Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


ሉቃስ 7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


የመ​ስ​ፍኑ ሎሌ እንደ ዳነ

1 ለሕ​ዝ​ቡም ቃሉን ነግሮ ከፈ​ጸመ በኋላ ወደ ቅፍ​ር​ና​ሆም ገባ።

2 አንድ የመቶ አለ​ቃም ነበረ፤ አገ​ል​ጋ​ዩም ታሞ ሊሞት ቀርቦ ነበር፤ እር​ሱም በእ​ርሱ ዘንድ የተ​ወ​ደደ ነበር።

3 የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱ​ስ​ንም ነገር በሰማ ጊዜ፥ መጥቶ አገ​ል​ጋ​ዩን እን​ዲ​ያ​ድ​ን​ለት ይማ​ል​ዱት ዘንድ የአ​ይ​ሁ​ድን ሽማ​ግ​ሎች ወደ እርሱ ላከ።

4 ወደ ጌታ​ችን ወደ ኢየ​ሱ​ስም መጥ​ተው ማለ​ዱት፤ እን​ዲ​ህም አሉት፥ “ፈጥ​ነህ ውረድ፤ ይህን ልታ​ደ​ር​ግ​ለት ይገ​ባ​ዋ​ልና።

5 እርሱ ወገ​ና​ች​ንን ይወ​ዳ​ልና፤ ምኵ​ራ​ባ​ች​ን​ንም ሠር​ቶ​ል​ና​ልና።”

6 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ሄደ፤ ወደ ቤቱም በቀ​ረበ ጊዜ፥ የመቶ አለ​ቃዉ ወዳ​ጆ​ቹን እን​ዲህ ብሎ ላከ፥ “አቤቱ፥ አት​ድ​ከም፤ ከቤቴ ጣራ በታች ልት​ገባ አይ​ገ​ባ​ኝ​ምና።

7 እኔም ወደ አንተ ልመጣ አይ​ገ​ባ​ኝም፤ ነገር ግን በቃ​ልህ እዘዝ፤ ብላ​ቴ​ና​ዬም ይድ​ናል።

8 እኔም እኮ ገዢ ሰው ነኝ፤ ወታ​ደ​ሮ​ችም አሉኝ፤ አን​ዱን ሂድ ብለው ይሄ​ዳል፤ ሌላ​ው​ንም ና ብለው ይመ​ጣል፤ አገ​ል​ጋ​ዬ​ንም እን​ዲህ አድ​ርግ ብለው ያደ​ር​ጋል።”

9 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ይህን ከእ​ርሱ በሰማ ጊዜ አደ​ነ​ቀው፤ ዘወር ብሎም ይከ​ተ​ሉት ለነ​በ​ሩት ሕዝብ፥ “እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልስ እንኳ እን​ዲህ ያለ እም​ነት ያለው ሰው አላ​ገ​ኘ​ሁም” አላ​ቸው።

10 የተ​ላ​ኩ​ትም በተ​መ​ለሱ ጊዜ ብላ​ቴ​ና​ውን ድኖ አገ​ኙት።


ስለ መበ​ለ​ቲቱ ልጅ መዳን

11 በማ​ግ​ሥ​ቱም ናይን ወደ​ም​ት​ባል ወደ አን​ዲት ከተማ ሄደ፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ብዙ ሕዝ​ብም አብ​ረ​ውት ሄዱ።

12 ወደ ከተ​ማው በር በደ​ረሰ ጊዜም እነሆ፥ ያን​ዲት መበ​ለት ሴት ልጅ ሙቶ ሬሳ​ውን ተሸ​ክ​መው ሲሄዱ አገኘ፤ ይኸ​ውም ለእ​ናቱ አንድ ነበረ፤ ብዙ​ዎ​ችም የከ​ተማ ሰዎች አብ​ረ​ዋት ነበሩ።

13 ጌታ​ች​ንም በአ​ያት ጊዜ አዘ​ነ​ላ​ትና፥ “አታ​ል​ቅሺ” አላት።

14 ቀር​ቦም ቃሬ​ዛ​ውን ያዘ፤ የተ​ሸ​ከ​ሙ​ትም ቆሙ፤ እር​ሱም፥ “አንተ ጐበዝ ተነሥ እል​ሃ​ለሁ” አለው።

15 የሞ​ተ​ውም ተነ​ሥቶ ተቀ​መጠ፤ መና​ገ​ርም ጀመረ፤ ለእ​ና​ቱም ሰጣት።

16 ሁሉም ፈሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አመ​ሰ​ገኑ፤ እን​ዲ​ህም አሉ፥ “ታላቅ ነቢይ ተነ​ሣ​ልን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን ጐብ​ኝ​ቶ​አ​ልና።”

17 ይህም የእ​ርሱ ዜና በይ​ሁዳ ሀገ​ሮች ሁሉና በአ​ው​ራ​ጃዋ ሁሉ ተሰማ።


ከዮ​ሐ​ንስ ስለ ተላ​ኩት መል​እ​ክ​ተ​ኞች

18 ይህ​ንም ሁሉ ደቀ መዝ​ሙ​ርቱ ለዮ​ሐ​ንስ ነገ​ሩት።

19 ዮሐ​ን​ስም ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ሁለ​ቱን ጠርቶ፥ “የሚ​መ​ጣው አንተ ነህን? ወይስ ተስፋ የም​ና​ደ​ር​ገው ሌላ አለ?” ብሎ ወደ ጌታ​ችን ወደ ኢየ​ሱስ ላካ​ቸው።

20 መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችም ወደ እርሱ ደር​ሰው፥ “የሚ​መ​ጣው አንተ ነህን? ወይስ ተስፋ የም​ና​ደ​ር​ገው ሌላ አለ? ብሎ መጥ​ምቁ ዮሐ​ንስ ወደ አንተ ልኮ​ናል” አሉት።

21 ያን​ጊ​ዜም ብዙ​ዎ​ችን ከደ​ዌ​አ​ቸ​ውና ከሕ​መ​ማ​ቸው ከክ​ፉ​ዎች አጋ​ን​ን​ትም ፈወ​ሳ​ቸው፤ ለብ​ዙ​ዎች ዕው​ራ​ንም እን​ዲ​ያዩ ብር​ሃ​ንን ሰጣ​ቸው።

22 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሄዳ​ችሁ ያያ​ች​ሁ​ት​ንና የሰ​ማ​ች​ሁ​ትን ለዮ​ሐ​ንስ ንገ​ሩት፤ ዕው​ሮች ያያሉ፤ አን​ካ​ሶ​ችም ይሄ​ዳሉ፤ ለም​ጻ​ሞ​ችም ይነ​ጻሉ፤ ደን​ቆ​ሮ​ችም ይሰ​ማሉ፤ ሙታ​ንም ይነ​ሣሉ፤ ለድ​ሆ​ችም ወን​ጌል ይሰ​በ​ካል።

23 በእ​ኔም የማ​ይ​ሰ​ና​ከል ብፁዕ ነው።”


ጌታ መጥ​ምቁ ዮሐ​ን​ስን ስለ ማመ​ስ​ገኑ

24 የዮ​ሐ​ንስ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትም ከሄዱ በኋላ ለሕ​ዝቡ ስለ መጥ​ምቁ ዮሐ​ንስ እን​ዲህ ይላ​ቸው ጀመር፥ “ምን ልታዩ ወደ ምድረ በዳ ወጣ​ችሁ? ከነ​ፋስ የተ​ነሣ የሚ​ወ​ዛ​ወዝ ሸን​በ​ቆን ነውን?

25 ወይስ ምን ልታዩ ወጥ​ታ​ች​ኋል? ቀጭን ልብስ የለ​በ​ሰ​ውን ሰው ነውን? እነሆ፥ በክ​ብር ልብስ ያጌ​ጡስ በነ​ገ​ሥ​ታት ቤት አሉ።

26 ወይስ ምን ልታዩ ወጥ​ታ​ች​ኋል? ነቢ​ይን ነውን? አዎን፥ እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከነ​ቢ​ይም ይበ​ል​ጣል።

27 እነሆ፥ መን​ገ​ድ​ህን በፊ​ትህ የሚ​ጠ​ርግ መል​እ​ክ​ተ​ኛ​ዬን በፊ​ትህ እል​ካ​ለሁ፥ ተብሎ ስለ እርሱ የተ​ጻ​ፈ​ለት ይህ ነው።

28 እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ሴቶች ከወ​ለ​ዱ​አ​ቸው መካ​ከል ከመ​ጥ​ምቁ ዮሐ​ንስ የሚ​በ​ልጥ ማንም አል​ተ​ነ​ሣም፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ግን የሚ​ያ​ን​ሰው ይበ​ል​ጠ​ዋል።”

29 ሕዝ​ቡም ሁሉ ቀራ​ጮ​ችም በሰሙ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጻድቅ ነው አሉት፤ የዮ​ሐ​ን​ስን ጥም​ቀት ተጠ​ም​ቀው ነበ​ርና።

30 ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንና የሕግ ጻፎች ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ተቃ​ወሙ፤ በእ​ርሱ አል​ተ​ጠ​መ​ቁ​ምና።

31 “እን​ግ​ዲህ የዚ​ችን ትው​ልድ ሰዎች በምን እመ​ስ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ? ማን​ንስ ይመ​ስ​ላሉ?

32 በገ​በያ ተቀ​ም​ጠው ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ጠር​ተው፥ “አቀ​ነ​ቀ​ን​ላ​ችሁ፥ አል​ዘ​ፈ​ና​ች​ሁ​ምም፤ ሙሾም አወ​ጣ​ን​ላ​ችሁ፥ አላ​ለ​ቀ​ሳ​ች​ሁ​ምም የሚ​ሉ​አ​ቸው ልጆ​ችን ይመ​ስ​ላሉ።

33 መጥ​ምቁ ዮሐ​ንስ እህል ሳይ​በላ ወይ​ንም ሳይ​ጠጣ መጥቶ ነበ​ርና ጋኔን አለ​በት አላ​ች​ሁት።

34 የሰው ልጅም እየ​በ​ላና እየ​ጠጣ መጣ፤ እና​ንተ ግን እነሆ፥ በላ​ተ​ኛና ወይን ጠጪ ሰው፥ የኃ​ጥ​ኣ​ንና የቀ​ራ​ጮች ወዳጅ አላ​ች​ሁት።

35 ጥበ​ብም ከል​ጆ​ችዋ ሁሉ ጸደ​ቀች።”


ስለ ፈሪ​ሳ​ዊ​ውና ስለ ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ዪቱ ሴት

36 ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያ​ንም አንዱ በእ​ርሱ ዘንድ ምሳ እን​ዲ​በላ ለመ​ነው፤ ወደ ፈሪ​ሳ​ዊ​ውም ቤት ገብቶ በማ​ዕድ ተቀ​መጠ።

37 እነሆ፥ ከዚ​ያች ከተማ ሰዎ​ችም አን​ዲት ኀጢ​አ​ተኛ ሴት በፈ​ሪ​ሳ​ዊው ቤት በማ​ዕድ እን​ደ​ተ​ቀ​መጠ ዐውቃ ሽቱ የሞ​ላ​በት የአ​ል​ባ​ስ​ጥ​ሮስ ቢል​ቃጥ ገዝታ መጣች።

38 በስ​ተ​ኋ​ላ​ውም በእ​ግ​ሮቹ አጠ​ገብ ቆማ አለ​ቀ​ሰች፤ እግ​ሮ​ቹ​ንም በእ​ን​ባዋ ታርስ ነበር፥ በራስ ጠጕ​ር​ዋም እግ​ሮ​ቹን ታብ​ሰ​ውና ትስ​መው፥ ሽቱም ትቀ​ባው ነበር።

39 የጠ​ራው ፈሪ​ሳ​ዊም ባየ ጊዜ በልቡ ዐሰበ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ይህስ ነቢይ ቢሆን ኖሮ ይህቺ የም​ት​ዳ​ስ​ሰው ሴት ማን እንደ ሆነች፥ እን​ዴ​ትስ እንደ ነበ​ረች ባላ​ወ​ቀም ነበ​ርን? ኀጢ​አ​ተኛ ናትና።”

40 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “ስም​ዖን ሆይ፥ የም​ነ​ግ​ርህ ነገር አለኝ” አለው፤ እር​ሱም፥ “መም​ህር ሆይ፥ ተና​ገር” አለው።

41 እር​ሱም እን​ዲህ አለው፥ “ለአ​ንድ አበ​ዳሪ ሁለት ባለ ዕዳ​ዎች ነበ​ሩት፤ በአ​ንዱ አም​ስት መቶ ዲናር ነበ​ረ​በት፤ በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም አምሳ።

42 የሚ​ከ​ፍ​ሉ​ትም ባጡ ጊዜ ለሁ​ለ​ቱም ተወ​ላ​ቸው፤ እን​ግ​ዲህ ከሁ​ለቱ አብ​ልጦ ሊወ​ደው የሚ​ገ​ባው ማን​ኛው ነው?”

43 ስም​ዖ​ንም መልሶ፥ “ብዙ​ውን የተ​ወ​ለት ነው እላ​ለሁ” አለው፤ እር​ሱም፥ “መል​ካም ፈረ​ድህ” አለው።

44 ወደ ሴቲ​ቱም ዘወር ብሎ ስም​ዖ​ንን እን​ዲህ አለው፥ “ይህ​ቺን ሴት ታያ​ታ​ለ​ህን? እኔ ወደ ቤትህ ገባሁ፤ ለእ​ግ​ሮች ውኃ ስንኳ አል​ሰ​ጠ​ኸ​ኝም፤ እር​ስዋ ግን አል​ቅሳ በእ​ን​ባዋ እግ​ሬን አራ​ሰች፤ በጠ​ጕ​ር​ዋም አበ​ሰች።

45 አን​ተስ ሰላ​ምታ አል​ሰ​ጠ​ኸ​ኝም፤ እር​ስዋ ግን ከገ​ባሁ ጀምሮ እግ​ሬን ከመ​ሳም አላ​ቋ​ረ​ጠ​ችም።

46 አንተ ራሴን እንኳ ዘይት አል​ቀ​ባ​ኸ​ኝም፤ እር​ስዋ ግን እግ​ሬን ሽቱ ቀባ​ችኝ።

47 ስለ​ዚ​ህም እል​ሃ​ለሁ፤ ብዙ ኀጢ​ኣቷ ተሰ​ር​ዮ​ላ​ታል፤ በብዙ ወድ​ዳ​ለ​ችና፤ ጥቂት የሚ​ወ​ድድ ጥቂት ይሰ​ረ​ይ​ለ​ታል፤ ብዙ የሚ​ወ​ድ​ድም ብዙ ይሰ​ረ​ይ​ለ​ታል።”

48 ሴቲ​ቱ​ንም፥ “ኀጢ​ኣ​ትሽ ተሰ​ረ​የ​ልሽ” አላት።

49 በማ​ዕዱ የተ​ቀ​መ​ጡ​ትም እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “ኀጢ​አ​ትን የሚ​ያ​ስ​ተ​ሰ​ርይ ይህ ማነው?” ይሉ ጀመር።

50 ሴቲ​ቱ​ንም አላት፥ “እም​ነ​ትሽ አድ​ኖ​ሻል፤ በሰ​ላም ሂጂ።”

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos