57 እግዚአብሔር ሆይ! እኔ የምፈልገው አንተን ብቻ ነው፤ ሕግህንም ለመጠበቅ ቃል እገባለሁ።
57 እግዚአብሔር ዕድል ፈንታዬ ነው፤ ቃልህን ለመታዘዝ ቈርጫለሁ።
57 ጌታ ድርሻዬ ነው፥ ቃልህን እጠብቃለሁ አልሁ።
የእኔ አለኝታ እግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ እርሱን ብቻ ተስፋ አደርጋለሁ።
እግዚአብሔር ሆይ! ዕድል ፈንታዬና ጽዋዬ አንተ ነህ፤ ድርሻዬንም አስተማማኝ ታደርገዋለህ።
እግዚአብሔር ሆይ! እንድትረዳኝ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ! ጠባቂዬ አንተ ነህ፤ በሕያዋን ምድር ዕድል ፈንታዬ አንተ ነህ።
የያዕቆብ አምላክ ግን እንደ እነርሱ አይደለም፤ እርሱ የሁሉ ነገር ፈጣሪ ነው። እስራኤልንም የራሱ ሕዝብ እንዲሆን መርጦታል፤ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።
አእምሮዬና ጒልበቴ ሊደክሙ ይችላሉ፤ እግዚአብሔር ግን እስከ ዘለዓለም ብርታቴና አለኝታዬ ነው።
እናንተ ክፉ አድራጊዎች ከእኔ ወዲያ ራቁ፤ እኔ የአምላኬን ትእዛዞች መጠበቅ እፈልጋለሁ።
ሕዝቡም ለኢያሱ “ይህ ከቶ አይደረግም! እኛ እግዚአብሔርን እናመልካለን” አሉት።
እግዚአብሔር ሕዝቦችን እንዲሁም በምድሪቱ የሚኖሩትን አሞራውያንን ሁሉ ከፊታችን አባሮልናል፤ ስለዚህም እርሱ አምላካችን ስለ ሆነ እግዚአብሔርን እናመልካለን።”
እርሱን ማምለክ መልካም መስሎ ካልታያችሁ ግን የቀድሞ አባቶቻችሁ ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ በነበሩበት ጊዜ ያመልኩአቸው የነበሩትን ወይም አሁን በምድራቸው የምትኖሩባቸውን የአሞራውያንን አማልክት ታመልኩ እንደሆን የምታመልኩትን ዛሬውኑ ምረጡ፤ እኔና ቤተሰቤ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን።”
እውነተኛ ትእዛዞችህን ለመጠበቅ በመሐላ የገባሁትን ቃል አጸናለሁ።
መከራ በደረሰብኝ ጊዜ “ለአንተ እሰጣለሁ” ያልኩትን ስእለት አቀርብልሃለሁ።
በወንድሞቻቸው በእስራኤላውያን መካከል ርስት አይኖራቸውም፤ በሰጣቸው ተስፋ መሠረት እግዚአብሔር ርስታቸው ነው።
ትእዛዞቹን የሚጠብቁ፥ በሙሉ ልባቸውም የሚፈልጉት፥ የተባረኩ ናቸው።