Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 59:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 መከታችን እግዚአብሔር ሆይ! ወገኖቼ የአንተን ተበቃይነት እንዳይረሱ፥ አትግደላቸው፤ ነገር ግን በኀይልህ በትናቸው፤ አዋርዳቸውም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ጋሻችን ጌታ ሆይ፤ አትግደላቸው፤ አለዚያ ሕዝቤ ይረሳል፤ በኀይልህ አንከራትታቸው፤ ዝቅ ዝቅም አድርጋቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 የአምላኬ ቸርነቱ ይገናኘኛል አምላኬ በጠላቶቼ ላይ ያሳየኛል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 በመ​ከ​ራ​ችን ረድ​ኤ​ትን ስጠን፥ በሰ​ውም መታ​መን ከንቱ ነው።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 59:11
22 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ግን ጋሻዬ ነህ፤ ድልን በማጐናጸፍ ክብርን የምትሰጠኝ አንተ ነህ።


በእነዚያ ቀኖች ሰዎች ሞትን ይፈልጋሉ፤ ነገር ግን አያገኙትም፤ ለመሞትም ይመኛሉ፤ ነገር ግን ሞት ከእነርሱ ይሸሻል።


በዚያን ጊዜ በይሁዳ ምድር ያሉ ወደ ተራራዎች ይሽሹ፤ በከተማይቱ ውስጥ ያሉ ከዚያ ይውጡ፤ ከከተማ ውጪ ያሉትም ወደ ከተማይቱ አይግቡ።


ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘለዓለሙ ያጠፋሃል፤ ከቤትህ አስወጥቶ ያባርርሃል። ከሕያዋንም ምድር ያስወግድሃል።


በጥንቃቄ ሁሉን ተመልክተህ አሳፍራቸው፤ ክፉዎችንም ባሉበት ስፍራ አጥፋቸው።


“እግዚአብሔር በመላው ዓለም በሕዝቦች መካከል ከአንድ የምድር ዳርቻ እስከ ሌላው ድረስ ይበትንሃል፤ በዚያም አንተም ሆንክ የቀድሞ አባቶችህ ሰግዳችሁላቸው የማታውቁትን ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩትን ባዕዳን አማልክት ታመልካለህ።


እግዚአብሔር በሌሎች ሕዝቦች መካከል ይበታትናችኋል፤ እግዚአብሔር በሚያኖራችሁ በአሕዛብ መካከል ጥቂቶቻችሁ ብቻ ትተርፋላችሁ።


ዘሮቻቸውን ሁሉ በአሕዛብ መካከል እንደሚጥላቸውና በመላው ዓለም እንደሚበታትናቸው ገለጠላቸው።


ጌታችንና አምላካችን ሆይ! አንተ እንደ ፀሐይና እንደ ጋሻ ነህ፤ በቸርነትና በክብር ትጠብቀናለህ፤ ደግ ለሚሠሩ ሰዎች ማናቸውንም መልካም ነገር አትከለክላቸውም።


አምላክ ሆይ! መርጠህ የቀባኸውን ንጉሣችንን ባርከው፤ ጋሻችን ስለ ሆነም ተመልከተው።


እንደሚታረዱ በጎች አደረግኸን፤ በአሕዛብ ምድር በተንከን።


እንግዲህ በምትኖሩበት ዘመን ሁሉ ይህን በዐይናችሁ ያያችሁትን ሁሉ እንዳትረሱና ከአእምሮአችሁ እንዳይጠፋ ተጠንቀቁ። ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁም አስተምሩአቸው፤


በእናንተም ላይ ጦርነት አምጥቼ በባዕዳን አገሮች ሁሉ እበትናችኋለሁ፤ ሰይፍንም አስመዝዝባችኋለሁ፤ ምድራችሁ ሰው አልባ፥ ከተሞቻችሁም ውድማ ይሆናሉ፤


በሕይወት ያሉ ሰዎች አንድ ቀን እንደሚሞቱ ያውቃሉ፤ ሙታን ግን አንዳች ነገር አያውቁም፤ ፈጽሞ የተረሱ በመሆናቸውም ዋጋ የላቸውም።


ነገር ግን ዳዊትን የኅሊና ወቀሳ አስጨነቀው፤


እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ሆኖ ስለሚረዳኝ፥ የጠላቶቼን ውድቀት አያለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios