ሚክያስም ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፤ “እንግዲህ እግዚአብሔር የሚለውን ስማ! እግዚአብሔር በሰማይ ባለው ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ፥ መላእክቱም ሁሉ በቀኝና በግራው ቆመው አየሁ፤
ሆሴዕ 4:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህች ምድር በሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ላይ እግዚአብሔር የሚያቀርበው ወቀሳ አለው፤ ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! እርሱ የሚልህን ሁሉ ስማ፦ “በምድሪቱ ላይ ታማኝነትና ፍቅር እግዚአብሔርንም ማወቅ ጠፍቶአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ የእስራኤል ልጆች፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ እግዚአብሔር በምድሪቱ በምትኖሩት ላይ የሚያቀርበው ክስ አለውና፤ ምክንያቱም ታማኝነት የለም፤ ፍቅርም የለም፤ እግዚአብሔርንም ማወቅ በምድሪቱ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ የእስራኤል ልጆች ሆይ! እውነትና ጽኑ ፍቅር አምላክንም ማወቅ በምድሪቱ ስለ ሌለ ጌታ በምድሪቱ ላይ ከሚኖሩ ጋር ሙግት አለውና የጌታን ቃል ስሙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ የእስራኤል ልጆች ሆይ! እውነትና ምሕረት፥ እግዚአብሔርንም ማወቅ በምድር ስለሌለ እግዚአብሔር በምድር ላይ የሚኖሩትን ይወቅሳልና የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እውነትና ምሕረት እግዚአብሔርንም ማወቅ በምድር ስለሌለ እግዚአብሔር በምድሩ ላይ ከሚኖሩ ጋር ክርክር አለውና የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። |
ሚክያስም ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፤ “እንግዲህ እግዚአብሔር የሚለውን ስማ! እግዚአብሔር በሰማይ ባለው ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ፥ መላእክቱም ሁሉ በቀኝና በግራው ቆመው አየሁ፤
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እስቲ ኑና እንወያይ ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ቢቀላ እኔ አጥቤ እንደ በረዶ ይጸዳል፤ እንደ ደም የቀላ ቢሆን እንደ ባዘቶ ይነጣል።
ስለዚህም ወዳጄ እንዲህ ይላል፦ “እናንተ የኢየሩሳሌምና የይሁዳ ሕዝብ ሆይ! በእኔና በወይን ተክል ቦታዬ መካከል ስላለው ነገር እስቲ ፍረዱ፤
ማንም ሰው ክስ ሲመሠርት ትክክለኛውን ጉዳይ ይዞ አይመጣም ወደ ፍርድ ሸንጎም ሲቀርብ ለሕግ ታማኝ ሆኖ አይደለም፤ እነርሱ ከንቱ በሆነ አቤቱታ ላይ ተመሥርተው ውሸትን ይናገራሉ፤ ተንኰልን አስበው በደልን ይፈጽማሉ።
ቃሉን የምታከብሩ እናንተ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፦ “ስለ ስሜ የሚጠሉአችሁና የሚያገሉአችሁ እንዲህ ይሉአችኋል፦ ‘እናንተ ስትደሰቱ እናይ ዘንድ እስቲ እግዚአብሔር ክብሩን ይግለጥ፤’ ኀፍረት ላይ የሚወድቁት ግን እነርሱ ራሳቸው ናቸው።
የቀድሞ አባቶቻቸውን ከግብጽ ባወጣኋቸው ጊዜ ለእኔ እንዲታዘዙ ደጋግሜ አስጠነቀቅኋቸው፤ ሕዝቡንም እስከ ዛሬው ቀን ድረስ እንኳ ከማስጠንቀቅ አልተቈጠብኩም።
‘የይሁዳ ነገሥታትና የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሁሉ እኔ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የምነግራችሁን አድምጡ፤ እነሆ በጆሮው ለሚሰማው ሰው ሁሉ የሚዘገንን መቅሠፍት አመጣለሁ።
እግዚአብሔር ሕዝቡን በሚገሥጽበት ጊዜ የሚያሰማው ድምፅ እስከ ምድር ዳርቻ ይደርሳል፤ በሕዝቦች ሁሉ ላይ ይፈርዳል፤ ክፉዎችንም በሞት ይቀጣል፤’ እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል።”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤ እኔን የማያውቁ ሞኞች ሆነዋል፤ ማስተዋል ስለ ጐደላቸው እንደ ሕፃናት የሚታለሉ ናቸው፤ ክፉ ነገር ለመሥራት የተራቀቁ ብልኆች ናቸው፤ መልካም ነገር ማድረግ ግን ከቶ አይሆንላቸውም።”
ምድር ታለቅሳለች፤ ሰማይም በጨለማ ይጋረዳል፤ ይህን እግዚአብሔር ተናግሮአል፤ ሐሳቡም አይለወጥም፤ ቊርጥ ውሳኔ አድርጎአል፤ ወደ ኋላም አይመለስም።
ከዚህ በኋላ እኔ እንደዚህ አልኩ፥ “የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ሕግ ስላላወቁ፤ እነዚህ ድኾችና ማስተዋል የጐደላቸው ሰነፎች ናቸው፤ መንገዱንም አይከተሉም።
ምድራቸው በእኔ በእስራኤል ቅዱስ ዘንድ በበደል የተሞላች ብትሆንም እንኳ እኔ የሠራዊት ጌታ አምላካቸው እስራኤልንና ይሁዳን አልረሳኋቸውም።
ይህ ሕዝብ ለእኔ ለአምላኩ የማይታዘዝና ከቅጣቱም ሥነ ሥርዓትን መማር የማይፈልግ ሆኖአል፤ በዚህ ምክንያት እውነት ጨርሳ ጠፍታለች፤ ስለ እርስዋ በአንደበቱ የሚያነሣ እንኳ የለም።”
እኔም እንዲህ አልኩ፦ “እናንተ ሴቶች፥ እግዚአብሔር የሚለውን አድምጡ፤ ቃሉንም ለመቀበል የተዘጋጃችሁ ሁኑ፤ እንዴት ማልቀስ እንደሚገባቸው ሴቶች ልጆቻችሁን አስተምሩ፤ ሙሾ የማውጣትንም ዘዴ ለወዳጆቻችሁ አስጠኑ።
እነርሱ በአንደበታቸው ሐሰት ለመናገር ዘወትር የተዘጋጁ ናቸው፤ ስለዚህም በምድሪቱ ላይ በእውነት ፈንታ ሐሰት ነግሦአል። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤ ከአንዱ ኃጢአት ወደ ሌላው ኃጢአት ይተላለፋሉ፤ የእኔንም አምላክነት ዐውቀው አላከበሩኝም።”
ከዚህም የተነሣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤን ለማጥራት እንደ ብረት እፈትናቸዋለሁ፤ ሕዝቤ ክፉ ነገር ስለ ፈጸሙ ይህን ከማድረግ በቀር ሌላ ምን አደርጋቸዋለሁ?
እግዚአብሔር በይሁዳ ሕዝብ ላይ የሚያቀርበው ወቀሳ አለው፤ የያዕቆብንም ልጆች እንደ አካሄዳቸው ይቀጣቸዋል፤ ባደረጉትም ክፉ ሥራ መጠን ዋጋቸውን ይከፍላቸዋል።
“ካህናት ሆይ! ይህን ስሙ! እናንተም የእስራኤል ሕዝብ አስተውሉ! እናንተም ንጉሣውያን ቤተሰብ ይህን አድምጡ! እነሆ ፍርድ በእናንተ ላይ መጥቶአል፤ በምጽጳ እንደ ወጥመድ፥ በታቦርም እንደ ተዘረጋ መረብ ሆናችኋል።
እናንተ ሽማግሌዎች ይህን ስሙ! በይሁዳም ምድር የምትኖሩ ሁሉ ይህን አድምጡ! ለመሆኑ ይህን የመሰለ ነገር በዘመናችሁ ወይም በቀድሞ አባቶቻችሁ ዘመን ተደርጎ ያውቃልን?
አሁንም እግዚአብሔር የሚለውን ቃል ስማ፤ አንተ ‘በእስራኤል ላይ ትንቢት አትናገር፤ የይስሐቅ ዘሮች የሆኑትንም የእስራኤልን ሕዝብ አትስበክ’ ብለህ ከልክለኸኛል።
እናንተ ተራራዎች! እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ የሚያቀርበውን ወቀሳ ስሙ! እናንተም ጠንካራ የሆናችሁ የምድር መሠረቶች! አድምጡ! እግዚአብሔር ሕዝቡን እስራኤልን ይወቅሳል ይገሥጻልም።
ሆኖም እናንተ እርሱን አላወቃችሁትም፤ እኔ ግን ዐውቀዋለሁ፤ እኔ አላውቀውም ብል እንደ እናንተ ሐሰተኛ በሆንኩ ነበር፤ እኔ ግን ዐውቀዋለሁ፤ ቃሉንም እጠብቃለሁ።
ወደ ልቡናችሁ ተመለሱ፤ ኃጢአትም አትሥሩ፤ በእናንተ መካከል አንዳንዶች እግዚአብሔርን የማያውቁ አሉ። ይህንንም የምለው እንድታፍሩ ብዬ ነው።