ወደ ሕግህም ትመልሳቸው ዘንድ አስመሰከርህባቸው፤ ነገር ግን አልሰሙህም፤ ሰውም ባደረገው ጊዜ በሕይወት የሚኖርበትን ትእዛዝህንና ፍርድህን ተላለፉ፤ ጀርባቸውን ሰጡ፤ አንገታቸውንም አደነደኑ፤ አልሰሙምም።
ኤርምያስ 7:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን በክፉ ልባቸው አሳብና እልከኝነት ሄዱ፤ ወደፊትም ሳይሆን ወደ ኋላቸው ሄዱ እንጂ አልሰሙኝም ጆሮአቸውንም አላዘነበሉም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱ ግን አልሰሙም፤ ልብ ብለው ለማድመጥም አልፈለጉም፤ ይልቁን የክፉ ልባቸውን ሐሳብ በእልኸኝነት ተከተሉ፤ ወደ ፊት በመሄድ ፈንታም ወደ ኋላቸው ተመለሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን በክፉ ልባቸው ሐሳብና እልከኝነት ሄዱ ወደፊትም ሳይሆን ወደ ኋላቸው ሄዱ እንጂ አልሰሙም ጆሮአቸውንም አላዘነበሉም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ ግን መስማት አልፈለጉም፤ ትኲረትም አልሰጡትም፤ በዚህ ፈንታ በእልኽና በክፋት የተሞላው ልባቸው የመራቸውን አደረጉ፤ ወደ ፊት ሳይሆን ወደ ኋላቸው ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን በክፉ ልባቸው አሳብና እልከኝነት ሄዱ ወደ ፊትም ሳይሆን ወደ ኋላቸው ሄዱ እንጂ አልሰሙም ጆሮአቸውንም አላዘነበሉም። |
ወደ ሕግህም ትመልሳቸው ዘንድ አስመሰከርህባቸው፤ ነገር ግን አልሰሙህም፤ ሰውም ባደረገው ጊዜ በሕይወት የሚኖርበትን ትእዛዝህንና ፍርድህን ተላለፉ፤ ጀርባቸውን ሰጡ፤ አንገታቸውንም አደነደኑ፤ አልሰሙምም።
ቃሌን ይሰሙ ዘንድ እንቢ የሚሉ፥ በክፉ ልባቸውም እልከኝነት የሚሄዱ፥ ያገለግሏቸውና ይሰግዱላቸው ዘንድ ሌሎችን አማልክት ተከትለው የሚሄዱ እነዚህ ክፉ ሕዝብ አንዳች እንደማትረባ እንደዚች መታጠቂያ ይሆናሉ።
መታጠቂያ በሰው ወገብ ላይ እንደምትጣበቅ፥ እንዲሁ ለስም፥ ለመመኪያና ለክብር ሕዝብ ይሆኑልኝ ዘንድ የእስራኤልን ቤት ሁሉ፥ የይሁዳንም ቤት ሁሉ ከእኔ ጋር አጣብቄአለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን አልሰሙም።”
አንቺ እኔን ከድተሽኛል፤ እኔንም መከተል ትተሻል፤ ይላል እግዚአብሔር፤ ወደ ኋላሽም ተመልሰሻል፤ ስለዚህ እጄን በአንቺ ላይ ዘርግቼ አጠፋሻለሁ፤ ይቅርም አልላቸውም።
እናንተም ከአባቶቻችሁ ይልቅ ክፉ አድርጋችኋል፤ እነሆም ሁላችሁ እንደ ክፉ ልባችሁ ፍላጎት ሄዳችኋል፤ እኔንም አልሰማችሁም።
እነርሱ ግን አልሰሙም፤ ጆሮአቸውንም አላዘነበሉም፤ እንዳይሰሙና ተግሣጼን እንዳይቀበሉም ከአባቶቻቸው ይልቅ አንገታቸውን አደነደኑ።”
እነርሱ ግን፥ “እንጨክናለን፤ ክዳታችንን ተከትለን እንሄዳለን፥ ሁላችንም ክፉ ልባችንን ደስ የሚያሰኛትን እናደርጋለን” አሉ።
ግንዱን፥ “አንተ አባቴ ነህ፤ ድንጋዩንም፦ አንተ ወለድኸኝ” ይላሉ፤ ፊታቸውንም ሳይሆን ጀርባቸውን ሰጡኝ፤ በመከራቸው ጊዜ ግን፥ “ተነሥተህ አድነን ይላሉ።
በጐሰቈልሽ ጊዜ ተናገርሁሽ፤ አንቺም፦ አልሰማም አልሽ፤ ከሕፃንነትሽ ጀምሮ ቃሌን አለመስማትሽ መንገድሽ ነው።
የእግዚአብሔርን ቃል ለሚያቃልሉ ሰላም ይሆንላችኋል፥ በፍላጎታቸውና በልቡናቸው ክፋት ለሚሄዱም ሁሉ፦ ክፉ ነገር አያገኛችሁም” ይላሉ።
በአምላክሽ በእግዚአብሔር ላይ እንዳመፅሽ፥ መንገድሽንም ከለመለመ ዛፍ ሁሉ በታች ለእንግዶች እንደ ዘረጋሽ፥ ቃሌንም እንዳልሰማሽ ኀጢአትሽን ብቻ ዕወቂ ይላል እግዚአብሔር።
ያንጊዜም ኢየሩሳሌምን የእግዚአብሔር ዙፋን ብለው ይጠሩአታል፤ አሕዛብም ሁሉ በእግዚአብሔር ስም ወደ ኢየሩሳሌም ይሰበሰባሉ፤ ከእንግዲህም ወዲህ ክፉውን እልከኛ ልባቸውን ተከትለው አይሄዱም።
እነርሱም ገብተው ወረሱአት፤ ነገር ግን ቃልህን አልሰሙም፤ በሕግህም አልሄዱም፤ ያደርጉም ዘንድ ካዘዝሃቸው ሁሉ ምንም አላደረጉም፤ ስለዚህ ይህን ክፉ ነገር ሁሉ አመጣህባቸው።
ፊታቸውንም ሳይሆን ጀርባቸውን ወደ እኔ መለሱ፤ እኔም በማለዳ ተነሥቼ ሳስተምራቸው ተግሣጽን ይቀበሉ ዘንድ አልሰሙም።
ደግሞም፦ እያንዳንዳችሁ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ ሥራችሁንም አሳምሩ፤ ታገለግሉአቸውም ዘንድ ሌሎችን አማልክት አትከተሉ፤ ለእናንተና ለአባቶቻችሁም በሰጠሁት ምድር ትቀመጣላችሁ እያልሁ ባሪያዎችን ነቢያትን ሁሉ ልኬባችሁ ነበር፤ እናንተ ግን ጆሮአችሁን አላዘነበላችሁም፤ እኔንም አልሰማችሁኝም።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፤ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፤ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደ ሆነች ዕወቁ፤ በእርስዋም ላይ ሂዱ፤ ለነፍሳችሁም መድኀኒትን ታገኛላችሁ፤” እነርሱ ግን፥ “አንሄድባትም” አሉ።
ነገር ግን አንገታቸውን አደነደኑ እንጂ አልሰሙኝም፤ ጆሮአቸውንም አላዘነበሉም፤ አባቶቻቸውም ከአደረጉት ይልቅ የባሰ አደረጉ።
ነገር ግን የእስራኤልን ቤት በምድረ በዳ በትእዛዜ ሂዱ አልኋቸው፤ አልሄዱምም፤ ሰው ቢያደርገው ኖሮ በሕይወት የሚኖርበትንም ሕጌን አፈረሱ፤ ሰንበታቴንም ፈጽመው አረከሱ። በዚህም ጊዜ አጠፋቸው ዘንድ ቍጣዬን በምድረ በዳ አፈስስባቸዋለሁ አልሁ።
ልጆቻቸው ግን አማረሩኝ፤ ሰው ቢያደርገው ኖሮ በሕይወት የሚኖርበትን ፍርዴን ጠብቀው አላደረጉትም፤ በሥርዐቴም አልሄዱም፤ ሰንበታቴንም አረከሱ፤ በዚህም ጊዜ፦ መዓቴን አፈስስባቸዋለሁ፤ ቍጣዬንም በምድረ በዳ እፈጽምባቸዋለሁ አልሁ።
እነርሱ ግን ዐመፁብኝ፤ ይሰሙኝም ዘንድ አልወደዱም፤ ሁሉም እያንዳንዱ ርኵሰቱን ከፊቱ አላስወገደም፤ የግብጽንም ጣዖታት አልተወም፤ በዚህም ጊዜ በግብፅ ምድር መካከል ቍጣዬን እፈጽምባቸው ዘንድ መዓቴን አፈስስባቸዋለሁ አልሁ።
ለንጉሡ ለኢያሪም እጅ መንሻ ይሆን ዘንድ አስረው ወደ አሦር ይወስዱታል፤ ኤፍሬምን እፍረት ይይዘዋል፤ እስራኤልም በምክሩ ያፍራል።
አንተን ለጥፋት፥ በእርስዋም የሚኖሩትን ለማፍዋጫ እሰጥ ዘንድ የዘንበሪን ሥርዓትና የአክዓብን ቤት ሥራ ሁሉ ጠብቃችኋል፥ በምክራቸውም ሄዳችኋል፥ የሕዝቤንም ስድብ ትሸከማላችሁ።
“የዚህንም ርግማን ቃሎች በሰማችሁ ጊዜ በልቡ ‘ይህን በልቤ ስንፍና በማድረግ ሄጃለሁና ይቅር ይለኛል’ የሚል ቢኖር የበደለኛ ፍዳ ካልበደለ ጋር እንዳይተካከል፥