ለሕዝቤም ለእስራኤል ስፍራ አደርጋለሁ፤ እተክላቸውማለሁ፤ ብቻቸውን ይቀመጣሉ፤ ከዚያም በኋላ የሚጠራጠሩት የለም፤ እንደ ቀድሞው ዘመን የኀጢአት ልጅ መከራ አያጸናባቸውም።
ኤርምያስ 11:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለበዓልም በማጠናቸው ያስቈጡኝ ዘንድ ለራሳቸው ስለ ሠሩአት ስለ እስራኤልና ስለ ይሁዳ ቤት ክፋት የተከለሽ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ክፉን ነገር ተናግሮብሻል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስራኤልና የይሁዳ ቤት ለበኣል በማጠን ባደረጉት ክፋት ስላስቈጡኝ፣ አንቺን የተከለሽ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ክፉ ነገር ዐውጆብሻል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለበዓልም በማጠናቸው አስቈጡኝ፥ ለራሳቸው ስለ ሠሩአት ስለ እስራኤልና ስለ ይሁዳ ቤት ክፋት የተከለሽ የሠራዊት ጌታ ክፉን ነገር ተናግሮብሻል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እኔ የሠራዊት አምላክ ነኝ፤ እናንተ የይሁዳና የእስራኤል ሕዝብ እኔ እንደ ተከልኩት ዛፍ ናችሁ፤ ነገር ግን በዓል ተብሎ ለሚጠራው ጣዖት መሥዋዕት በማቅረባችሁ አስቈጣችሁኝ፤ ስለዚህ አሁን ጥፋትን አመጣባችኋለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለበኣልም በማጠናቸው ያስቈጡኝ ዘንድ ለራሳቸው ስለ ሠሩአት ስለ እስራኤልና ስለ ይሁዳ ቤት ክፋት የተከለሽ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ክፉን ነገር ተናግሮብሻል። |
ለሕዝቤም ለእስራኤል ስፍራ አደርጋለሁ፤ እተክላቸውማለሁ፤ ብቻቸውን ይቀመጣሉ፤ ከዚያም በኋላ የሚጠራጠሩት የለም፤ እንደ ቀድሞው ዘመን የኀጢአት ልጅ መከራ አያጸናባቸውም።
በይሁዳም ከተሞች ሁሉ ለሌሎች አማልክት ያጥን ዘንድ የኮረብታ መስገጃዎችን አሠራ፤ የአባቶቻቸውንም አምላክ እግዚአብሔርን አስቈጣ።
አጥር አጠርሁ፤ በዙሪያውም ቈፈርሁ፤ ድንጋዮችንም ለቅሜ አወጣሁ፤ ምርጥ የሆነውንም ወይን ተከልሁ፤ በመካከሉም ግንብ ሠራሁ፤ ደግሞም የመጥመቂያ ጕድጓድ ማስሁለት፤ ወይንንም ያፈራ ዘንድ ጠበቅሁት፤ ዳሩ ግን እሾህን አፈራ።
እግዚአብሔር ለክብሩ የተከላቸው የጽድቅ ዛፎች እንዲባሉ ለጽዮን አልቃሾች አደርግላቸው ዘንድ፥ በአመድም ፋንታ አክሊልን፥ በልቅሶም ፋንታ የደስታን ዘይት፥ በኀዘንም መንፈስ ፋንታ የምስጋናን መጐናጸፊያ እሰጣቸው ዘንድ ልኮኛል።
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ ሊያመልጡት የማይችሉትን ክፉ ነገር በዚህ ሕዝብ ላይ አመጣለሁ፤ ወደ እኔም ይጮኻሉ፤ እኔ ግን አልሰማቸውም።
ይሁዳ ሆይ! አማልክትህ እንደ ከተሞችህ ቍጥር እንዲሁ ናቸው፤ እንደ ኢየሩሳሌምም መንገዶች ቍጥር ለነውረኛ ነገር ለበዓል ታጥኑባቸው ዘንድ መሠዊያዎችን አድርጋችኋል።
አንተ ተክለሃቸዋል፤ ሥር ሰድደዋል፤ ወልደዋል አፍርተውማል፤ በአፋቸውም አንተ ቅርብ ነህ፤ ከልባቸው ግን ሩቅ ነህ።
ሕዝቤ ግን ረስተውኛል፤ ለከንቱ ነገርም አጥነዋል፤ የቀድሞውን ጐዳና ትተው ወደ ጠማማውና ወደ ሰንከልካላው መንገድ ለመሄድ በመንገዳቸው ተሰናከሉ።
ስለ እነርሱ የተናገርሁባቸው ሕዝብ ከክፋታቸው ቢመለሱ፥ እኔ አደርግባቸው ዘንድ ካሰብሁት ክፉ ነገር እጸጸታለሁ።
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ቃሌን እንዳይሰሙ አንገታቸውን አደንድነዋልና እነሆ በዚች ከተማና በመንደሮችዋ ሁሉ ላይ የተናገርሁባትን ክፉ ነገር ሁሉ አመጣለሁ።”
እኔ የተመረጠች ወይን፥ ፍጹምም እውነተኛ ዘር አድርጌ ተክዬሽ ነበር፤ አንቺ ግን ተለውጠሽ እንዴት መራራ የእንግዳ ወይን ግንድ ሆንሽ?
ዐይኔንም ለበጎነት በእነርሱ ላይ አደርጋለሁ፤ ወደዚህችም ምድር ለመልካም እመልሳቸዋለሁ፤ እሠራቸዋለሁ እንጂ አላፈርሳቸውም፤ እተክላቸዋለሁ እንጂ አልነቅላቸውም።
አሁንም መንገዳችሁንና ሥራችሁን አሳምሩ፤ የአምላካችሁንም የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ እግዚአብሔርም የተናገረባችሁን ክፉ ነገር ይተዋል።
በውኑ የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስና ሕዝቡ ሁሉ ገደሉትን? በውኑ እግዚአብሔርን አልፈሩምን? ወደ እግዚአብሔርስ አልተማለሉምን? እግዚአብሔርስ የተናገረባቸውን ክፉ ነገር አይተዉምን? እኛም በነፍሳችን ላይ ታላቅ ክፋት እናደርጋለን።”
ይችን ከተማ የሚወጉ ከለዳውያን ይመጣሉ፤ ከተማዋንም በእሳት ያነድዱአታል፤ ያስቈጡኝም ዘንድ በሰገነታቸው ላይ ለበዓል ያጠኑባቸውን፥ ለሌሎችም አማልክት የመጠጥን ቍርባን ያፈሰሱባቸውን ቤቶች ያቃጥሉአቸዋል።
የእስራኤል ልጆችና የይሁዳ ልጆች ከታናሽነታቸው ጀምሮ በፊቴ ክፉ ነገርን ብቻ አድርገዋልና፤ የእስራኤልም ልጆች እኔን በእጃቸው ሥራ ከማስቈጣት በቀር ሌላ ሥራ አላደረጉምና፥ ይላል እግዚአብሔር።
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ በተናገርኋቸው ጊዜ አልሰሙምና፥ በጠራኋቸውም ጊዜ አልመለሱልኝምና የተናገርሁባቸውን ክፉ ነገር ሁሉ በይሁዳ ላይ በኢየሩሳሌምም በሚቀመጡ ሁሉ ላይ አመጣባቸዋለሁ።”
እግዚአብሔር በዚህ ሕዝብ ላይ የተናገረው ቍጣውና መዓቱ ታላቅ ነውና ምናልባት ልመናቸው በእግዚአብሔር ፊት ትደርስ ይሆናል፤ ሁሉም ከክፉ መንገዳቸው ይመለሱ ይሆናል።”
የአዛዦችም አለቃ ኤርምያስን ወሰደው፤ እንዲህም አለው፥ “አምላክህ እግዚአብሔር ይህን ክፉ ነገር በዚህ ስፍራ ላይ ተናገረ።
እግዚአብሔርም እንደ ተናገረው አደረገ፤ እርሱን በድላችኋልና፥ ቃሉንም አልሰማችሁምና ይህ ነገር ሆነባችሁ።
አደርግባችሁ ዘንድ ከአሰብሁት ክፉ ነገር ተመልሻለሁና በዚች ምድር ብትቀመጡ እሠራችኋለሁ እንጂ አላፈርሳችሁም፥ እተክላችኋለሁ እንጂ አልነቅላችሁም።
ሰውነታችሁንም ታጠፉ ዘንድ፥ በምድርም አሕዛብ ሁሉ መካከል መረገሚያና መሰደቢያ ትሆኑ ዘንድ፥ ለመቀመጥ በገባችሁባት በግብፅ ምድር ለሌሎች አማልክት በማጠናችሁ በእጃችሁ ሥራ ለምን ታስቈጡኛላችሁ?
እንዲህ በለው፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ የሠራሁትን አፈርሳለሁ፥ የተከልሁትንም እነቅላለሁ፤ ይኸውም በምድር ሁሉ ነው።
ያስቈጡኝ ዘንድ፥ ለሰማይ ንግሥት እንጎቻ እንዲያደርጉ፥ ለሌሎችም አማልክት የመጠጥ ቍርባን እንዲያፈስሱ ልጆች እንጨት ይሰበስባሉ፤ አባቶችም እሳት ያነድዳሉ፤ ሴቶችም ዱቄት ይለውሳሉ።
ብትገድሉም፥ ብታመነዝሩም፥ ብትሰርቁም፥ በሐሰትም ብትምሉ፥ ለበአልም ብታጥኑ፥ የማታውቋቸውንም እንግዶች አማልክት ብትከተሉ ክፉ ያገኛችኋል።
እስራኤል ፍሬው የበዛለት የለመለመ ወይን ነው፤ እንደ ፍሬው ብዛት መሠዊያዉን አብዝቶአል፤ እንደ ምድሩም ማማር መጠን ሐውልቶችን ሠርተዋል።