ልያም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅንም ወለደች፥ ስሙንም ሮቤል ብላ ጠራችው፥ “እግዚአብሔር መዋረዴን አይቶአልና፥ እንግዲህስ ወዲህ ባሌ ይወድደኛል” ስትል።
ዘፍጥረት 49:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ሮቤል እርሱ የበኵር ልጄና ኀይሌ፥ የልጆችም መጀመሪያ ነው፤ ክፉ ሆነ፤ አንገቱንም አደነደነ። ጭንቅ ነገርንም አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሮቤል፣ አንተ የበኵር ልጄ ነህ፤ ኀይሌና የጕብዝናዬም መጀመሪያ፤ በክብር ትልቃለህ፤ በኀይልም ትበልጣለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሮቤል፥ አንተ በኩር ልጄና ኃይሌ፥ የጉብዝናዬም መጀመሪያ፥ የክብር አለቃና የኃይል አለቃ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሮቤል፥ ኀይልና የጐልማሳነት ብርታት በነበረኝ ጊዜ፥ የወለድኩህ የበኲር ልጄ ነህ። ከልጆቼ ሁሉ በክብርና በኀይል የምትበልጥ አንተ ነህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሮቤል አንተ በኵር ልጄና ኃይሌ የጕብዝናዬም መጀመሪያ ነህ፤ የክብር አለቃና የኃይል አለቃ። |
ልያም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅንም ወለደች፥ ስሙንም ሮቤል ብላ ጠራችው፥ “እግዚአብሔር መዋረዴን አይቶአልና፥ እንግዲህስ ወዲህ ባሌ ይወድደኛል” ስትል።
ከአባታቸው ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብፅ የገቡት የእስራኤል ልጆች ስም ይህ ነው፤ ያዕቆብና ልጆቹ፤ የያዕቆብ በኵር ሮቤል።
የእስራኤልም በኵር የሮቤል ልጆች እነዚህ ናቸው። እርሱ የበኵር ልጅ ነበረ፤ ነገር ግን ወደ አባቱ ምንጣፍ ስለ ወጣ አባቱ እስራኤል በረከቱን ለልጁ ለዮሴፍ ሰጠ፤ ብኵርናም አልተቈጠረለትም።
የእስራኤል በኵር የሮቤል ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገናቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች እንደ እየስማቸው ቍጥር፥ በየራሳቸው፥ ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለው ወንድ ሁሉ፥ ወደ ሰልፍ የሚወጡት ሁሉ፥
ነገር ግን ከከብቱ ሁለት እጥፍ ለእርሱ በመስጠት ከተጠላችው ሚስት የተወለደው ልጅ በኵር እንደ ሆነ ያስታውቅ። የኀይሉ መጀመሪያ ነውና በኵርነቱ የእርሱ ነው።
“በሎዲቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፡ አሜን የሆነው፥ የታመነውና እውነተኛው ምስክር፥ በእግዚአብሔርም ፍጥረት መጀመሪያ የነበረው እንዲህ ይላል፦