Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 35:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 የልያ ልጆች፤ የያ​ዕ​ቆብ በኵር ልጅ ሮቤል፥ ስም​ዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳ​ኮር፥ ዛብ​ሎን፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 የልያ ልጆች፦ የያዕቆብ የበኵር ልጅ ሮቤል፣ ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ ይሳኮር፣ ዛብሎን፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 የልያ ልጆች፥ የያዕቆብ በኩር ልጅ ሮቤል፥ ስምዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮር፥ ዛብሎን፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 የልያ ልጆች፥ የያዕቆብ የመጀመሪያ ልጅ ሮቤል፥ ስምዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮርና ዛብሎን ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 የያዕቆብም ልጆች አሥራ ሁለት ናቸው የልያ ልጆች የያዕቆብ በኵር ልጅ ሮቤል ስምዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮር፥ ዛብሎን፤

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 35:23
33 Referencias Cruzadas  

ዕቁ​ባ​ቶ​ቹ​ንና ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም በፊት አደ​ረገ፤ ልያ​ንና ልጆ​ች​ዋን በኋላ፥ ራሔ​ል​ንና ዮሴ​ፍ​ንም ከሁሉ በኋላ አደ​ረገ።


የግ​ዝ​ረ​ት​ንም ኪዳን ሰጠው፤ ከዚ​ህም በኋላ ይስ​ሐ​ቅን ወለደ፤ በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀንም ገረ​ዘው፤ እን​ዲሁ ይስ​ሐ​ቅም ያዕ​ቆ​ብን፥ ያዕ​ቆ​ብም ዐሥራ ሁለ​ቱን የቀ​ደሙ አባ​ቶ​ችን ገረዙ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ልያ የተ​ጠ​ላች መሆ​ን​ዋን በአየ ጊዜ ማኅ​ፀ​ን​ዋን ከፈ​ተ​ላት፤ ራሔል ግን መካን ነበ​ረች።


ከአ​ባ​ታ​ቸው ከያ​ዕ​ቆብ ጋር ወደ ግብፅ የገ​ቡት የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ስሞች እነ​ዚህ ናቸው፤ ሰው ሁሉ ከቤተ ሰቡ ጋር ገባ፤


ለላ​ባም ሁለት ሴቶች ልጆች ነበ​ሩት፤ የታ​ላ​ቂቱ ስም ልያ የታ​ና​ሺ​ቱም ስም ራሔል ነበረ።


“ሮቤል እርሱ የበ​ኵር ልጄና ኀይሌ፥ የል​ጆ​ችም መጀ​መ​ሪያ ነው፤ ክፉ ሆነ፤ አን​ገ​ቱ​ንም አደ​ነ​ደነ። ጭንቅ ነገ​ር​ንም አደ​ረገ።


ከእ​ና​ን​ተም ጋር የሚ​ቆ​ሙት ሰዎች ስሞ​ቻ​ቸው እነ​ዚህ ናቸው፤ ከሮ​ቤል የሰ​ዲ​ዮር ልጅ ኤሊ​ሱር፥


የእ​ስ​ራ​ኤል በኵር የሮ​ቤል ልጆች በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው፥ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች እንደ እየ​ስ​ማ​ቸው ቍጥር፥ በየ​ራ​ሳ​ቸው፥ ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያለው ወንድ ሁሉ፥ ወደ ሰልፍ የሚ​ወ​ጡት ሁሉ፥


በመ​ጀ​መ​ሪያ በም​ሥ​ራቅ በኩል የሚ​ሰ​ፍ​ሩት ከሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር የይ​ሁዳ ሰፈር ሰዎች ይሆ​ናሉ፤ የይ​ሁዳ ልጆ​ችም አለቃ የአ​ሚ​ና​ዳብ ልጅ ነአ​ሶን ነበረ።


በመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ቀን መባ​ውን ያቀ​ረበ ከይ​ሁዳ ነገድ የአ​ሚ​ና​ዳብ ልጅ ነአ​ሶን ነበረ።


በመ​ጀ​መ​ሪ​ያም የይ​ሁዳ ልጆች ሰፈር በሥ​ር​ዐ​ታ​ቸው ከየ​ሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር ተጓዘ፤ በሠ​ራ​ዊ​ቱም ላይ የአ​ሚ​ና​ዳብ ልጅ ነአ​ሶን አለቃ ነበረ።


ስማ​ቸ​ውም ይህ ነበረ፤ ከሮ​ቤል ነገድ የዝ​ኩር ልጅ ሰሙ​ኤል፤


የእ​ስ​ራ​ኤል በኵር ሮቤል፤ የሮ​ቤል ልጆች፤ ከሄ​ኖኅ የሄ​ኖ​ኃ​ው​ያን ወገን፤ ከፈ​ሉስ የፈ​ሉ​ሳ​ው​ያን ወገን።


የሰ​ዎ​ቹም ስም ይህ ነው፤ ከይ​ሁዳ ነገድ የዮ​ፎኒ ልጅ ካሌብ፥


ሙሴም በዚያ ቀን እን​ዲህ ብሎ ሕዝ​ቡን አዘዘ፦


ሮቤ​ልን እፈ​ል​ገ​ዋ​ለሁ፤ አይ​ሙ​ት​ብኝ፤ ቍጥ​ሩም ብዙ ይሁን።


ሙሴም ለሮ​ቤል ነገድ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው ርስ​ትን ሰጣ​ቸው።


የይ​ሁ​ዳም ነገድ ድን​በር በየ​ወ​ገ​ና​ቸው ከኤ​ዶ​ም​ያስ ዳርቻ፥ ከጺን ምድረ በዳ ጀምሮ በዐ​ዜብ በኩል እስከ ቃዴስ ድረስ ነው።


ሁለ​ተ​ኛ​ውም ዕጣ ለስ​ም​ዖን ልጆች ነገድ በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ወጣ፤ ርስ​ታ​ቸ​ውም በይ​ሁዳ ልጆች ርስት መካ​ከል ነበረ።


ሦስ​ተ​ኛ​ውም ዕጣ ለዛ​ብ​ሎን ልጆች በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ወጣ፤ የር​ስ​ታ​ቸ​ውም ድን​በር እስከ ኤሴ​ዴቅ ጎላ ነበረ፤


አራ​ተ​ኛ​ውም ዕጣ ለይ​ሳ​ኮር ልጆች ወጣ።


በአ​ማ​ሌቅ ዘንድ ሥር የነ​በ​ራ​ቸው እነ​ርሱ ከኤ​ፍ​ሬም፥ ብን​ያም ሆይ! በሕ​ዝብ መካ​ከል ከአ​ንተ በኋላ ወረዱ፤ አለ​ቆች ከማ​ኪር፥ የን​ጉ​ሥ​ንም ዘንግ የሚ​ይዙ ከዛ​ብ​ሎን ወረዱ።


የይ​ሳ​ኮ​ርም አለ​ቆች ከዲ​ቦራ ጋር ነበሩ፤ ይሳ​ኮ​ርም እንደ ባርቅ ነበረ፤ ከእ​ግሩ በኋላ ወደ ሸለ​ቆው ቸኮሉ፤ በሮ​ቤል ፈሳ​ሾች አጠ​ገብ ብዙ የልብ ማመ​ን​ታት ነበረ።


ዛብ​ሎን ነፍ​ሱን ወደ ሞት ያሳ​ለፈ ሕዝብ ነው፤ ንፍ​ታ​ሌ​ምም በሀ​ገሩ ኮረ​ብታ ላይ ነው።


በከተማይቱ በር አደባባይም የነበሩ ሕዝብ ሁሉ ሽማግሌዎቹም፦ እኛ ምስክሮች ነን፣ እግዚአብሔር ይህችን ወደ ቤትህ የምትገባውን ሴት የእስራኤልን ቤት እንደ ሠሩ እንደ ሁለቱ እንደ ራሔልና እንደ ልያ ያድርጋት፣ አንተም በኤፍራታ ባለ ጠጋ ሁን፥ ስምህም በቤተ ልሔም ይጠራ።


ለሰ​ልፍ ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰዎች የነ​በሩ የስ​ም​ዖን ልጆች ሰባት ሺህ አንድ መቶ ነበሩ።


በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገ​ዶች ላይ እነ​ዚህ ነበሩ፦ በሮ​ቤ​ላ​ው​ያን ላይ የዝ​ክሪ ልጅ ኤል​ያ​ዛር አለቃ ነበረ፤ በስ​ም​ዖ​ና​ው​ያን ልጅ የመ​ዓካ ልጅ ሰፋ​ጥ​ያስ ነበረ፤


“የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም መው​ጫ​ዎች እነ​ዚህ ናቸው። በሰ​ሜን ወገን ልኩ አራት ሺህ አም​ስት መቶ ክንድ ነው።


ከስምዖን ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከሌዊ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከይሳኮር ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios