1 ዜና መዋዕል 2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 የእስራኤልም ልጆች ስሞች እነዚህ ናቸው፤ ሮቤል፥ ስምዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮር፥ ዛብሎን፤ 2 ዳን፥ ዮሴፍ፥ ብንያም፥ ንፍታሌም፥ ጋድ፥ አሴር። 3 የይሁዳ ልጆች፤ ዔር፥ አውናን፥ ሴሎም፤ እነዚህ ሦስቱ ከከነዓናዊቱ ሴት ከሴዋ ልጅ ተወለዱለት። የይሁዳም የበኵር ልጅ ዔር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነበረ፤ ገደለውም። 4 ምራቱም ትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደችለት፤ የይሁዳም ልጆች ሁሉ አምስት ነበሩ። 5 የፋሬስ ልጆች፤ ኤስሮም፥ ያሙሔል። 6 የዛራም ልጆች፤ ዘምሪ፥ ኤታን፥ ኤማን፥ ካልኮል፥ ዳራ፤ ሁሉም አምስት ነበሩ። 7 የዘምሪም ልጅ ከርሚ ነው፤ የከርሚም ልጅ እስራኤልን ያስጨነቀ፥ እርሙን ሰርቆ የበደለ አካን ነበረ። 8 የኤታንም ልጅ አዛርያ ነበረ። 9 ለኤስሮም የተወለዱለት ልጆች፤ ኢያሬሄም፥ አራም፥ ካሌብ ነበሩ። 10 አራምም አሚናዳብን ወለደ፤ አሚናዳብም የይሁዳን ልጆች አለቃ ነአሶንን ወለደ፤ 11 ነአሶንም ሰልሞንን ወለደ፤ ሰልሞን ቦዔዝን ወለደ፤ 12 ቦዔዝም ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፤ 13 እሴይም የበኵር ልጁን ኤልያብን፥ ሁለተኛውንም አሚናዳብን፥ ሦስተኛውንም ሣማን፥ 14 አራተኛውንም ናትናኤልን፥ አምስተኛውንም ራዳይን፥ 15 ስድስተኛውንም አሶንን፥ ሰባተኛውንም ዳዊትን ወለደ፤ 16 እኅቶቻቸውም ሶርህያና አቢግያ ነበሩ። የሶርህያም ልጆች አቢሳ፥ ኢዮአብ፥ አሣሄል እኒህ ሦስቱ ነበሩ። 17 አቢግያም አሜሳይን ወለደች፤ የአሜሳይም አባት እስማኤላዊው ይትኤር ነበረ። 18 የኤስሮምም ልጅ ካሌብ ዐዙባ የምትባል ሚስት አገባ፥ ይሪዖትንም አገባ፤ ልጆችዋም ያሳር፥ ሶባብ፥ ኤርኖን ነበሩ። 19 ዐዙባም ሞተች፥ ካሌብም ኤፍራታን አገባ፤ እርስዋም ኦርን ወለደችለት። 20 ኦርም ኡሪን ወለደ፥ ኡሪም ባስልኤልን ወለደ። 21 ከዚያም በኋላ ኤስሮም ስድሳ ዓመት በሆነው ጊዜ ወደ አገባት ወደ ገለዓድ አባት ወደ ማኬር ልጅ ገባ፤ ሴጉብንም ወለደችለት። 22 ሴጉብም ኢያኤርን ወለደ፤ ለእርሱም በገለዓድ ምድር ሃያ ሦስት ከተሞች ነበሩት። 23 ኤስሮምም ጌሱርንና አራምን የኢያዔርን ከተሞች ከቄናትና ከመንደሮችዋ ጋር ስድሳውን ከተሞች ወሰደ። እነዚህ ሁሉ የገለዓድ አባት የማኪር ልጆች ከተሞች ነበሩ። 24 ኤስሮምም ከሞተ በኋላ ካሌብ ወደ ኤፍራታ መጣ። የኤስሮምም ሚስት አብያ የቴቁሔን አባት አስሖርን ወለደችለት። 25 የኤስሮምም የበኵር ልጁ የኢያሬምሄል ልጆች በኵሩ ራም፥ በአናን፥ አራን፥ አሶም፥ አኪያ ነበሩ። 26 ለኢያሬምሄልም አጥራ የተባለች ሌላ ሚስት ነበረችው፤ እርስዋም የአናም እናት ነበረች። 27 የኢያሬምሄል የበኵሩ የራም ልጆች ማኦስ፥ ኢያቢን ዔቄር ነበሩ። 28 የአናምም ልጆች ሸማይና ያዳይ ነበሩ። የሸማይም ልጆች ናዳብና አቢሱር ነበሩ። 29 የአቢሱርም ሚስት ስም አቢካኤል ነበረ፤ እርስዋም፥ አዛቡርንና ሞሊድን ወለደችለት። 30 የናዳብም ልጆች ሴሌድና አፋይም ነበሩ፤ ሴሌድም ልጆችን ሳይወልድ ሞተ። 31 የአፋይምም ልጅ ይሲ፥ የይሲም ልጅ ሶሳን፥ የሶሳንም ልጅ አሕላይ ነበረ። የአሕላይም ልጅ ይዳይ ነበረ። 32 የይዳይ ልጆች አክሲም፥ ዮቴርና ዮናታን ነበሩ፤ ዮቴርም ልጆችን ሳይወልድ ሞተ። 33 የዮናታንም ልጆች ፋሌትና አዛዝ ነበሩ፤ እነዚህም የኢያሬምሔል ልጆች ነበሩ። 34 ለሶሳንም ሴቶች ልጆች እንጂ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፤ ለሶሳንም ኢዮሄል የተባለ ግብፃዊ አገልጋይ ነበረው። 35 ሶሳንም ለአገልጋዩ ለኢዮሄል ልጁን አጋባት፥ እርስዋም ያቲን ወለደችለት። 36 ያቲም ናታንን ወለደ፤ ናታንም ዛቤትን ወለደ፤ 37 ዛቤትም አውፋልን ወለደ፤ አውፋልም ዖቤድን ወለደ፤ 38 ዖቤድም ኢያሁን ወለደ፤ ኢያሁም አዛርያስን ወለደ፤ 39 አዛርያስም ኬሌስን ወለደ፤ ኬሌስም ኤልዓሳን ወለደ፤ 40 ኤልዓሳም ሲስማኤልን ወለደ፤ ሲስማኤልም ሱላምን ወለደ፤ 41 ሱላምም ኢዮቆምን ወለደ፤ ኢዮቆምም ኤልሳማን ወለደ። 42 የኢያሬምሄል ወንድም የካሌብ ልጆች በኵር የዚፍ አባት ማሪስ ነው፤ የኬብሮንም አባት የማሪስ ልጆች ነበሩ። 43 የኬብሮንም ልጆች፤ ቆሬ፥ ተፋ፥ ሬቆምና፥ ሴማዓ ነበሩ። 44 ሴማዓም የኤርቃምን አባት ራኤምን ወለደ፤ ኤርቃምም ሰማኤምን ወለደ። 45 የሰማኤምም ልጅ ማዖን ነበረ፤ ማዖንም የቤት ሱር አባት ነበረ። 46 የካሌብም ዕቅብት ጌፋ አራንን፥ ሞሳን፥ ጋዜዝን ወለደች። አራንም ጊዚኢን ወለደ። 47 የያዳይም ልጆች፤ ሬጌም፥ ዮታም፥ ጌርሶም፥ ፋሌጥ፥ ጌፋና፥ ሰጋፍ ነበሩ። 48 የካሌብም ዕቅብት ማዕካ ሴብርንና ቲርሐናን ወለደች። 49 ደግሞም የምድሜናን አባት ስጋብን የመክቢናንና የጌባልን አባት ሳዑልን ወለደች፤ የካሌብም ሴት ልጅ አስካ ነበረች። 50 የካሌብም ልጆች እነዚህ ነበሩ፤ የኤፍራታ የበኵሩ የኦር ልጅ የቀርያታርም አባት ሶባል ነበር፥ 51 የቤተ ልሔም አባት ሰልሞን፥ የቤት ጋዲር አባት ኦሪ። 52 የቀርያታርምም አባት የሶባል ልጆች አረኤ፥ ሃጼ፥ አማኒት ነበሩ። 53 የቀርያታርም ወገኖች፤ ይትራውያን፥ ፋታውያን፥ ሹማታውያን፥ ሚሸራውያን፤ ከእነዚህም ሶራሐውያንና ኤሽታአላውያን ወጡ። 54 የሰልሞንም ልጆች ቤተ ልሔም፥ ነጦፋውያን፥ አጦሮት ቤትዮአብ፥ የመናሕታውያን እኩሌታ፥ ሰራዓውያንም ነበሩ። 55 በያቤጽም የተቀመጡ የጸሓፊዎች ወገኖች፤ ቴርዓውያን፥ ሹማታውያን፥ ሡካታውያን ነበሩ፤ እነዚህ ከሬካብ ቤት አባት ከሐማት የወጡ ቄናውያን ናቸው። |