Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘዳግም 32:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እስራኤል የእግዚአብሔር ድርሻ ነው፤ ያዕቆብም አንጡራ ሀብቱ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 የእግዚአብሔር ድርሻ የገዛ ሕዝቡ፣ ያዕቆብ የተለየ ርስቱ ነውና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ሕዝቡ የጌታ ድርሻ ነው፥ ያዕቆብም የተለየ ርስቱ ነው።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ሕዝቡ ያዕ​ቆ​ብም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዕድል ፋንታ ሆነ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም የር​ስቱ ገመድ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 የእግዚአብሔር እድል ፈንታ ሕዝቡ ነው፤ 2 ያዕቆብም የርስቱ ገምድ ነው።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 32:9
28 Referencias Cruzadas  

የያዕቆብ አምላክ ግን እንደ እነርሱ አይደለም፤ እርሱ የሁሉ ነገር ፈጣሪ ነው። እስራኤልንም የራሱ ሕዝብ እንዲሆን መርጦታል፤ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።


የያዕቆብ አምላክ ግን እንደ እነርሱ አይደለም፤ እርሱ የሁሉ ነገር ፈጣሪ ነው፤ ለራሱ የተለየ ሕዝብ እንዲሆን እስራኤልን መርጦታል፤ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።


እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! የቀድሞ አባቶቻችንን ከግብጽ ምድር ባወጣህ ጊዜ ከዓለም ሕዝብ ሁሉ መካከል እስራኤልን የራስህ ሕዝብ እንዲሆን የመረጥከው መሆኑን በአገልጋይህ በሙሴ አማካይነት ተናግረሃል።”


እነርሱ እኮ እንደ እቶን እሳት ከምታቃጥል ከግብጽ ምድር ያወጣሃቸው ሕዝብህ ናቸው።


እነርሱም ለራሴ የሠራኋቸው ሕዝቦች ስለ ሆኑ እኔን ያመሰግናሉ።”


እግዚአብሔር ያዕቆብን ለራሱ፥ የእስራኤልንም ሕዝብ የግሉ አድርጎ መረጠ።


ከበጎች እረኝነት አውጥቶም፥ የእስራኤል ንጉሥና የእግዚአብሔር ሕዝብ ጠባቂ አደረገው።


ለምን ዐይነት ተስፋ እንደ ተጠራችሁና ቅዱሳን የሚወርሱት ክቡር ርስት ምን ያኽል ብዙ እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ የልቡናችሁ ዐይን እንዲበራላችሁ እጸልያለሁ።


ምድሩ ተመልሶ ለእግዚአብሔር ሕዝብ በሚሰጥበት ጊዜ እናንተ ምንም ድርሻ አይኖራችሁም።


ሳሙኤል የወይራ ዘይት መያዣውን ቀንድ ወስዶ በሳኦል ራስ ላይ አፈሰሰው፤ ሳመውም። ከዚያም በኋላ “እግዚአብሔር በሕዝቡ በእስራኤል ላይ መሪ እንድትሆን ቀባህ፤ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ነግሠህ በዙሪያቸው ካሉ ጠላቶች ታድናቸዋለህ እግዚአብሔር በርስቱ ላይ የሾመህ ለመሆኑ ይህ ማስረጃ ነው፤


አምላክ ሆይ፥ ሕዝብህ እስኪያልፍ ድረስ፥ የተቤዠኸው ሕዝብ እስኪያልፍ ድረስ፥ ፍርሀትና ድንጋጤ ወደቀባቸው፤ በሥልጣንህ እንደ ድንጋይ ጸጥ አሉ።


እንዲህም አለ፦ “እግዚአብሔር ሆይ፥ በአንተ ዘንድ ሞገስን አግኝቼ ከሆነ ከእኛ ጋር አብረህ እንድትወጣ እለምንሃለሁ፤ ይህ ሕዝብ እልኸኛ ነው፤ ነገር ግን ኃጢአታችንንና ክፉ ሥራችንን ሁሉ ይቅር በል፤ የራስህ ሕዝብ አድርገህ ተቀበለን።”


የምነግርህን አድምጠህ ልጄንና እኔን በማጥፋት እግዚአብሔር የራሱ ካደረገው ምድር ሊያስወግደን ከሚፈልገው ሰው ታድነኛለህ ብዬ አስቤ ነው።


አምላክ ሆይ! ሕዝብህን አድን፤ የአንተ የሆኑትንም ባርክ፤ እረኛቸውም ሁን፤ ለዘለዓለምም ተንከባከባቸው።


ከጥንት ጀምሮ የመረጥከውን፥ የራስህ ወገን እንዲሆን ከባርነት የዋጀኸውን ሕዝብህን አስታውስ፤ ከዚህ በፊት መኖሪያህ ያደረግኸውን የጽዮንን ተራራ አስብ።


ስለዚህ እግዚአብሔር ሕዝቡን ተቈጣ፤ እጅግም ተጸየፋቸው።


በተቀደሰችው ምድር ይሁዳን የራሱ ርስት ያደርጋታል፤ ኢየሩሳሌምንም እንደገና ይመርጣታል።


ከዚህም ሁሉ በላይ ይህ ሕዝብ ለራስህ ወገን እንዲሆን የመረጥከውና በታላቁ ኀይልህና ብርታትህ ከግብጽ ምድር ያወጣኸው ነው።”


አምላካችን እግዚአብሔር አባቶቻችንንና እኛን ከግብጽ ባርነት አውጥቶናል፤ ያደረገውን ተአምራት ሁሉ አይተናል፤ ሕዝቦችን ሁሉ አልፈን በመጣንበት ጊዜ በሰላም ጠብቆናል፤


የእኔ ከተማ ግን ታላቅ ከተማ ናት፤ በእስራኤል ሰላም የሰፈነባትና ታማኝ ከተማ እርስዋ ናት፤ ታዲያ፥ አንተ ይህችን ከተማ ለመደምሰስ ለምን ታቅዳለህ? የእግዚአብሔር ርስት የሆነውን ነገር ለማፍረስ ትፈልጋለህን?”


እግዚአብሔር አምላኩ የሆነለትና እግዚአብሔር የራሱ አድርጎ የመረጠው ሕዝብ የተባረከ ነው!


በአንተ ከሚመኩት ወገኖችህ እንደ አንዱ ሆኜ፥ ሕዝቦችህ ሲበለጽጉ እንዳይና የወገኖችህንም ደስታ እንድካፈል አድርገኝ።


የሠራዊት አምላክም “እናንተ በግብጽ የምትኖሩ ሕዝቤ፥ የፈጠርኳችሁ አሦራውያንና የመረጥኳችሁ የእስራኤል ሕዝብ የተባረካችሁ ሁኑ” ይላቸዋል።


እግዚአብሔር እያንዳንዳቸው የት መኖር እንደሚገባቸው ወሰነ፤ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፈ ለዘለዓለም ይኖሩበታል።


የምታስገኘውን ሰብልና ሌሎችን መልካም ነገሮች ሁሉ አግኝተው እንዲደሰቱ ለም ወደ ሆነች ምድር አገባኋቸው፤ እነርሱ ግን ምድሬን አበላሹ፤ የሰጠኋቸውን አገር አረከሱ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios