Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 32:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 ፊታ​ቸ​ው​ንም ሳይ​ሆን ጀር​ባ​ቸ​ውን ወደ እኔ መለሱ፤ እኔም በማ​ለዳ ተነ​ሥቼ ሳስ​ተ​ም​ራ​ቸው ተግ​ሣ​ጽን ይቀ​በሉ ዘንድ አል​ሰ​ሙም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 ፊታቸውን ሳይሆን ጀርባቸውን ሰጡኝ፤ ደጋግሜ ባስተምራቸውም አይሰሙም፤ ተግሣጽም አይቀበሉም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 ፊታቸውንም ሳይሆን ጀርባቸውን ወደ እኔ መለሱ፤ እኔም በማለዳ ተነሥቼ ባለማቋረጥ ባስተምራቸውም እንኳ ተግሣጽን ለመቀበል አልሰሙም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 እነርሱ እኔን ትተው ሄደዋል፤ ዘወትር በመደጋገም ባስተምራቸውም አልሰሙኝም፤ ተግሣጼንም አልተቀበሉም፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 ፊታቸውንም ሳይሆን ጀርባቸውን ወደ እኔ መለሱ፥ እኔም በማለዳ ተነሥቼ ሳስተምራቸው ተግሣጽን ይቀበሉ ዘንድ አልሰሙም።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 32:33
17 Referencias Cruzadas  

አሁ​ንም ይህን ነገር ሁሉ ስላ​ደ​ረ​ጋ​ችሁ፥ ተና​ገ​ር​ኋ​ችሁ፤ ነገር ግን አል​ሰ​ማ​ች​ሁም፤ ጠራ​ኋ​ች​ሁም፤ ነገር ግን አል​መ​ለ​ሳ​ች​ሁም፤


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወደ ውስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባይ አመ​ጣኝ፤ እነ​ሆም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ መግ​ቢያ ፊት በወ​ለ​ሉና በመ​ሠ​ዊ​ያው መካ​ከል ሃያ አም​ስት የሚ​ያ​ህሉ ሰዎች ነበሩ፤ ጀር​ባ​ቸ​ውም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ፥ ፊታ​ቸ​ውም ወደ ምሥ​ራቅ ነበረ፤ እነ​ር​ሱም ወደ ምሥ​ራቅ ለፀ​ሐይ ይሰ​ግዱ ነበር።


ግን​ዱን፥ “አንተ አባቴ ነህ፤ ድን​ጋ​ዩ​ንም፦ አንተ ወለ​ድ​ኸኝ” ይላሉ፤ ፊታ​ቸ​ው​ንም ሳይ​ሆን ጀር​ባ​ቸ​ውን ሰጡኝ፤ በመ​ከ​ራ​ቸው ጊዜ ግን፥ “ተነ​ሥ​ተህ አድ​ነን ይላሉ።


በጥ​ዋ​ትም ገስ​ግሦ ዳግ​መኛ ወደ ቤተ መቅ​ደስ ገባ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ እርሱ ተሰ​በ​ሰቡ፤ እር​ሱም ተቀ​ምጦ ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው ጀመር።


ደግ​ሞም፦ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችሁ ከክፉ መን​ገ​ዳ​ችሁ ተመ​ለሱ፤ ሥራ​ች​ሁ​ንም አሳ​ምሩ፤ ታገ​ለ​ግ​ሉ​አ​ቸ​ውም ዘንድ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት አት​ከ​ተሉ፤ ለእ​ና​ን​ተና ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም በሰ​ጠ​ሁት ምድር ትቀ​መ​ጣ​ላ​ችሁ እያ​ልሁ ባሪ​ያ​ዎ​ችን ነቢ​ያ​ትን ሁሉ ልኬ​ባ​ችሁ ነበር፤ እና​ንተ ግን ጆሮ​አ​ች​ሁን አላ​ዘ​ነ​በ​ላ​ች​ሁም፤ እኔ​ንም አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ኝም።


የባ​ሪ​ያ​ዎ​ችን የነ​ቢ​ያ​ትን ቃል ትሰሙ ዘንድ በማ​ለዳ ወደ እና​ንተ ብል​ካ​ቸው አል​ሰ​ማ​ች​ሁም።


ነገር ግን በክፉ ልባ​ቸው አሳ​ብና እል​ከ​ኝ​ነት ሄዱ፤ ወደ​ፊ​ትም ሳይ​ሆን ወደ ኋላ​ቸው ሄዱ እንጂ አል​ሰ​ሙ​ኝም ጆሮ​አ​ቸ​ው​ንም አላ​ዘ​ነ​በ​ሉም።


እነርሱ ግን ደንደሳቸውን አዞሩ እንጂ መስማትን እምቢ አሉ፣ እንዳይሰሙም ጆሮአቸውን አደነቈሩ።


አብ​ዝች ብጠ​ራ​ቸው አጥ​ብ​ቀው ከፊቴ ራቁ፤ ለበ​ዓ​ሊ​ምም ይሠዉ ነበር፤ ለተ​ቀ​ረጹ ምስ​ሎ​ችም ያጥኑ ነበር።


በማ​ለ​ዳም ባሪ​ያ​ዎ​ችን ነቢ​ያ​ትን ሁሉ ላክ​ሁ​ባ​ቸው፤ የጠ​ላ​ሁ​ት​ንም ርኩስ ነገር አታ​ድ​ርጉ ብዬ ላክ​ሁ​ባ​ቸው።


በጠ​ላት ፊት እንደ በረሃ ዐውሎ ነፋስ እበ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በጥ​ፋ​ታ​ቸ​ውም ቀን ጀር​ባ​ዬን እንጂ ፊቴን አላ​ሳ​ያ​ቸ​ውም።


እር​ሱም ከም​ድር እን​ስ​ሶች ይልቅ፥ ከሰ​ማ​ይም ወፎች ይልቅ የሚ​ለ​የኝ ነው።


“የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሂድና ለይ​ሁዳ ሰዎ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለሚ​ቀ​መጡ ተና​ገር፤ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ ቃሌን ትሰሙ ዘንድ ተግ​ሣ​ጽን አት​ቀ​በ​ሉ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ዘን​ግ​ተ​ሽ​ኛ​ልና፥ ወደ ኋላ​ሽም ጥለ​ሽ​ኛ​ልና አንቺ ደግሞ ሴሰ​ኝ​ነ​ት​ሽ​ንና ኀጢ​አ​ት​ሽን ተሸ​ከሚ።”


አን​ተም፦ የአ​ም​ላ​ኩን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ያል​ሰማ፥ ተግ​ሣ​ጽ​ንም ያል​ተ​ቀ​በለ ሕዝብ ይህ ነው፤ እው​ነት ጠፍ​ቶ​አል፤ ከአ​ፋ​ቸ​ውም ተቈ​ር​ጦ​አል ትላ​ቸ​ዋ​ለህ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios