Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 60:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 አም​ላኬ ሆይ፥ ልመ​ና​ዬን ስማኝ፥ ጸሎ​ቴ​ንም አድ​ም​ጠኝ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ጣልኸን፤ አንኰታኰትኸን፤ ተቈጣኸንም፤ አሁን ግን መልሰህ አብጀን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ለመዘምራን አለቃ፥ ለትምህርት የዳዊት ቅኔ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 አምላክ ሆይ! እስከ አሁን ጣልከን፤ ሰባበርከን፤ እስከ አሁን ተቈጣኸን፤ አሁን መልሰን።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 60:1
36 Referencias Cruzadas  

አድ​ር​አ​ዛ​ርም ልኮ በካ​ላ​ማቅ ወንዝ ማዶ የነ​በ​ሩ​ትን ሶር​ያ​ው​ያን ሰበ​ሰ​ባ​ቸው፤ ወደ ኤላ​ምም መጡ፤ የአ​ድ​ር​አ​ዛ​ርም ሠራ​ዊት አለቃ ሶቤቅ በፊ​ታ​ቸው ነበረ።


ዳዊ​ትም ከላ​ይ​ኛው መጋ​ደያ መጣ፤ በዚ​ያም መታ​ቸ​ውና፥ “ውኃ እን​ደ​ሚ​ያ​ጠፋ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠላ​ቶቼን ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን በፊቴ አጠ​ፋ​ቸው” አለ። ስለ​ዚ​ህም የዚያ ስፍራ ስም “የላ​ይ​ኛው መጋ​ደያ” ተብሎ ተጠራ።


መላ​ዋን ኤዶ​ም​ያ​ስን ይጠ​ብቁ ዘንድ በኤ​ዶ​ም​ያስ ሁሉ ጭፍ​ሮ​ችን አኖረ፤ ኤዶ​ማ​ው​ያ​ንም ሁሉ ለን​ጉሥ ዳዊት ገባ​ሮች ሆኑ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዳዊ​ትን በሚ​ሄ​ድ​በት ቦታ ሁሉ ጠበ​ቀው።


ዳዊ​ትም ደግሞ እስከ ኤፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ግዛት ለማ​ስ​ፋ​ፋት በሄደ ጊዜ የሱ​ባን ንጉሥ የረ​አ​ብን ልጅ አድ​ር​አ​ዛ​ርን መታ።


እር​ሱም በጨው ሸለቆ ከኤ​ዶ​ም​ያስ ዐሥር ሺህ ሰው ገደለ፤ ሴላ​ንም በጦ​ር​ነት ወስዶ ስም​ዋን እስከ ዛሬ ድረስ “ዮቅ​ት​ኤል” ብሎ ጠራት።


ዳዊ​ትም በኤ​ፍ​ራ​ጥስ ወንዝ አጠ​ገብ የነ​በ​ረ​ውን ግዛ​ቱን ለማ​ጽ​ናት በሄደ ጊዜ ሔማ​ታ​ዊ​ውን የሱ​ባን ንጉሥ አድ​ር​አ​ዛ​ርን መታ።


“አን​ተም ልጄ ሰሎ​ሞን ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልብን ሁሉ ይመ​ረ​ም​ራ​ልና፥ የነ​ፍ​ስ​ንም አሳብ ሁሉ ያው​ቃ​ልና የአ​ባ​ቶ​ች​ህን አም​ላክ ዕወቅ፤ በፍ​ጹም ልብና በነ​ፍ​ስህ ፈቃ​ድም ተገ​ዛ​ለት፤ ብት​ፈ​ል​ገው ታገ​ኘ​ዋ​ለህ፤ ብት​ተ​ወው ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይተ​ው​ሃል።


አሜ​ስ​ያ​ስም በረታ፤ ሕዝ​ቡ​ንም ሰብ​ስቦ ወደ ጨው ሸለቆ ሄደ፤ ከሴ​ይ​ርም ልጆች ዐሥር ሺህ ገደለ።


ባለ ዕዳም ገን​ዘ​ቡን ሁሉ ይበ​ር​ብ​ረው፥ የደ​ከ​መ​በ​ት​ንም ሁሉ ባዕድ ይበ​ዝ​ብ​ዘው።


የን​ግ​ሥት ሴቶች ልጆች ለክ​ብ​ርህ ናቸው፤ በወ​ርቅ ልብስ ተጐ​ና​ጽ​ፋና ተሸ​ፋ​ፍና ንግ​ሥ​ቲቱ በቀ​ኝህ ትቆ​ማ​ለች።


አቤቱ፥ ጣል​ኸን አፈ​ረ​ስ​ኸ​ንም፤ ገረ​ፍ​ኸን፥ ይቅ​ርም አል​ኸን።


በመ​ከ​ራ​ችን ረድ​ኤ​ትን ስጠን፥ በሰ​ውም መታ​መን ከንቱ ነው።


አቤቱ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፤ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ ስም​ህ​ንም እጠ​ራ​ለሁ፤ ተአ​ም​ራ​ት​ህን ሁሉ እና​ገ​ራ​ለሁ።


የእ​ን​ባ​ች​ንን እን​ጀራ ትመ​ግ​በ​ና​ለህ፥ እን​ባ​ች​ን​ንም በስ​ፍር ታጠ​ጣ​ና​ለህ።


በፊ​ቷም መን​ገ​ድን ጠረ​ግህ፥ ሥሮ​ች​ዋ​ንም ተከ​ልህ፥ ምድ​ር​ንም ሞላች።


በረ​ዳ​ታ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይበ​ላ​ችሁ፥ ለያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ እልል በሉ።


በመ​ባቻ ቀን በታ​ወ​ቀ​ችው በዓ​ላ​ችን ቀን መለ​ከ​ትን ንፉ፤


የባ​ሪ​ያ​ህን ነፍስ ደስ አሰ​ኛት፥ ነፍ​ሴን ወደ አንተ አነ​ሣ​ለ​ሁና።


ሰውን ወደ ኀሣር አት​መ​ል​ሰው፤ የሰው ልጆች ሆይ፥ ተመ​ለሱ ትላ​ለህ፤


እኛ በቍ​ጣህ አል​ቀ​ና​ልና፥ በመ​ቅ​ሠ​ፍ​ት​ህም ደን​ግ​ጠ​ና​ልና።


በተ​ኵ​ላና በእ​ባብ ላይ ትጫ​ና​ለህ፤ አን​በ​ሳ​ው​ንና ዘን​ዶ​ውን ትረ​ግ​ጣ​ለህ።


ወድጃቸዋለሁና የይሁዳን ቤት አበረታለሁ፥ የዮሴፍንም ቤት አድናለሁ፣ አደላድላቸዋለሁም፣ እመልሳቸዋለሁ፣ እኔም አምላካቸው እግዚአብሔር ነኝና፥ እኔም እሰማቸዋለሁና እንዳልጣልኋቸው ይሆናሉ።


ሳሙ​ኤ​ልም፥ “ያደ​ረ​ግ​ኸው ምን​ድን ነው?” አለ። ሳኦ​ልም፥ “ሕዝቡ ከእኔ ተለ​ይ​ተው እንደ ተበ​ታ​ተኑ፥ አን​ተም በነ​ገ​ር​ኸኝ መሠ​ረት በቀ​ጠ​ሮው ቀን እን​ዳ​ል​መ​ጣህ፥ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ወደ ማኪ​ማስ እንደ ተሰ​በ​ሰቡ አየሁ፤


ያም ሰው መልሶ፥ “እስ​ራ​ኤል ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ፊት ሸሹ፤ ደግ​ሞም በሕ​ዝቡ ዘንድ ታላቅ ግድያ ሆኖ​አል፥ ሁለ​ቱም ልጆ​ችህ አፍ​ኒ​ንና ፊን​ሐስ ሞተ​ዋል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት ተማ​ር​ካ​ለች” አለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos