መዝሙር 125 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉምየእግዚአብሔር ወገኖች ዋስትና 1 በእግዚአብሔር የሚታመኑ ሰዎች ከቶ እንደማይነቃነቅና እንደማይናወጥ እንደ ጽዮን ተራራ የጸኑ ናቸው። 2 ተራራዎች በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደ ሆኑ እንዲሁም ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም እግዚአብሔር በሕዝቡ ዙሪያ ነው። 3 ክፉዎች በጻድቃን ምድር ላይ የሚዳኙት ለብዙ ጊዜ አይደለም፤ አለበለዚያ ጻድቃንም ክፉ ማድረግን ይጀምራሉ። 4 እግዚአብሔር ሆይ! ትእዛዞችህን ለሚፈጽሙ ደጋግ ሰዎች ቸርነት አድርግላቸው። 5 ነገር ግን ክፉ አድራጊዎችን በምትቀጣበት ጊዜ የአንተን መንገድ የተዉትን ከሐዲዎችንም አብረህ ቅጣቸው። ሰላም ከእስራኤል ጋር ይሁን! |