13 እግዚአብሔር ስላዳነኝ አመሰግነዋለሁ፤ የወይን ጠጅ መባም አቀርብለታለሁ።
13 የመዳንን ጽዋ አነሣለሁ፤ የእግዚአብሔርንም ስም እጠራለሁ።
13 የመድኃኒትን ጽዋ ከፍ አደርጋለሁ፥ የጌታንም ስም እጠራለሁ።
እግዚአብሔር ሆይ! ዕድል ፈንታዬና ጽዋዬ አንተ ነህ፤ ድርሻዬንም አስተማማኝ ታደርገዋለህ።
እርሱን በምጠራው ጊዜ ሁሉ ስለሚሰማኝ፥ በዘመኔ ሁሉ ወደ እርሱ እጮኻለሁ።
እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ስሙንም ጥሩ ያደረገውንም ሁሉ ለአሕዛብ ንገሩ።
የጌታን ጽዋ እየጠጣችሁ ደግሞ የአጋንንትን ጽዋ መጠጣት አትችሉም፤ የጌታ ማእድ ተካፋዮች ሆናችሁ ደግሞ የአጋንንትን ማእድ ተካፋይ መሆን አትችሉም፤
ከእንግዲህ ወዲህ ከአንተ አንርቅም፤ በሕይወት ጠብቀን፤ እኛም እናመሰግንሃለን።
እኛ እግዚአብሔርን አመስግነን የምንካፈለው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቈርሰው ኅብስት ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን?
እንዲሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን አንሥቶ ሰጣቸውና እንዲህ አላቸው፤ “ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው ደሜ የሚፈጸም አዲስ ኪዳን ነው።
በዚያን ቀን እንዲህ ትላላችሁ፦ “እግዚአብሔርን አመስግኑ! ስሙንም አክብሩ! በሕዝቦች መካከል እርሱ ያደረገውን ተናገሩ! ስለ ገናናነቱም መስክሩ!
የምስጋና መሥዋዕት አቀርብልሃለሁ፤ ወደ አንተም እጸልያለሁ።