Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 8:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 “እኒህ ሕዝብ በቀ​ስታ በሚ​ሄ​ደው በሰ​ሊ​ሆም ውኃ ቍርጥ ምክ​ርን መከሩ፤ ረአ​ሶ​ን​ንና የሮ​ሜ​ል​ዩን ልጅ ያነ​ግ​ሡ​ላ​ቸው ዘንድ ይወ​ዳ​ሉና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 “ይህ ሕዝብ በጸጥታ የሚፈስሰውን የሰሊሆምን ውሆች ትቶ፣ በረአሶንና በሮሜልዩ ልጅ ተደስቷልና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 “ይህ ሕዝብ በጸጥታ የሚፈሰውን የሰሊሆምን ውሆች ትቶ፤ በረአሶንና በሮሜልዩ ልጅ ተደስቶአልና።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 “በጸጥታ የሚሄደውን የሰሊሆምን ምንጭ ውሃ ትተው በንጉሥ ረጺንና በንጉሥ ፋቁሔ ተደስተዋል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ይህ ሕዝብ በቀስታ የሚሄደውን የሰሊሆምን ውኃ ጠልቶአልና፥ ረአሶንንና የሮሜልዩንም ልጅ ወዶአልና

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 8:6
19 Referencias Cruzadas  

በሁ​ለ​ቱም አዕ​ማድ ራስ ላይ እን​ዲ​ቀ​መጡ ከፈ​ሰሰ ናስ ሁለት ጕል​ላ​ትን ሠራ፤ የአ​ን​ዱም ጕል​ላት ቁመት አም​ስት ክንድ፥ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ጕል​ላት ቁመት አም​ስት ክንድ ነበረ።


የመ​ሴ​ፋም ገዢ የኮ​ል​ሐዜ ልጅ ሰሎም የም​ን​ጩን በር አደሰ፤ ሠራው፤ ከደ​ነ​ውም፤ ሳን​ቃ​ዎ​ቹ​ንም አቆመ፤ ቍል​ፎ​ቹ​ንና መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አደ​ረገ፤ ከዳ​ዊ​ትም ከተማ እስ​ከ​ሚ​ወ​ር​ደው ደረጃ ድረስ በን​ጉሡ አት​ክ​ልት አጠ​ገብ ያለ​ውን የመ​ዋኛ ቅጥር ሠራ።


ለር​ስቱ እኛን መረ​ጠን፥ የያ​ዕ​ቆ​ብን ውበት የወ​ደደ።


እንቢ ብት​ሉና ባት​ሰ​ሙኝ ግን ሰይፍ ትበ​ላ​ች​ኋ​ለች፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፍ ይህን ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።


እነሆ፥ ኀያል ብርቱ የሆነ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ሠ​ፍት በኀ​ይል እን​ደ​ሚ​ወ​ርድ የበ​ረዶ ወጨፎ፥ እን​ደ​ሚ​ያ​ጠ​ፋም ዐውሎ ነፋስ፥ እን​ደ​ሚ​ያ​ጥ​ለ​ቀ​ል​ቅም እንደ ብዙ ውኃ ፈሳሽ በጠ​ነ​ከረ እጅ ወደ ምድር ይጥ​ላል።


ስለ​ዚህ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ እን​ዲህ ይላል፥ “ይህ​ችን ቃል አቃ​ል​ላ​ች​ኋ​ልና፥ በሐ​ሰ​ትና በጠ​ማ​ማ​ነት ተስፋ አድ​ር​ጋ​ች​ኋ​ልና፥ አጕ​ረ​ም​ር​ማ​ች​ኋ​ል​ምና፥ በዚ​ህም ቃል ታም​ና​ች​ኋ​ልና፤


ስለ​ዚህ ገለባ በእ​ሳት ፍም እን​ደ​ሚ​ቃ​ጠል፥ በነ​በ​ል​ባ​ልም እን​ደ​ሚ​በላ፥ እን​ዲሁ የእ​ነ​ርሱ ሥር የበ​ሰ​በሰ ይሆ​ናል፤ አበ​ባ​ቸ​ውም እንደ ትቢያ ይበ​ን​ናል፤ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ ጥለ​ዋ​ልና፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቅዱስ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል አቃ​ል​ለ​ዋ​ልና።


እን​ዲ​ህም በለው፥ “ተጠ​በቅ፥ ዝምም በል፤ አት​ፍራ፤ ከእ​ነ​ዚህ ከሚ​ጤሱ ሁለት የእ​ን​ጨት ጠለ​ሸ​ቶች፥ የተ​ነሣ ልብህ አይ​ደ​ን​ግጥ፤ ከተ​ቈ​ጣሁ በኋላ ይቅር እላ​ለ​ሁና።


ወደ ይሁዳ እን​ው​ጣና እን​ነ​ጋ​ገ​ራ​ቸው፤ ወደ እኛም እን​መ​ል​ሳ​ቸው፤ የጣ​ብ​ኤ​ል​ንም ልጅ እና​ን​ግ​ሥ​ባ​ቸው፤”


የኤ​ፍ​ሬ​ምም ራስ ሳም​ሮን ነው፤ የሳ​ም​ሮ​ንም ራስ የሮ​ሜ​ልዩ ልጅ ፋቁሔ ነው። ባታ​ምኑ አት​ጸ​ኑም።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደግሞ ተና​ገ​ረኝ፤ እን​ዲ​ህም አለኝ፦


ምንጭ ከዓ​ለት ይጠ​ፋ​ልን? በረ​ዶስ ከሊ​ባ​ኖስ ይጠ​ፋ​ልን? ወራጅ ውኃስ በኀ​ይ​ለኛ ነፋስ ይመ​ለ​ሳ​ልን?


ሕዝቤ ሁለት ክፉ ነገ​ሮ​ችን አድ​ር​ገ​ዋ​ልና፤ የሕ​ይ​ወት ውኃ ምንጭ እኔን ትተ​ው​ኛል፥ የተ​ነ​ደ​ሉ​ትን ውኃ​ው​ንም ይይዙ ዘንድ የማ​ይ​ች​ሉ​ትን ጕድ​ጓ​ዶች ለራ​ሳ​ቸው ቈፍ​ረ​ዋል።


አሁ​ንስ የግ​ዮ​ንን ውኃ ትጠጪ ዘንድ በግ​ብፅ መን​ገድ ምን ጉዳይ አለሽ? የወ​ን​ዞ​ች​ንም ውኃ ትጠጪ ዘንድ በአ​ሦር መን​ገድ ምን ጉዳይ አለሽ?


ወይስ እነ​ዚያ በሰ​ሊ​ሆም ግንብ ተጭኖ የገ​ደ​ላ​ቸው ዐሥራ ስም​ንቱ ሰዎች ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሰዎች ይልቅ ተለ​ይ​ተው ኀጢ​እ​ታ​ኞች ይመ​ስ​ሉ​አ​ች​ኋ​ልን?


እን​ዲ​ህም አለው፥ “ሂድና በሰ​ሊ​ሆም መጠ​መ​ቂያ ታጠብ” ትር​ጓ​ሜ​ውም የተ​ላከ ማለት ነው፤ ሄዶም ታጠ​በና እያየ ተመ​ለሰ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos