Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -


መዝሙር 16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም


መዝሙር 16
የዳዊት ቅኔ በሚክታም ።

1 አምላክ ሆይ፤ መጠጊያዬ ነህና፣ በከለላህ ሰውረኝ።

2 እግዚአብሔርን፣ “አንተ ጌታዬ ነህ፤ ከአንተ በቀር በጎነት የለኝም” አልሁት።

3 በምድር ያሉ ቅዱሳን፣ ሙሉ ደስታ የማገኝባቸው ክቡራን ናቸው።

4 ሌሎችን አማልክት የሚከተሉ፣ ሐዘናቸው ይበዛል፤ እኔ ግን የደም ቍርባናቸውን አላፈስስም፤ ስማቸውንም በአፌ አልጠራም።

5 እግዚአብሔር የርስት ድርሻዬና ጽዋዬ ነው፤ ዕጣዬም በእጅህ ናት።

6 መካለያ ገመድ ባማረ ስፍራ ተጥሎልኛል፤ በርግጥም የተዋበች ርስት አግኝቻለሁ።

7 የሚመክረኝን እግዚአብሔርን እባርካለሁ፤ በሌሊት እንኳ ልቤ ቀናውን ያመላክተኛል።

8 እግዚአብሔርን ሁልጊዜ በፊቴ አድርጌአለሁ፤ እርሱ በቀኜ ስላለ አልናወጥም።

9 ስለዚህ ልቤ ደስ አለው፤ አንደበቴም ሐሤት አደረገ፤ ሥጋዬም ያለ ሥጋት ዐርፎ ይቀመጣል፤

10 በሲኦል አትተወኝምና፤ በአንተ የታመነውም መበስበስን እንዲያይ አትፈቅድም።

11 የሕይወትን መንገድ ታሳየኛለህ፤ በአንተ ዘንድ የደስታ ሙላት፣ በቀኝህም የዘላለም ፍሥሓ አለ።

መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™

የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.

በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።

The Holy Bible, New Amharic Standard Version™

Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.

Used with permission. All rights reserved worldwide. 

Biblica, Inc.
Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos