Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


መዝሙር 105 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ሃሌ ሉያ።

1 ቸር ነውና፥ ምሕ​ረ​ቱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ።

2 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ኀይል ማን ይና​ገ​ራል? ምስ​ጋ​ና​ው​ንስ ሁሉ ይሰማ ዘንድ ማን ያደ​ር​ጋል?

3 ፍር​ድን የሚ​ጠ​ብቁ፥ ጽድ​ቅ​ንም ሁል​ጊዜ የሚ​ያ​ደ​ርጉ ብፁ​ዓን ናቸው።

4 አቤቱ፥ ሕዝ​ብ​ህን በይ​ቅ​ር​ታህ ዐስ​በን፥ በማ​ዳ​ን​ህም ይቅር በለን፤

5 የመ​ረ​ጥ​ሃ​ቸ​ውን በጎ​ነት እናይ ዘንድ፥ በሕ​ዝ​ብ​ህም ደስታ ደስ ይለን ዘንድ፥ ከር​ስ​ት​ህም ጋር እን​ከ​ብር ዘንድ።

6 ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ጋር ኃጢ​አት ሠራን፥ ዐመ​ፅ​ንም፥ በደ​ል​ንም።

7 አባ​ቶ​ቻ​ችን በግ​ብፅ ሀገር ሳሉ ተአ​ም​ራ​ት​ህን አላ​ስ​ተ​ዋ​ሉም፥ የም​ሕ​ረ​ት​ህ​ንም ብዛት አላ​ሰ​ቡም፤ በኤ​ር​ትራ ባሕር ባለፉ ጊዜ አስ​መ​ረ​ሩህ።

8 ኀይ​ሉን ያሳ​ያ​ቸው ዘንድ ስለ ስሙ አዳ​ና​ቸው።

9 የኤ​ር​ት​ራ​ንም ባሕር ገሠ​ጻት፥ ደረ​ቀ​ችም፤ እንደ ምድረ በዳ በጥ​ልቅ መራ​ቸው።

10 ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም እጅ አዳ​ና​ቸው፥ ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም እጅ ተቤ​ዣ​ቸው።

11 ያሳ​ደ​ዱ​አ​ቸ​ው​ንም ውኃ ደፈ​ና​ቸው፥ ከእ​ነ​ር​ሱም አንድ ስንኳ አል​ቀ​ረም።

12 ያን​ጊ​ዜም በቃሉ አመኑ፥ በም​ስ​ጋ​ና​ውም አመ​ሰ​ገ​ኑት።

13 ፈጥ​ነ​ውም ሥራ​ውን ረሱ፥ በም​ክ​ሩም አል​ጸ​ኑም።

14 በም​ድረ በዳም ምኞ​ትን ተመኙ፥ በበ​ረ​ሃም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አሳ​ዘ​ኑት።

15 የለ​መ​ኑ​ት​ንም ሰጣ​ቸው፤ ለነ​ፍ​ሳ​ች​ውም ጥጋ​ብን ላከ።

16 ሙሴ​ንም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቀ​ደ​ሰ​ውን አሮ​ን​ንም በሰ​ፈር አስ​ቈ​ጧ​ቸው።

17 ምድር ተከ​ፈ​ተች፥ ዳታ​ን​ንም ዋጠ​ችው፥ የአ​ቤ​ሮ​ን​ንም ወገን ደፈ​ነች፤

18 በማ​ኅ​በ​ራ​ቸው እሳት ነደ​ደች፥ ነበ​ል​ባ​ልም ኃጥ​ኣ​ንን አቃ​ጠ​ላ​ቸው።

19 በኮ​ሬ​ብም ጥጃን ሠሩ፥ ቀልጦ ለተ​ሠራ ምስ​ልም ሰገዱ።

20 ሣር​ንም በሚ​በላ በበሬ ምሳሌ ክብ​ራ​ቸ​ውን ለወጡ።

21 ያዳ​ና​ቸ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ረሱ። ታላቅ ነገ​ር​ንም በግ​ብፅ፥

22 ድን​ቅ​ንም በካም ምድር፥ ግሩም ነገ​ር​ንም በኤ​ር​ትራ ባሕር ያደ​ረ​ገ​ውን።

23 እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋ​ቸው የቍ​ጣ​ውን መቅ​ሠ​ፍት ይመ​ልስ ዘንድ የተ​መ​ረ​ጠው ሙሴ በመ​ቅ​ሠ​ፍት ጊዜ በፊቱ ባይ​ቆም ኖሮ፥ ባጠ​ፋ​ቸው ነበር አለ።

24 የተ​ወ​ደ​ደ​ች​ው​ንም ምድር ናቁ፥ በቃ​ሉም አል​ታ​መ​ኑም፥

25 በድ​ን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸ​ውም ውስጥ አን​ጐ​ራ​ጐሩ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል አል​ሰ​ሙም።

26 እጁ​ንም አነ​ሣ​ባ​ቸው። በም​ድረ በዳ ይጥ​ላ​ቸው ዘንድ፥

27 ዘራ​ቸ​ው​ንም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ይጥል ዘንድ፥ በየ​ሀ​ገ​ሩም ይበ​ት​ና​ቸው ዘንድ።

28 በብ​ዔል ፌጎ​ርም ዐለቁ፥ የሞተ መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም በሉ፤

29 በሥ​ራ​ቸ​ውም አነ​ሣ​ሱት ቸነ​ፈ​ርም በላ​ያ​ቸው በዛ።

30 ፊን​ሐ​ስም ተነ​ሥቶ አዳ​ና​ቸው፥ ቸነ​ፈ​ሩም ተወ።

31 ያም እስከ ዘለ​ዓ​ለም ለልጅ ልጅ ጽድቅ ሆኖ ተቈ​ጠ​ረ​ለት።

32 በክ​ር​ክር ውኃ ዘን​ድም አስ​ቈ​ጡት፥ ስለ እነ​ር​ሱም ሙሴ ተበ​ሳጨ፤

33 መን​ፈ​ሱን አስ​መ​ር​ረ​ዋ​ታ​ልና፤ በከ​ን​ፈ​ሮ​ቹም አዘዘ።

34 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ላ​ቸው አሕ​ዛ​ብን አላ​ጠ​ፉም፤

35 ከአ​ሕ​ዛብ ጋር ተደ​ባ​ለቁ፥ ሥራ​ቸ​ው​ንም ተማሩ።

36 ለጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ተገዙ፥ በደ​ልም ሆነ​ባ​ቸው።

37 ወን​ዶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ለአ​ጋ​ን​ንት ሠዉ፤

38 ንጹሕ ደም​ንም አፈ​ሰሱ፥ የወ​ን​ዶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንና የሴ​ቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ደም፥ ለከ​ነ​ዓን ጣዖ​ቶች ሠዉ፥ ምድ​ርም በደም ታለ​ለች።

39 በሥ​ራ​ቸ​ውም ረከ​ሰች፥ በጣ​ዖ​ታ​ቸ​ውም አመ​ነ​ዘሩ።

40 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሕ​ዝቡ ላይ ቍጣን ተቈጣ፥ ርስ​ቱ​ንም ተጸ​የፈ።

41 በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው። የሚ​ጠ​ሉ​አ​ቸ​ውም ገዙ​አ​ቸው።

42 ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አሠ​ቃ​ዩ​አ​ቸው፥ ከእ​ጃ​ቸ​ውም በታች ተዋ​ረዱ።

43 ብዙ ጊዜ አዳ​ና​ቸው፤ እነ​ርሱ ግን በም​ክ​ራ​ቸው አስ​መ​ረ​ሩት፥ በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸ​ውም መከራ ተቀ​በሉ።

44 እንደ ተጨ​ነ​ቁም ተመ​ለ​ከ​ታ​ቸው፥ ጸሎ​ታ​ቸ​ው​ንም ሰማ​ቸው፤

45 ለእ​ነ​ር​ሱም ኪዳ​ኑን አሰበ፥ እንደ ምሕ​ረ​ቱም ብዛት አዘ​ነ​ላ​ቸው።

46 በማ​ረ​ኩ​አ​ቸ​ውም ሁሉ ፊት ይቅ​ር​ታን ሰጣ​ቸው።

47 አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ አድ​ነን፤ ቅዱስ ስም​ህን እና​መ​ሰ​ግን ዘንድ፥ በም​ስ​ጋ​ና​ህም እን​መካ ዘንድ፥ ከአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ሰብ​ስ​በን።

48 ከዘ​ለ​ዓ​ለም እስከ ዘለ​ዓ​ለም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ይሁን ይሁን ይበል።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos