Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


መዝሙር 60 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም


የእግዚአብሔርን ታዳጊነት የሚገልጥ ጸሎት

1 አምላክ ሆይ! እስከ አሁን ጣልከን፤ ሰባበርከን፤ እስከ አሁን ተቈጣኸን፤ አሁን መልሰን።

2 ምድርን በማንቀጥቀጥ ሰነጣጠቅኻት፤ ስለ ተሰባበረ ፍርስራሹን ጠግን።

3 በሕዝብህ ላይ የችግር ቀን አመጣህ፤ እንድንንገዳገድ ያደረገንን የወይን ጠጅንም ሰጠኸን።

4 ከጠላት መሣሪያ ማምለጥ እንዲችሉ፥ የሚፈሩህ አይተው የሚጠነቀቁበትን ምልክት ሰጠሃቸው።

5 የምትወደው ሕዝብህ ከጒዳት እንዲድን በኀይልህ ታደገን፤ ጸሎታችንን ስማ።

6 እግዚአብሔር በመቅደሱ ሆኖ እንዲህ አለ፦ “ድል አድርጌ ሴኬምን እሸነሽናለሁ፤ የሱኮትንም ሸለቆ ለሕዝቤ አከፋፍላለሁ።

7 ገለዓድና ምናሴ የእኔ ናቸው፤ ኤፍሬም የራሴ መከላከያ ቊር ነው፤ ይሁዳም በትረ መንግሥቴ ነው።

8 ሞአብ መታጠቢያዬ ነው፤ ኤዶም የእኔ መሆኑን ለማረጋገጥ ጫማዬን አኖርበታለሁ፤ በፍልስጥኤማውያንም ላይ።”

9 ወደተመሸገችው ከተማ ማን ይወስደኛል? እስከ ኤዶምስ ማን ይመራኛል?

10 አምላክ ሆይ! አንተ ጥለኸናል፤ ከሠራዊታችንም ጋር ወደ ጦር ሜዳ መውጣት ትተሃል።

11 የሰው ርዳታ ከንቱ ነው። ስለዚህ ጠላቶቻችንን ድል እንድናደርግ አንተ እርዳን።

12 እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ እናሸንፋለን፤ እርሱ ጠላቶቻችንን ያዋርዳቸዋል።

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia
Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos