መዝሙር 16:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! ዕድል ፈንታዬና ጽዋዬ አንተ ነህ፤ ድርሻዬንም አስተማማኝ ታደርገዋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር የርስት ድርሻዬና ጽዋዬ ነው፤ ዕጣዬም በእጅህ ናት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ የርስቴ እድል ፈንታና ጽዋዬ ነው፥ ዕጣ ፈንታዬንም የምታጸና አንተ ነህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰኰናዬ እንዳይናወጥ አረማመዴን በመንገድህ አጽና። |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔ የምደግፈው የመረጥኩትና በእርሱም ደስ የሚለኝ አገልጋዬ ይህ ነው፤ መንፈሴ በእርሱ እንዲያድርበት አደርጋለሁ፤ እርሱ ለሕዝቦች ሁሉ ትክክለኛ ፍርድን ያመጣል።
ሕይወቱን ለሞት አሳልፎ ሰጠ፤ ከክፉ አድራጊዎችም ጋር ተቈጠረ፤ ይሁን እንጂ እርሱ የብዙዎችን ኃጢአት ተሸከመ፤ ለበደለኞችም ማለደ፤ ስለዚህ እኔ ከታላላቆቹ ጋር ድርሻ እንዲኖረውና ከኀያላን ጋር ምርኮን እንዲካፈል አደርገዋለሁ።”
የያዕቆብ አምላክ ግን እንደ እነርሱ አይደለም፤ እርሱ የሁሉ ነገር ፈጣሪ ነው። እስራኤልንም የራሱ ሕዝብ እንዲሆን መርጦታል፤ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።
እርሱ በእኛና በእናንተ፥ በሮቤልና በጋድ ሕዝቦች መካከል የዮርዳኖስን ወንዝ መለያ ድንበር አድርጎአል፤ ስለዚህ ከእግዚአብሔር ጋር ምንም ግንኙነት አይኖራችሁም’ ይሉአቸው ይሆናል ብለን በመፍራት ብቻ ነው። በዚህም ዐይነት የእናንተ ዘሮች የእኛን ዘሮች ለእግዚአብሔር እንዳይሰግዱ ይከለክሉአቸው ይሆናል።
እኛ እርሱን የሠራነው በእኛና በእናንተ ሕዝብ መካከል ምልክት ሆኖ እንዲኖር ነው፤ ይኸውም ከእኛ በኋላ ለሚነሡት ትውልዶች በተቀደሰ ድንኳኑ ፊት እግዚአብሔርን እንደምናመልክ የሚቃጠልና ሌላም መሥዋዕት፥ እንዲሁም የአንድነት መሥዋዕት ስናቀርብ ለመኖራችን ምስክር ይሆናል፤ ይኸውም የእናንተ ዘሮች የእኛን ልጆች ‘ከእግዚአብሔር ጋር ምንም ግንኙነት የላችሁም’ እንዳይሉአቸው ለማድረግ ይጠቅማል፤