Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 90:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እግዚአብሔር ሆይ! ቊጣህ እስከ መቼ ይቈያል? እባክህ ለአገልጋዮችህ ራራ!

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እግዚአብሔር ሆይ፤ ተመለስ፤ ይህ እስከ መቼ ይሆናል? ለአገልጋዮችህም ራራላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 አቤቱ፥ ተመለስ፥ እስከ መቼስ ነው? ለአገልጋዮችህ ራራ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 በተ​ኵ​ላና በእ​ባብ ላይ ትጫ​ና​ለህ፤ አን​በ​ሳ​ው​ንና ዘን​ዶ​ውን ትረ​ግ​ጣ​ለህ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 90:13
20 Referencias Cruzadas  

እነርሱን ለማዳን ቃል ኪዳኑን ያስታውስ ነበር፤ ስለ ታላቅ ፍቅሩም ምሕረት ያደርግላቸው ነበር።


እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይፈርዳል፤ ለአገልጋዮቹም ይራራል።


ኀይል ማጣታቸውን ሲያይ፥ እግዚአብሔር ለአገልጋዮቹ ይራራል፤ ነጻም፥ ባሪያም ሳይለይ ጌታ ለሕዝቡ ይፈርዳል።


የሠራዊት አምላክ ሆይ! ፊትህን ወደ እኛ መልስ! ከሰማይ ወደ እኛ ወደ ታች ተመልከት፤ እይም፤ ይህን የወይን ግንድህን ጠብቅ!


እኛ ከጥፋት እንድንድን ምናልባት እግዚአብሔር ራርቶልን ከሚያስፈራው ቊጣው ይመለስ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?”


እግዚአብሔርም ራርቶላቸው “ይህም ደግሞ አይፈጸምም” አለኝ።


እግዚአብሔርም ራርቶላቸው “ይህ ያየኸው ነገር አይፈጸምም!” አለኝ።


“እስራኤል ሆይ! እንዴት እተውሃለሁ? እንዴትስ አሳልፌ እሰጥሃለሁ? በአዳማና በጸቦይም ያደረግኹትንስ፥ እንዴት አደርግብሃለሁ? ለአንተ ያለኝ ፍቅር ታላቅ ስለ ሆነ፥ ይህን ሁሉ ላደርግብህ አልፈቅድም!


እግዚአብሔር ሆይ! የምትሰወረው ለዘለዓለም ነውን? ቊጣህስ እንደ እሳት የሚነደው እስከ መቼ ነው?


ስለዚህ ለከተማይቱ ምሕረትን ለማሳየት ወደ ኢየሩሳሌም እመለሳለሁ ቤተ መቅደሴና ከተማይቱ እንደገና ታድሰው ይሠራሉ።”


ነገር ግን ከአገራቸው ካወጣኋቸው በኋላ እንደገና ምሕረት አደርግላቸዋለሁ፤ እያንዳንዱንም ሕዝብ ወደ ገዛ ምድሩና ወደ ገዛ አገሩ መልሼ አመጣዋለሁ።


አምላክ ሆይ! ጠላቶች በአንተ ላይ የሚሳለቁት እስከ መቼ ነው? ስምህንስ የሚዳፈሩት ያለማቋረጥ ነውን?


ስለዚህ እግዚአብሔር ከቊጣ ወደ ምሕረት ተመልሶ፥ ሊያመጣባቸው የነበረውን መቅሠፍት እንዲገታ አደረገ።


ግብጻውያን ‘እግዚአብሔር ከግብጽ ምድር መርቶ ያወጣቸው ለክፉ ነገር፥ ማለት በተራራዎች ላይ ሊገድላቸውና ፈጽሞ ሊያጠፋቸው ነው’ እያሉ መዘባበቻ እንዲያደርጉን ለምን ትፈቅዳለህ? አሁንም ከቊጣህ ወደ ምሕረት ተመለስ፤ ይህንንም ሁሉ ጥፋት በሕዝብህ ላይ አታምጣ።


የቃል ኪዳኑም ታቦት ጒዞውን ባቆመ ጊዜ “በብዙ ሺህ ወደሚቈጠሩት ወደ እስራኤላውያን ሕዝብ ተመለስ” ይል ነበር።


ከሞቱት መካከል አንድም የሚያስታውስህ የለም። በመቃብርስ ሆኖ የሚያመሰግንህ ማነው?


ይህችን አንተ የተከልካትን ተንከባክበህም ያሳደግኻትን የወይን ግንድ ጠብቃት!


አምላክ ሆይ! ለምን መንገድህን እንድንስት አደረግኸን? እንዳንፈራህስ ለምን ልባችንን አደነደንክ? ለአገልጋዮችህ፥ የአንተ ስለ ሆኑት ነገዶች ስትል እባክህ ተመለስ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios