Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 15:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 በክ​ብ​ር​ህም ብዛት ጠላ​ቶ​ች​ህን አጠ​ፋህ፤ ቍጣ​ህን ሰደ​ድህ፤ እንደ ገለ​ባም በላ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 “በግርማህ ታላቅነት፣ የተቃወሙህን ጣልሃቸው፤ ቍጣህን ሰደድህ፤ እንደ ገለባም በላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 የግርማህ ታላቅነት አንተን በመቃወም የተነሱብህን ጣላቸው፤ ቁጣህን ሰደድህ፥ እንደ ገለባም በላቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ግርማ በተሞላው ድል አድራጊነትህ ጠላትህን ገለበጥህ፤ ቊጣህ እንደ እሳት ስለ ነደደ እንደ ገለባ በላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 በክብርህም ብዛት የተነሡብህን አጠፋህ፤ ቍጣህን ሰድደህ፤ እንደ ገለባም በላቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 15:7
29 Referencias Cruzadas  

ስለ​ዚህ ገለባ በእ​ሳት ፍም እን​ደ​ሚ​ቃ​ጠል፥ በነ​በ​ል​ባ​ልም እን​ደ​ሚ​በላ፥ እን​ዲሁ የእ​ነ​ርሱ ሥር የበ​ሰ​በሰ ይሆ​ናል፤ አበ​ባ​ቸ​ውም እንደ ትቢያ ይበ​ን​ናል፤ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ ጥለ​ዋ​ልና፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቅዱስ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል አቃ​ል​ለ​ዋ​ልና።


እነሆ፥ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድድ ቀን ይመጣል፣ ትዕቢተኞችና ኃጢአትን የሚሠሩ ሁሉ ገለባ ይሆናሉ፣ የሚመጣውም ቀን ያቃጥላቸዋል፥ ሥርንና ቅርንጫፍንም አይተውላቸውም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


እነሆ፥ ሁሉም እንደ እብቅ እሳት ይቃ​ጠ​ላሉ፤ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ው​ንም ከነ​በ​ል​ባል ኀይል አያ​ድ​ኑም፤ እንደ እሳ​ትም ፍም ይሆ​ኑ​ብ​ሻል፤ በላ​ያ​ቸ​ውም ትቀ​መ​ጫ​ለሽ።


የተ​ቈ​ጣ​ኸው ቍጣና ትዕ​ቢ​ትህ ወደ ጆሮዬ ደር​ሶ​አ​ልና ሰለ​ዚህ ስና​ጋ​ዬን በአ​ፍ​ን​ጫህ፥ ልጓ​ሜ​ንም በከ​ን​ፈ​ርህ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ በመ​ጣ​ህ​በ​ትም መን​ገድ እመ​ል​ስ​ሃ​ለሁ።


የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን በፍ​ርድ ከፍ ከፍ ይላል፤ ቅዱ​ሱም አም​ላክ በጽ​ድቅ ይከ​ብ​ራል።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም ያመ​ሰ​ግ​ናሉ። ስሙ ብቻ​ውን ከፍ ከፍ ብሎ​አ​ልና፥ በሰ​ማ​ይና በም​ድር ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል።


እንደ ፍቁሩ አም​ላክ ማንም የለም፤ በሰ​ማይ የሚ​ኖ​ረው፥ በጠ​ፈ​ርም በታ​ላ​ቅ​ነት ያለው እርሱ ረዳ​ትህ ነው።


በም​ድር ላይም ወደቀ፤ ወዲ​ያ​ውም፥ “ሳውል፥ ሳውል፥ ለምን ታሳ​ድ​ደ​ኛ​ለህ?” የሚ​ለ​ውን ቃል ሰማ።


መንሹም በእጁ ነው፤ አውድማውንም ፈጽሞ ያጠራል፤ ስንዴውንም በጎተራው ይከታል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።”


በዚያም ቀን የሕይወት ውኃ ከኢየሩሳሌም ይወጣል፣ እኵሌታው ወደ ምሥራቁ ባሕር፥ እኵሌታውም ወደ ምዕራቡ ባሕር ይሄዳል፣ ይህ በበጋና በክረምት ይሆናል።


እግዚአብሔርም ይወጣል፥ በሰልፍም ቀን እንደ ተዋጋ ከእነዚያ አሕዛብ ጋር ይዋጋል።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ከክብሩ በኋላ ወደ በዘበዙአችሁ አሕዛብ ልኮኛል፣ የሚነካችሁ የዓይኑን ብሌን የሚነካ ነውና።


አሁንም፦ ርኩስ ትሁን፥ ዓይናችንም በጽዮን ላይ ይይ የሚሉ ብዙ አሕዛብ በአንቺ ላይ ተሰብስበዋል።


አቤቱ! እንደ አንተ ያለ የለም፤ አንተ ታላቅ ነህ ስም​ህም በኀ​ይል ታላቅ ነው።


በአ​ም​ላ​ኩም በና​ሳ​ራክ ቤት ሲሰ​ግድ ልጆቹ አድ​ራ​ሜ​ሌ​ክና ሳራ​ሳር በሰ​ይፍ ገደ​ሉት፤ ወደ አራ​ራ​ትም ሀገር ኰበ​ለሉ። ልጁም አስ​ራ​ዶን በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ወጣ፤ ከአ​ሦ​ራ​ው​ያ​ንም ሰፈር መቶ ሰማ​ንያ አም​ስት ሺህ ሰዎ​ችን ገደለ፤ ማለ​ዳም በተ​ነሡ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሁሉም በድ​ኖች ሆነው አገ​ኙ​አ​ቸው።


የተ​ገ​ዳ​ደ​ር​ኸው፥ የሰ​ደ​ብ​ኸ​ውስ ማንን ነው? ቃል​ህ​ንስ ከፍ ከፍ ያደ​ረ​ግ​ህ​በት፥ ዐይ​ን​ህ​ንስ ወደ ላይ ያነ​ሣ​ህ​በት ማን ነው? በእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ላይ አይ​ደ​ለ​ምን?


አቤቱ፥ ጆሮ​ህን አዘ​ን​ብ​ልና ስማ፤ አቤቱ፥ ዐይ​ን​ህን ክፈ​ትና በሕ​ያው አም​ላክ ላይ ይገ​ዳ​ደር ዘንድ የላ​ከ​ውን የሰ​ና​ክ​ሬ​ምን ቃል ተመ​ል​ከት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ድሆ​ችን ሰም​ቶ​እ​ቸ​ዋ​ልና፥ እስ​ረ​ኞ​ች​ንም አል​ና​ቃ​ቸ​ው​ምና።


ነገር ግን ኀይ​ሌን እገ​ል​ጥ​ብህ ዘንድ፥ ስሜም በም​ድር ሁሉ ላይ ይነ​ገር ዘንድ ስለ​ዚህ ጠበ​ቅ​ሁህ።


አም​ላ​ካ​ችን በእ​ው​ነት የሚ​ያ​ቃ​ጥል እሳት ነውና።


ሙሴም እጁን በባ​ሕሩ ላይ ዘረጋ፤ ባሕ​ሩም ማለዳ ወደ መፍ​ሰሱ ተመ​ለሰ፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም ከእ​ርሱ ሸሹ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን በባ​ሕሩ መካ​ከል ጣላ​ቸው።


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​በላ እሳት፥ ቀና​ተ​ኛም አም​ላክ ነውና።


ሕዝ​ቡም ሁሉ ስለ ገለባ እብቅ ሊሰ​በ​ስቡ በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ተበ​ተኑ።


በልቡ ጠቢብ ነው፥ ኀይ​ለ​ኛም፥ ታላ​ቅም ነው፤ ክፉስ ሆኖ በፊቱ የቆመ ማን ነው?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios