Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 5:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 የእስራኤል ቅዱስ የሠራዊት አምላክ ያዘዘውን ሕግና ያስተማረውን ሥርዓት ስለ አቃለሉ ገለባና ድርቆሽ በእሳት ጋይቶ እንደሚጠፋ የእነርሱም ሥር መሠረት በስብሶ ይጠፋል፤ አበባቸውም ደርቆ እንደ ትቢያ ይበናል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ስለዚህ የእሳት ነበልባል ገለባን እንደሚበላ፣ ድርቆሽም በእሳት ጋይቶ እንደሚጠፋ፣ የእነርሱም ሥር እንዲሁ ይበሰብሳል፤ አበባቸውም እንደ ትቢያ ይበንናል፤ የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ሕግ ንቀዋልና፤ የእስራኤል ቅዱስ የተናገረውንም ቃል አቃልለዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ስለዚህ የእሳት ነበልባል ገለባን እንደሚበላ፤ ድርቆሽም በእሳት ጋይቶ እንደሚጠፋ፤ የእነርሱም ሥር እንዲሁ ይበሰብሳል፤ አበባቸውም እንደ ትቢያ ይበናል፤ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ሕግ ንቀዋልና፤ የእስራኤል ቅዱስ የተናገረውንም ቃል አቃለዋል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ስለ​ዚህ ገለባ በእ​ሳት ፍም እን​ደ​ሚ​ቃ​ጠል፥ በነ​በ​ል​ባ​ልም እን​ደ​ሚ​በላ፥ እን​ዲሁ የእ​ነ​ርሱ ሥር የበ​ሰ​በሰ ይሆ​ናል፤ አበ​ባ​ቸ​ውም እንደ ትቢያ ይበ​ን​ናል፤ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ ጥለ​ዋ​ልና፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቅዱስ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል አቃ​ል​ለ​ዋ​ልና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ስለዚህ የእሳት ወላፈን ቃርሚያን እንደሚበላ፥ እብቅም በነበልባል ውስጥ እንደሚጠፋ፥ እንዲሁ የእነርሱ ሥር የበሰበሰ ይሆናል ቡቃያቸውም እንደ ትብያ ይበንናል፥ የሠራዊትን ጌታ የእግዚአብሔርን ሕግ ጥለዋልና፥ የእስራኤልም ቅዱስ የተናገረውን ቃል አቃልለዋልና።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 5:24
44 Referencias Cruzadas  

የሰደብከውና የተዳፈርከው ማንን ነው? ድምፅህንስ ከፍ ያደረግኸው በማን ላይ ነው? በትዕቢትስ ዐይንህን ያነሣኸው በማን ላይ ነው? በእስራኤል ቅዱስ በእግዚአብሔር ላይ ነው።


“ነገር ግን እነርሱ በአንተ ላይ ዐምፀው ለቃልህ አንታዘዝም አሉ፤ ሕግህንም ላለመስማት ፊታቸውን መለሱ፤ በማስጠንቀቅ ወደ አንተ እንዲመለሱ ያስተማሩአቸውን ነቢያትህን ገደሉ፤ በየጊዜውም በአንተ ላይ ክፉ የስድብ ቃል ተናገሩ፤


ሥሩ ከመሠረቱ እንደሚደርቅና ቅርንጫፎቹም እንደሚረግፉ ዛፍ ይሆናል።


ሥሮቹም በድንጋይ ካብ ላይ ይጠመጠማሉ፤ በየቋጥኙም ላይ ይጣበቃሉ።


ስሕተትህን መታረም ትጠላለህ፤ ቃሎቼንም ትንቃለህ።


ግርማ በተሞላው ድል አድራጊነትህ ጠላትህን ገለበጥህ፤ ቊጣህ እንደ እሳት ስለ ነደደ እንደ ገለባ በላቸው።


ስለዚህ ሕዝቡ ገለባ ፈልገው ለማግኘት በመላይቱ የግብጽ ምድር ተሰማሩ።


ገለባ በእሳት ብልጭታ እንደሚጋይ “ኀይለኞች ነን” የሚሉ ሰዎች ይጠፋሉ፤ እንደ ቃጠሎ እሳት በእነርሱ ላይ የሚመጣውን ጥፋት የሚያቆም የለም።


እናንተ ኃጢአተኞች በደልን የተሸከማችሁ ወገኖች! የክፉ አድራጊዎችም ትውልድ! ሕይወታችሁ የተበላሸ፥ እግዚአብሔርን የተዋችሁና የእስራኤልን ቅዱስ የናቃችሁ በእርሱም ላይ ጀርባችሁን ያዞራችሁ ናችሁ።


ስለዚህም ርግማን ምድርን ያጠፋል፤ ሕዝቦችዋም በበደሉት በደል ተጠያቂዎች ይሆናሉ፤ ስለዚህ የምድር ነዋሪዎች ይደመሰሳሉ፤ የሚተርፉትም ጥቂቶች ናቸው።


አምላክ ሆይ፥ ክንድህ ለመቅጣት ተነሥቶአል፤ አንተን የሚጠሉ ሰዎች አያዩትም፤ ለሕዝብህ ምን ያኽል ቅናት እንዳለህ አይተው ይፈሩ፤ ለጠላቶችህ ባዘጋጀኸው ቅጣት ይጥፉ።


ስለዚህ የእስራኤል ቅዱስ ቃል ይህ ነው፦ “እናንተ ማስጠንቀቂያን ንቃችሁ ይደግፈናል ብላችሁ በተማመናችሁበት በግፍና በማታለል ላይ እምነታችሁን ጥላችኋል።


“እነርሱ ዘወትር የእግዚአብሔርን መመሪያ መስማት የማይፈልጉ ዐመፀኛ ዘርና የማይታመኑ ልጆች ናቸው።


“እነሆ፥ እነርሱ እንደ ገለባ እሳት ይበላቸዋል፤ ከነበልባሉ ኀይል ራሳቸውን ሊያድኑ አይችሉም፤ ገለባውም ራስን ለማሞቅ ፍም አይኖረውም።


እንዲሁም የእስራኤል ራስ ሰማርያ ስትሆን፥ የሰማርያም ራስ ንጉሥ ፋቁሔ ነው። “ጽኑ እምነት ባይኖራችሁ እናንተም አትጸኑም።”


“በጸጥታ የሚሄደውን የሰሊሆምን ምንጭ ውሃ ትተው በንጉሥ ረጺንና በንጉሥ ፋቁሔ ተደስተዋል፤


የሕዝቡ ክፋት ኲርንችቱንና እሾኹን እንደሚያቃጥል እሳት ነው፤ እንደ በረሓ እሳት ደኑን በሚያቃጥልበት ጊዜ ጢሱ ተትጐልጒሎ ሲወጣ ቀጥ ብሎ የቆመ ዐምድ ይመስላል።


የሠራዊት አምላክ ተቈጥቶአል፤ የቅጣቱም ፍርድ በአገሪቱ በሞላ እንደ እሳት ይነዳል፤ ሕዝቡም እንደ ማገዶ ይሆናል፤ ወንድም ለወንድሙ አይራራም።


ምድር ሆይ! ስሚ! እነርሱ ያስተማርኳቸውን ሥርዓት ስለ ተቃወሙ፤ ለሕጌም ስላልታዘዙ ስለ ክፉ ሐሳባቸው ሁሉ እቀጣቸው ዘንድ በሕዝቡ ላይ ጥፋትን አመጣለሁ።


ጥበበኞቻችሁ ኀፍረት ደርሶባቸዋል፤ በወጥመድ ተይዘውም ግራ ገብቶአቸዋል፤ እነርሱ ቃሌን ትተዋል፤ ታዲያ ምን ዐይነት ጥበብ ሊኖራቸው ይችላል?


ስለዚህ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በዱር ካሉ ዛፎች መካከል የወይንን ግንድ ለማገዶ እንዳደረግሁት የኢየሩሳሌምን ሕዝብ እንዲሁ አደርገዋለሁ።


እኔ በመካከላችሁ የምገኝ ቅዱሱ አምላክ ነኝ እንጂ ሰው አይደለሁም። ስለዚህ የቊጣዬን መቅሠፍት አላመጣም፤ ዳግመኛም እስራኤልን አላጠፋም፤ በቊጣዬም ወደ እናንተ አልመጣም።


ስለዚህ ብልና ነቀዝ እህልንና እንጨትን እንደሚያጠፉ እኔም እስራኤልንና ይሁዳን አጠፋለሁ።


የእስራኤል ሕዝብ ነፋስ እንደ መታው፥ ሥሩ እንደ ደረቀና ማፍራት እንደማይችል ዛፍ ያለ ፍሬ ይቀራሉ፤ ልጆች ቢወልዱም እጅግ የሚወዱአቸውን ልጆቻቸውን እገድላለሁ።”


እንደ ሠረገላ ድምፅ እያሰሙ በተራሮች ጫፍ ላይ ይዘላሉ፤ ገለባን እንደሚያቃጥል እሳትም፥ ሁሉን ነገር ያቃጥላሉ፤ ለጦርነት እንደ ተዘጋጀ ብርቱ ሠራዊት በሰልፍ ይተማሉ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የይሁዳ ሕዝብ ደጋግመው ስለ ሠሩት ኃጢአት ያለ ጥርጥር እቀጣቸዋለሁ፤ እነርሱ ሕጌን ጥሰዋል፤ ትእዛዜንም አልጠበቁም፤ አባቶቻቸው ይከተሉአቸው የነበሩት የሐሰት አማልክት እነርሱንም አስተዋቸዋል፤


“እኔ ግን ለእናንተ ስል ቁመታቸው እንደ ሊባኖስ ዛፍ፥ ብርታታቸው እንደ ዋርካ ዛፍ የነበረውን አሞራውያንን ከነሥር መሠረታቸው ነቃቅዬ አጠፋሁላችሁ፤


እናንተ ሰካራሞች! እርስ በርሱ የተያያዘ እሾኽና ድርቆሽ በእሳት ተቃጥሎ እንደሚጠፋ፥ እናንተም እንዲሁ ትጠፋላችሁ።


የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ ትዕቢተኞችና ክፉ አድራጊዎች እንደ ገለባ በእሳት የሚቃጠሉበት ጊዜ እየመጣ ነው፤ የሚመጣውም ከእነርሱ ሥር፥ ወይም ቅርንጫፍ ሳያስቀር ሁሉንም ያቃጥላል።


እርሱ መንሹ በእጁ ነው። በእርሱም አውድማውን ደኅና አድርጎ ያጠራል። ስንዴውን በጐተራ ይከተዋል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።”


እንደገናም ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፦ “እናንተን የሚሰማ እኔን ይሰማል፤ እናንተን የማይቀበል እኔን አይቀበልም፤ እኔን የማይቀበልም የላከኝን አይቀበልም፤” አላቸው።


እርሱ በአውድማ ላይ እህሉን ከገለባ ለመለየት መንሹን በእጁ ይዞአል፤ ካጣራውም በኋላ ጥሩውን እህል በጐተራው ይከታል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።”


ፈሪሳውያንና የሕግ መምህራን ግን በዮሐንስ እጅ አንጠመቅም በማለት የእግዚአብሔርን ፈቃድ ተቃውመው ነበር።


እኔን የማይፈልግና ቃሌንም የማይቀበለውን ሰው የሚፈርድበት አለ፤ እኔ የተናገርኩት ቃል በመጨረሻው ቀን ይፈርድበታል።


‘እናንተ ፌዘኞች እዩ! ተደነቁ! ጥፉም! ማንም ሰው ቢያወራላችሁ የማታምኑትን ሥራ በዘመናችሁ እሠራለሁ።’ ”


በዝናብ ፈንታ እስክትጠፋ ድረስ እግዚአብሔር በአንተ ላይ በዐውሎ ነፋስ የሚነዳ ትቢያና አሸዋ ይልክብሃል።


ስለዚህ ይህን ምክር የሚቃወም፥ የሚቃወመው ቅዱስ መንፈሱን የሚሰጣችሁን እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን አይደለም።


በእግዚአብሔር ላይ ማመፅ እንደ ሟርተኛነት፥ የትዕቢት እልኸኛነትም ጣዖትን በማምለክ ኃጢአት እንደ መሥራት ይቈጠራል፤ አንተ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ስለ ተውክ በንጉሥነትህ እንዳትቀጥል እርሱም አንተን ትቶሃል።”


ሳሙኤልም “እኔ ከአንተ ጋር አልሄድም፤ አንተ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መፈጸም ትተሃል፤ አንተም የእስራኤል ንጉሥ ሆነህ እንዳትቀጥል እርሱ ትቶሃል” ሲል መለሰለት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos