ይደፍናሉ።


ስለዚህ ለከተማይቱ ምሕረትን ለማሳየት ወደ ኢየሩሳሌም እመለሳለሁ ቤተ መቅደሴና ከተማይቱ እንደገና ታድሰው ይሠራሉ።”


እኔ አምላካቸው አበረታቸዋለሁ እነርሱም ለቃሌ ይታዘዛሉ።” እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።


እነርሱንም ወደ እሳት እጨምራቸዋለሁ፤ ብርም በእሳት እንደሚጠራ አጠራቸዋለሁ፤ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፤ ከዚያን በኋላ ወደ እኔ ይጸልያሉ፤ እኔም እመልስላቸዋለሁ። እኔ ‘ሕዝቤ’ ብዬ እጠራቸዋለሁ፤ እነርሱም ‘እግዚአብሔር አምላካችን’ ብለው ይጠሩኛል።”


አሁን ግን ከዚህ ሕዝብ የተረፉትን እንደ ቀድሞው ጊዜ አላደርግባቸውም።


ያም ቀን ሲደርስ እረኛ በጎቹን ከአደጋ እንደሚያድን አምላካቸው እግዚአብሔር ሕዝቡን ያድናል። በዘውድ ላይ ያለ ጌጥ እንደሚያበራ፥ እነርሱም በእግዚአብሔር ምድር ያበራሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos