የተገዳደርኸው፥ የሰደብኸውስ ማን ነው? ቃልህንስ ከፍ ከፍ ያደረግኸው፥ ዐይንህንም ወደ ላይ ያነሣኸው በማን ላይ ነው? በእስራኤል ቅዱስ ላይ ነው።
ኢሳይያስ 5:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ ገለባ በእሳት ፍም እንደሚቃጠል፥ በነበልባልም እንደሚበላ፥ እንዲሁ የእነርሱ ሥር የበሰበሰ ይሆናል፤ አበባቸውም እንደ ትቢያ ይበንናል፤ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ሕግ ጥለዋልና፤ የእስራኤልም ቅዱስ የተናገረውን ቃል አቃልለዋልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ የእሳት ነበልባል ገለባን እንደሚበላ፣ ድርቆሽም በእሳት ጋይቶ እንደሚጠፋ፣ የእነርሱም ሥር እንዲሁ ይበሰብሳል፤ አበባቸውም እንደ ትቢያ ይበንናል፤ የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ሕግ ንቀዋልና፤ የእስራኤል ቅዱስ የተናገረውንም ቃል አቃልለዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ የእሳት ነበልባል ገለባን እንደሚበላ፤ ድርቆሽም በእሳት ጋይቶ እንደሚጠፋ፤ የእነርሱም ሥር እንዲሁ ይበሰብሳል፤ አበባቸውም እንደ ትቢያ ይበናል፤ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ሕግ ንቀዋልና፤ የእስራኤል ቅዱስ የተናገረውንም ቃል አቃለዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል ቅዱስ የሠራዊት አምላክ ያዘዘውን ሕግና ያስተማረውን ሥርዓት ስለ አቃለሉ ገለባና ድርቆሽ በእሳት ጋይቶ እንደሚጠፋ የእነርሱም ሥር መሠረት በስብሶ ይጠፋል፤ አበባቸውም ደርቆ እንደ ትቢያ ይበናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ የእሳት ወላፈን ቃርሚያን እንደሚበላ፥ እብቅም በነበልባል ውስጥ እንደሚጠፋ፥ እንዲሁ የእነርሱ ሥር የበሰበሰ ይሆናል ቡቃያቸውም እንደ ትብያ ይበንናል፥ የሠራዊትን ጌታ የእግዚአብሔርን ሕግ ጥለዋልና፥ የእስራኤልም ቅዱስ የተናገረውን ቃል አቃልለዋልና። |
የተገዳደርኸው፥ የሰደብኸውስ ማን ነው? ቃልህንስ ከፍ ከፍ ያደረግኸው፥ ዐይንህንም ወደ ላይ ያነሣኸው በማን ላይ ነው? በእስራኤል ቅዱስ ላይ ነው።
“ነገር ግን ተመልሰው ዐመፁብህ፤ ሕግህንም ወደ ኋላቸው ጣሉት፤ ወደ አንተም ይመለሱ ዘንድ የመሰከሩባቸውን ነቢያትህን ገደሉ፤ እጅግም አስቈጡህ።
ኀይላቸውም እንደ መቃ መስዬ፥ ሥራቸውም እንደ ጠለሸት ይሆናል፤ ኃጥአንና ዐማፅያንም አብረው ይቃጠላሉ፤ እሳቱንም የሚያጠፋላቸው ያጣሉ።”
ኀጢአተኛ ወገንና ዐመፅ የተሞላበት ሕዝብ፥ የክፉዎች ዘር፥ በደለኞች ልጆች ሆይ፥ ወዮላችሁ! እግዚአብሔርን ተዋችሁት፤ የእስራኤልንም ቅዱስ አስቈጣችሁት።
ስለዚህ ምድር ትውጣቸዋለች፤ በእርስዋ የተቀመጡ በድለዋልና፤ በምድር የሚኖሩ ሰዎችም ይቸገራሉ፤ ጥቂት ሰዎችም ይቀራሉ።
አቤቱ፥ ከፍ ያለች ክንድህን አላወቁም፤ ካወቁ ግን ያፍራሉ። አላዋቆች ሰዎችን ቅንአት ያዛቸው፤ አሁንም እሳት ጠላቶችን ትበላለች።
ስለዚህ የእስራኤል ቅዱስ እንዲህ ይላል፥ “ይህችን ቃል አቃልላችኋልና፥ በሐሰትና በጠማማነት ተስፋ አድርጋችኋልና፥ አጕረምርማችኋልምና፥ በዚህም ቃል ታምናችኋልና፤
እነሆ፥ ሁሉም እንደ እብቅ እሳት ይቃጠላሉ፤ ሰውነታቸውንም ከነበልባል ኀይል አያድኑም፤ እንደ እሳትም ፍም ይሆኑብሻል፤ በላያቸውም ትቀመጫለሽ።
“እኒህ ሕዝብ በቀስታ በሚሄደው በሰሊሆም ውኃ ቍርጥ ምክርን መከሩ፤ ረአሶንንና የሮሜልዩን ልጅ ያነግሡላቸው ዘንድ ይወዳሉና።
ኀጢአት እንደ እሳት ይነድዳል፤ እሳት እንደ በላችው ደረቅ ሣር ይቃጠላል፤ እንደ ዱር ሣርም ይቃጠላል፤ በተራራዎች ዙሪያ ያለው ሁሉ አብሮ ይቃጠላል።
በእግዚአብሔር ቍጣ ምድር ሁሉ ትቃጠላለች፤ ሕዝቡም እሳት እንደሚበላው እንጨት ሆኖአል፤ ሰውም ለወንድሙ አይራራም።
ምድር ሆይ፥ ስሚ! እነሆ ቃሌን ስላልሰሙ፥ ሕጌንም ስለ ጣሉ፥ እኔንም ስለ ናቁ በዚህ ሕዝብ ላይ እንደ ሥራቸው ፍሬ፥ ክፉን ነገር አመጣባቸዋለሁ።
ጥበበኞች አፍረዋል፤ ደንግጠውማል፤ ተማርከውማል፤ እነሆ የእግዚአብሔርን ቃል ጥለዋል፤ ምን ዓይነት ጥበብ አላቸው?
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዱር ዛፎች መካከል ያለውን የወይን ግንድ እሳት ይበላው ዘንድ እንደ ሰጠሁት፥ እንዲሁ በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን አሳልፌ እሰጣለሁ።
እኔ አምላክ ነኝ እንጂ ሰው አይደለሁምና፥ በመካካልህም ቅዱሱ ነኝና እንግዲህ የቍጣዬን መቅሠፍት አላደርግም፤ ኤፍሬምንም ያጠፉት ዘንድ አልተውም፤ ወደ ከተማም አልገባም አልሁ።
ኤፍሬም ታመመ፤ ሥሩም ደረቀ፤ ከእንግዲህም ወዲህ ፍሬ አያፈራም፤ ደግሞም ቢወልዱ የተወደደውን የማኅፀናቸውን ፍሬ እገድላለሁ።
ድምፃቸውም በተራራ ላይ እንደ አሉ ሠረገሎች ድምፅ፥ ገለባውንም እንደሚበላ እንደ እሳት ነበልባል ድምፅ ነው፤ ለሰልፍም እንደ ተዘጋጀ እንደ ብዙና ብርቱ ሠራዊት ያኰበኵባሉ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የእግዚአብሔርን ሕግ አፍርሰዋልና፥ ትእዛዙንም አልጠበቁምና፥ አባቶቻቸውም የተከተሉት ከንቱ ነገር አስቶአቸዋልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የይሁዳ ኀጢአት መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስላቸውም።
እኔ ግን ቁመቱ እንደ ዝግባ ቁመት፥ ብርታቱም እንደ ወይራ ዛፍ የነበረውን አሞራዊውን ከፊታቸው አጠፋሁ፤ ፍሬውንም ከላዩ፥ ሥሩንም ከታቹ አጠፋሁ።
እነሆ፥ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድድ ቀን ይመጣል፣ ትዕቢተኞችና ኃጢአትን የሚሠሩ ሁሉ ገለባ ይሆናሉ፣ የሚመጣውም ቀን ያቃጥላቸዋል፥ ሥርንና ቅርንጫፍንም አይተውላቸውም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
“እናንተን የሚሰማ እኔን ይሰማል፤ እናንተንም እንቢ የሚል እኔን እንቢ ይላል፤ እኔንም እንቢ የሚል የላከኝን እንቢ ይላል፤ እኔንም የሚሰማ የላከኝን ይሰማል።”
መንሹ በእጁ ነው፤ የዐውድማውንም እህል ያጠራል፤ ስንዴውንም በጎተራው ይሰበስባል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥላል።”
የሚክደኝን፥ ቃሌንም የማይቀበለውን ግን የሚፈርድበት አለ፤ እኔ የተናገርሁት ቃል እርሱ በመጨረሻዪቱ ቀን ይፈርድበታል።
‘እነሆ፥ እናንተ የምታቃልሉ፥ እዩ፤ ተደነቁም፤ ያለዚያ ግን ትጠፋላችሁ፤ ማንም ቢነግራችሁ የማታምኑትን ሥራ እኔ በዘመናችሁ እሠራለሁና።’ ”
ኀጢኣት እንደ ምዋርተኝነት ናትና አምልኮተ ጣዖትም ደዌንና ኀዘንን ያመጣል። የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና እግዚአብሔር ንጉሥ እንዳትሆን ናቀህ” አለው።
ሳሙኤልም ሳኦልን፥ “የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና፥ እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንዳትሆን ንቆሃልና ከአንተ ጋር አልመለስም” አለው።