Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሆሴዕ 10:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ለን​ጉሡ ለኢ​ያ​ሪም እጅ መንሻ ይሆን ዘንድ አስ​ረው ወደ አሦር ይወ​ስ​ዱ​ታል፤ ኤፍ​ሬ​ምን እፍ​ረት ይይ​ዘ​ዋል፤ እስ​ራ​ኤ​ልም በም​ክሩ ያፍ​ራል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ለታላቁ ንጉሥ እንደ እጅ መንሻ፣ ወደ አሦር ይወሰዳል፤ ኤፍሬም ይዋረዳል፤ እስራኤልም ስለ ጣዖቱ ያፍራል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 እርሱም ደግሞ ለታላቁ ንጉሥ እጅ መንሻ እንዲሆን ወደ አሦር ተማርኮ ይወሰዳል፤ ኤፍሬምን እፍረት ይይዘዋል፥ እስራኤልም በምክሩ ያፍራል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ጣዖቱ ወደ አሦር በመወሰድ ለታላቁ ንጉሥ እጅ መንሻ ሆኖ ይቀርባል፤ እስራኤል ከተከተለው ክፉ ምክር የተነሣ ኀፍረትና ውርደት ይደርስበታል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ለንጉሡ ለኢያሪም እጅ መንሻ ይሆን ዘንድ ወደ አሦር ይማረካል፥ ኤፍሬምን እፍረት ይይዘዋል፥ እስራኤልም በምክሩ ያፍራል።

Ver Capítulo Copiar




ሆሴዕ 10:6
22 Referencias Cruzadas  

የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ስል​ም​ና​ሶር በእ​ርሱ ላይ ዘመተ፤ ሆሴ​ዕም ተገ​ዛ​ለት፤ ግብ​ርም አመ​ጣ​ለት።


የተ​ዋ​ረዱ ሰዎች ንብ​ረ​ቱን ይወ​ስ​ዳሉ፤ ምክ​ሩም ትጥ​ለ​ዋ​ለች።


በወ​ደ​ዱ​አ​ቸው ጣዖ​ታት ያፍ​ራ​ሉና፥ በፈ​ለ​ጉ​አ​ቸ​ውም የአ​ድ​ባር ዛፎች ዕፍ​ረት ይይ​ዛ​ቸ​ዋ​ልና፤


ስለ​ዚህ የፈ​ር​ዖን ኀይል እፍ​ረት፥ በግ​ብፅ መታ​መ​ንም ስድብ ይሆ​ን​ባ​ች​ኋል።


የሚ​ቃ​ወ​ሙት ሁሉም ያፍ​ራሉ፤ ይዋ​ረ​ዱ​ማል፤ አፍ​ረ​ውም ይሄ​ዳሉ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ይታ​መ​ን​ባት ከነ​በ​ረው ከቤ​ቴል እን​ዳ​ፈረ፥ እን​ዲሁ ሞአብ ከካ​ሞሽ ታፍ​ራ​ለች።


ነገር ግን በክፉ ልባ​ቸው አሳ​ብና እል​ከ​ኝ​ነት ሄዱ፤ ወደ​ፊ​ትም ሳይ​ሆን ወደ ኋላ​ቸው ሄዱ እንጂ አል​ሰ​ሙ​ኝም ጆሮ​አ​ቸ​ው​ንም አላ​ዘ​ነ​በ​ሉም።


ከአ​ሦ​ራ​ው​ያን ልጆች ጋር ፈጽ​መሽ አመ​ነ​ዘ​ርሽ፤ ከዚ​ህም ጋር ገና አል​ጠ​ገ​ብ​ሽም፤ ዝሙ​ት​ሽም አል​በ​ቃ​ሽም።


ክፉ​ውን መን​ገ​ዳ​ች​ሁ​ንና መል​ካም ያይ​ደ​ለ​ውን ሥራ​ች​ሁ​ንም ታስ​ባ​ላ​ችሁ፤ ስለ በደ​ላ​ች​ሁና ስለ ርኵ​ሰ​ታ​ች​ሁም ራሳ​ች​ሁን ትጸ​የ​ፋ​ላ​ችሁ።


አንተ በክ​ን​ፎ​ችዋ ውስጥ የነ​ፋስ መና​ወጥ ነህ፤ ከመ​ሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውም የተ​ነሣ ያፍ​ራሉ።


እንደ ብዛ​ታ​ቸው መጠን ኀጢ​አት ሠሩ​ብኝ፤ እኔም ክብ​ራ​ቸ​ውን ወደ ውር​ደት እለ​ው​ጣ​ለሁ።


ኤፍ​ሬ​ምም ደዌ​ውን አያት፤ ይሁ​ዳም ሥቃ​ዩን አያት፤ ኤፍ​ሬም ወደ አሦር ሄደ፤ ወደ ንጉ​ሡም ወደ ኢያ​ሪም መል​እ​ክ​ተ​ኛን ላከ፤ እርሱ ግን ፈጽሞ ይፈ​ው​ሳ​ችሁ ዘንድ አል​ቻ​ለም፤ ከእ​ና​ን​ተም ሕማም አል​ተ​ወ​ገ​ደም።


ይህ ደግሞ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ነው፤ ሠራ​ተኛ ሠራው፤ እር​ሱም አም​ላክ አይ​ደ​ለም፤ ሰማ​ርያ ሆይ! እን​ቦ​ሳሽ ተቅ​በ​ዝ​ብ​ዞ​አ​ልና።


አንተን ለጥፋት፥ በእርስዋም የሚኖሩትን ለማፍዋጫ እሰጥ ዘንድ የዘንበሪን ሥርዓትና የአክዓብን ቤት ሥራ ሁሉ ጠብቃችኋል፥ በምክራቸውም ሄዳችኋል፥ የሕዝቤንም ስድብ ትሸከማላችሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos